Get Mystery Box with random crypto!

ፊትና 'ፊትና እንቅልፍ ላይ ነች፤ የቀሰቀሳት የአላህ እርግማን በሷ ላይ ይሁን፡፡” የሚል ብሂል | ABX

ፊትና

"ፊትና እንቅልፍ ላይ ነች፤ የቀሰቀሳት የአላህ እርግማን በሷ ላይ ይሁን፡፡” የሚል ብሂል አለ፡፡ አባባሉ ዐረብኛ ነው፡፡ ሐዲሥ ሁሉ ይመስለኝ ነበር፡፡
“ፊትና” ማለት እኩይ ዓላማን በማንገብ በሰዎች መካከል ጥላቻን፣ መቃቃርን፣ መጣላትን፣ የሚያመጣ የሀሠት ወሬ፣ ቅጥፈት፣ ነገር፣ ተንኮል፣ ሀሜት፣ ዉዥንብር መርጨት ነው፡፡ ታላቆቹን ኸሊፋዎች ዑሥማንና ዐሊን ያስገደላቸው መናፍቃን የቀሰቀሱት ፊት ነው፡፡ የዘመናችን መናፍቃን ፊትና ደግሞ ከዚያ ዘመን የባሰ ነው፡፡
ከላይ የጠቀስኩት አባባል መነሻው ግን እንዲህ ነው ይለኛል ዛሬ ያነበብኩት ጽሑፍ፡፡
አንድ ሰዉዬ “ፊትና” የምትባል ሴት አገባ አሉ፡፡ በዉበቷ “ፈታኝ፣ አደገኛ” እንደማለት ነው እዚህ ጋ ትርጉሙ፡፡ ሰዉዬው በርግጥ ሲያገባት መልኳን አላየም ነበር አሉ፡፡ ከስሟ በመነሳት ግን እጅግ ቆንጆ እና በዉበቷም ፈታኝ ልትሆን እንደምትችል ገመተ፡፡ ለነገሩ እኛም ወጣት እያለን ቆንጆ የሆነችን ሴት “ቂያማ” እንል ነበር፡፡ አይ ወጣትነት!፡፡ እሣት እንደማለት፡፡

እና ሰውዬው ገና ሙሽሪት ፊትና ወዳለችበት ጓዳ ሲገባ መልከጥፉ ሆና አገኛት አሉ፡፡ ተኝታ ነበርና ሳታያየው ቀስብሎ ወደኋላ ተመልሶ ሹልክ ብሎ ወጣ፡፡
ከቤቱ ሲወጣ እናቱ አየችው “ እንዴ ወዴት እየሄድክ ነው!” አለችው አሉ፡፡ (አሉ ነው እንግዲህ)
“መጓዜ ነው አገር መልቀቄ ነው፡፡” አላት፡፡
“እንዴ ፊትናስ?” አለችው፡፡
“ፊትናማ ተኝታለች፤ የቀሰቀሳት የአላህ እርግማን በሷ ላይ ይሁን፡፡” አላት አሉ፡፡
እና ጉዳያችን ወዲህ ነው፡፡
በሙስሊሙ መካከል ዉዥንብር የሚፈጥር፣ አንድነታቸዉን የሚያናጋ፣ ጥቅሙን ከእስልምናን ጥቅም ያስቀደመዉን፣ ከማኅበረሰቡ ጥቅም ይልቅ ለሥልጣኑ የሚሟተው የሙስሊሙ ትልቅ ፈተናችን ነዉና…….. ከማለት ዉጭ ምን እንላለን፡፡


    http://t.me/MuhammedSeidABX