Get Mystery Box with random crypto!

“እሺ ካልኩት በኋላ ሸሸ ... 'እሺ ካልኩት በኋላ ሸሸ፤ እኔም ምነው እሽ ባላልኩት ብዬ እፍ | ABX

“እሺ ካልኩት በኋላ ሸሸ ...


"እሺ ካልኩት በኋላ ሸሸ፤ እኔም ምነው እሽ ባላልኩት ብዬ እፍረት ተሰማኝ፡፡”
ስትላት ሰማሁ በቀደም አንዲት ለጓደኛዋ፡፡ ቸኮልኩ መሠለኝ ... አለቻት ዐይን ዐይኗን እያየች።

እሺ ያለችው ለትዳር ነበር፡፡ ጠየቃት፤ በፊትም ታስበው ነበርና ከትንሽ ማንገራገር እሺ አለችው፡፡

ከዚያ ጠፋ፤ ሸሸ፣ ከዐይኗ ራቀ ። ምን ታድርግ? ደዉላ ምነው ጠፋህ አትለው ነገር፤ ተስማምቻለሁ እኮ ያንን ዕቃ አትወስድም ወይ አትለው ነገር …፡፡
እሱ ሲጠፋ መልሶ አሳፈራት፤ ተሸማቀቀች፤ ደበራት፣ እንደመበሳጨትም አደረጋት፡፡ የምሩን ነው ወይስ ሊፈትነኝ ነው የጠየቀኝ ብላም ራሷኝ ጠየቀች፡፡ የሰው ዉስጡ አይታወቅ ነገር፡፡

ትዳር አንዳንዴ ከንግድ ጋር ይመሳሰላል ። አንዱ ደህና ዋጋ ሰጥቶ ሲጠፋባችሁ ምን ይሰማችኋል ? ይመለስ ይሆን ብሎ በር በሩን እንደማየት። ማሰብ ፣ ተስፋ አለመቁረጥ ...

በርግጥ በወቅቱ ያኔ ትንሽ ላግደርድረው ብላም አስባ ነበር፤ ግና በዚያው ቢቀርስ ብላ ፈራች፤ ይሄ ስትናፍቀው የነበረ መልካም ጥያቄ ላይደገም ይችላል ብላ ሰጋች፡፡ መልካም አክሲዮን አይገፋም። ትዳር ሐላል አክሲዮን ። እስከ አኺራና ጀነት አብሮ የመዝለቅ እሳቤ።

እናም ተስገብግባ እሺ አለችው፡፡
ደግ አደረግሽ።
ቢሆን ባይሆን ፣ ቢመለስ ባይመለስ፣ ቢመጣ ቢቀር ...እሱ የጀሊሉ ዉሳኔ ነው። አንች ግን እንኳን ለሐላል ጓጋሽ።

ለሐላል ነገር መስገብገብ እኮ ጥፋት አይደለም፡፡ እንደዉም የሚበረታታ ነው።

እሺ ስላልሽው ምን አሳፈረሽ! ምንስ ያጠፋሽው ነገር አለ!፡፡ አዎ ምንም የተሳሳትሽው ነገር የለምና አትፈሪ፡፡

እርግጥ ነው በሰው ልብ መጫወት የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። ሰዉን እንደ ገበያ ዕቃ ያያሉ፤
ካስለፈለፉ በኋላ በዉስጣቸው በሰው የሚስቁ፣ እሺ አለችኝ ብሎ ለማስወራት የሚመጡም አሉ።

አንዳንዶች ፈሪ ናቸው። ቶሎ እሺ ስለተባሉ ብቻ ምርጫ ላይ ተሳስቼ ይሆን? ቸኩዬ ይሆን? ብለው የሚደነግጡና አሉ።
አንዳንዶች ደግሞ ለማግባት ወስነው አይመጡም፤ እሺ ከተባሉ በኋላም አጀላቸው የተቃረበ ይመስል የሚርበተበቱም አሉ፤
እሺ አልባልም ብለው አስበው ጠይቀው እሺ ሲባሉ ድራሻቸው የሚጠፋም አሉ፤
ፍላጎት ሳይኖራቸው ከአንገት በላይ ሰዉን የሚያወሩም አሉ፡፡

የሁሉን ልብ የሚያውቀው ጀሊሉ ነው። ፍርዱንም ለሱ መተው ነው ። እሱ ለያንዳንዱ የንያውን ይሠጣል ።
ቁምነገሩ ቁምነገረኛ ነው ብለው ላሰቡት ሰው ልብንና እጅን መሰጠት ነው። ለትክክለኛ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት ጥፋት አይደለም፤
ሐላልን መናፈቅ አያሳፍርም፤
ለምን ታፍሪያለሽ እሱ ከመልካም አክሲዩን የቀረው ይፈር፡፡

ተልቁ ችግራችን በምን ማፈር እንዳለብንና እንደሌለብን አለማወቃችን ነው ።

ሐላል ፍለጋ ላይ ማፈር ብሎ የለም።

http://t.me/MuhammedSeidABX