Get Mystery Box with random crypto!

ሰው .... ***, ከደረሱን ተረቶች መካከል … ለአህያ እንዲህ ተባለ - “ያለ ዕረፍት ከጠዋት | ABX

ሰው ....

***,
ከደረሱን ተረቶች መካከል …

ለአህያ እንዲህ ተባለ -
“ያለ ዕረፍት ከጠዋት እስከ ማታ ትሠራለህ ፤ ትላልቅ ሸክሞችን ትሸከማለህ፣ እንደለፋህ ትኖራለህ፣ በዚህም በምድር ላይ የሀምሳ ዓመት ዕድሜ ተሠጥቶሃል፡፡”

አህያም አለ “በርግጥ አህያ ልሁን፤ ነገርግን ሀምሳ ዓመት ብዙ ነው፤ ሀያ ዓመት ይብቃኝ” ፡፡ ለአህያም የጠየቀው ዕድሜ ተሠጠው፡፡

ለዉሻም እንዲህ ተባለ፡፡
“ ሥራህ የሰዉን ልጅ ቤት መጠበቅ ይሆናል፤ ከሰዎች አትርቅም፣ ከትራፊዉና ከሚጣልልህ ትበላለህ፣ የምድር ላይ ሕይወትህ ይህ ይሆናል፡፡  የሰላሳ ዓመት ዕድሜም ይሠጥሃል፡፡”
ዉሻም “ምድር ላይ የሰላሳ ዓመት ዕድሜ ብዙ ነው፣ አሥራ አምስት ይበቃኛል፡፡” አለ፡፡ የጠየቀው ተሠጠው፡፡

ለዝንጀሮም እንዲህ ተባለ “ከቅርንጫፍ ወደ ቅርንጫፍ እየዘለልክ ሕይወትን ትኖራለህ፣ ሰዎችም አንተን በማየትና ካንተ ጋር በመጫወት ይዝናናሉ፣ በዚህም የሀያ ዓመት ዕድሜ ይሰጥሃል፡፡”

ዝንጀሮም አለ “ ሀያ ዓመት እንኳን ይበዛብኛል፤ አሥር ይሁንልኝ፡፡” አለ፡፡ ያለው ተደረገለት፡፡

ለሰዉም ተባለ - አንተ ከፍጥረታት ሁሉ ብልሁ ነህ፤ በሌሎች ፍጥረታት ላይ አለቃ ትደረጋለህ፤ ምድርን ታንፃለህ፣ ወኪልም ትደረጋለህ፤ ለዚህም በምድር ቆይታህ ሀያ ዓመት ዉሰድ፡፡”

ሰዉም አለ፡፡ “እንደሰው ሀያ ዓመት ያንሰኛል፤ ባይሆን ሌሎች ያልተቀበሉትና የመለሱት ዕድሜ ይሠጠኝ” አለ፡፡
በዚህም አህያ የመለሰው ሰላሳ ዓመት፣ ዉሻ የመለሰው አሥራ አምስት ዓመት፣ ዝንጀሮ የመለሰው አሥር ዓመት ተሠጠዉና  ሰባ አምስት ዓመት ሆነለት፡፡

በዚህም የተነሳ የሰው ልጅ እስኪያገባ ድረስ የመጀመርያዉን ሀያ ዓመቱን እንደራሱ ዕድሜ እንደሰው ይኖራል አሉ፤ ቀጥሎ ያለዉን ሰላሳ ዓመት እንደ አህያ ይሠራል፣ ያለዕረፍት ይለፋል፣ ይደክማል፡፡
ከዚያ ዕድሜው ከፍ ሲልና ሃምሳ ብዙ ጊዜውን እንደ ዉሻ እቤቱ ያሳልፋል፣ ጓሮ ያዘወትራል፣ ግቢዉን ይጠብቃል፣ መብራት ዉሃ ይቆጣጠራል፡፡ የቀረዉን አሥር ዓመት ደግሞ ከልጆቹ ወደ ልጆቹ እንዲሁም ወደ ልጅ ልጆቹ ቤት እየተዘዋወረ ይኖራል፡፡ ህፃናትና በድዱ ይስቃሉ፣ ወጣቶች በወጉ ይጫወታሉ፡፡

ሰው ማለት ይኸው ነው፡፡

http://t.me/MuhammedSeidABX