Get Mystery Box with random crypto!

ጥቂቶቹ እነሆ፡- የጀነት ጉጉት 1.     አሕመድ ቢን ሐርብ ፤ አላህ ይዘንለት “አንዳንዶቻች | ABX

ጥቂቶቹ እነሆ፡-

የጀነት ጉጉት

1.     አሕመድ ቢን ሐርብ ፤ አላህ ይዘንለት
“አንዳንዶቻችን፣ ከፀሐይ ሐሩር (ሽሽት) በጥላ እንከለላለን፤ ምነዋ ታድያ ከእሳት (ረመጥ ለመዳን) በጀነት የማንጠለል?!” ሲል ይጠይቃል ።

2.     ኡሙል በኒን -የዑመር ኢብን ዐብዱልዐዚዝ እህት (ረ.ዐ) 
“ከንፉግ ሁሉ ንፉግ፣ ጀነትን ለራሱ የሚነፍግ ነው።” ብላለች።

3.     የሕያ ኢብን ሙዓዝ ፤ አላህ ይዘንለት
“ስለ ነፍሴ ሕልፈት የማለቅስ አይደለሁም፤ ይልቁንም የኔ ማንባት፣ መሻቴ አይሰምር (ጉዳዬ አይሞላ) እንደሁ ከመፍራት ነው!” ብሏል።

4.     ዑመር ኢብን ዐብዱልዐዚዝ (ረ.ዐ) 
“ረጃእ ሆይ (ስማኝ)! እጅግ ገጉ የሆነች ነፍስ አለችኝ፤ (እና ይህች ነፍሴ) ፋጢመት ቢንት ዐብዱልመሊክን ተመኘች፤ አገባኋትም። ወደ ሹመትም አማተረች፤ ተሾምሁላትም። ኸሊፋነትንም ከጀለች፤ አገኘኋትም። አሁን ደግሞ ጀነትን ናፍቃለች፣ የኃያሉና የተከበረው አላህ ፍቃድ ከሆነ እንደምቀዳጃት ተስፋ አደርጋለሁ!” ብለዋል።

 
5.     ዐጧእ ኢብን መይሰራ (ረ.ዐ) 
“በምድራዊ ሕይወታችሁ ጉዳይ አልመክራችሁም፤ እናንተ በርሷ የተካናችሁና የተሰጣችሁ ናችሁና። አደራ የምላችሁስ በአኺራችሁ ጉዳይ ነው። በዚህች ጠፊ አላፊ ሀገር ሳላችሁ፥ ለዘላቂይቱ ዓለም ትጉ!” 

6.    ኢማም  ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ
“ፀጋ በምቾት) አይገኝም። ለ ጊዜያዊ ደስታ የሚሸነገልን ዘላለማዊ ደስታ ትሸሸዋለች። ብርታት የሌለው ሰው ሐሴትም የለውም፤ ትዕግስትን ያላደለው እርካታ አይኖረውም፤ መከራ የሌለው ተድላን አይቸርም፤ ፈተናን ያልታደለ እፎይታ የለውም። የአላህ ባርያስ ማለት በጊዜያዊ መከራ (ውስጥ አልፎ) ዘላቂ ሐሴትን የሚጎናፀፍ ነው!”

7.     የሕያ ኢብን ሙዓዝ (ረ.ዐ) 
“ዱንያን መዘንጋት አዳጋች ቢሆንም፣ ጀነትን ማጣት ግን ከባድ ሐዘን ነው። እናም፣ ምድራዊ ሕይወትህን ለነገይቱ ዓለም ጥሎሽ አድርጋት!”

ምንጭ ፦ አንዲት ዕለት በጀነት
ማሕሙድ አልሚስሪ
ትርጉም ፦ ዒማዱዲን ዙልፊቃር

https://t.me/NejashiPP