Get Mystery Box with random crypto!

قناة أبي العباد

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedbatii — قناة أبي العباد ق
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedbatii — قناة أبي العباد
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedbatii
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.53K
የሰርጥ መግለጫ

ليكن هدفنا فهم الكتاب والسنة على منهج السلف والعمل بما فيهما

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-15 06:38:29 https://vm.tiktok.com/ZMNGHLAEt/
206 viewsMuhammed Abdillah Bati, 03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 06:22:58
203 viewsMuhammed Abdillah Bati, 03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:38:53
241 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 09:26:13
262 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 20:01:12 ጠቃሚ ፈትዋ ነው አንብቡት
338 viewsMuhammed Abdillah Hussein, edited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:45:22
255 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:45:16 “ከላይ ነው ትእዛዙ!!”
~~~~~
ንፁህና ጥብቅ የሆነችን ሴት በዝሙት መወንጀል ከሰባት ከባባድ አጥፊ ወንጀሎች አንዱ እንደሆነ ነብዩ ﷺ እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል:- “ሰባት አጥፊዎችን ተጠንቀቁ!!”
ሶሐቦች: “ምንድን ናቸው እነሱ? የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” ብለው ሲጠይቁ ጊዜ እንዲህ አሉ፡-
1. በአላህ ማጋራት፣
2. ድግምት፣
3. አላህ በሐቅ (አግባብ ሆኖ ሲገኝ) ካልሆነ እንጂ እንዳትገደል እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል፣
4. ወለድ መብላት፣
5. የየቲምን ገንዘብ መብላት፣
6. (በሙስሊሞችና በከሃዲዎች መካከል) ጦርነት በሚካሄድበት ጊዜ መሸሽ፣
7. ጥብቅ የሆኑና የዘነጉ (የሚወነጀሉበትን ነገር የማያውቁ) ሴቶችን በዝሙት መወንጀል!! [ቡኻሪና ሙስሊም]
ሰባቱንም በሚገባ እናጢናቸው፡፡ ለጊዜው ግን ሰባተኛው ላይ እናነጣጥርማ፡፡ እህቶቻችንን ወንድሞቻችንን ባላዩት ባልሰሙት ባልጠረጠሩት በዝሙት የምንወነጅላቸው ስንቶቻችን ነን?!! ልብ በሉ! ዝሙት ከባድ ወንጀል መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ በከባድ ወንጀል ሰዎችን መወንጀል ደግሞ የከበደ ነው፡፡ አንዲትን ሴት ወይም አንድን ወንድ በዝሙት የወነጀለ ሰው “ፈፃሚዎቹ መርፌና ክር ሆነው ድርጊቱ በተጨባጭ ሲፈፀም አይቻለሁ” የሚሉ አራት አስተማማኝ ምስክር ሊያቀርብ የግድ ይለዋል፡፡ “ተቃቅፈው አይቻለሁ” “አንድ ላይ ነበሩ” “ሲስማት አይቻለሁ” … አይሰራም፡፡ “በአይኔ በብረቱ ዝሙቱ ሲፈፀም አይቻለሁ” የሚሉ አራት ምስክር ካልተሟላ ወንጃዮቹ እያንዳንዱ ሰማንያ ሰማንያ ጅራፍ ይጠብቃቸዋል!! ሌላም አለባቸው፡፡ ሀያሉ ጌታ እንዲህ ይላል፡-
وَالَّذِينَ يَرْمُونَ الْمُحْصَنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَأْتُوا بِأَرْبَعَةِ شُهَدَاءَ فَاجْلِدُوهُمْ ثَمَانِينَ جَلْدَةً وَلَا تَقْبَلُوا لَهُمْ شَهَادَةً أَبَدًا ۚ وَأُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ
(እነዚያም ጥብቆችን ሴቶች (በዝሙት) የሚሰድቡ ከዚያም አራትን ምስክሮች ያላመጡ፡ ሰማኒያ ግርፋትን ግረፏቸው፡፡ ከነርሱም ምስክርነትን ሁልጊዜ አትቀበሉ! እነዚያም እነሱ አመፀኞች ናቸው።) [ኑር፡ 3]
እስኪ ለአፍታ እንቁምና ወደ ኋላ እንመልከት፡፡ ስንቱን በዝሙት ወንጅለናል፡፡ የስንቱን ክብር አጉድፈናል? ጌታዬ ሆይ! ያለፈውን ይቅር በለን፡፡ በቀሪው ህይወታችንም ጠብቀን!!
ይህ በንዲህ እንዳለ … ዛሬ ቀኑ ዓሹራ ነው። አላህ ሙሳ ዐለይሂ ሰላምን ከፊርዐውን መንጋጋ ነፃ ያወጣበት ቀን። እኛ ሙስሊሞች ይህን ቀን በሱናው መሰረት በፆም እናሳልፈዋለን። ሺዓዎችስ? ከስር ያለውን ምስል ተመልከቱ፡፡ በዚህ መልኩ ነው የሚያሳልፉት፡፡ “ምነው? ጤናም አይደሉ?” ካላችሁ መልሱ አጭር ነው፡፡ “ከላይ ነው ትእዛዙ!”
ዓኢሻህ የምንኮራባት እናታችን ናት!! ጌታችን "ሚስቶቹም (ለአማኞቹ) እናቶቻቸው ናቸው!" ይላል፡፡ [አሕዛብ፡ 6] ይሄ የጌታችን ችሮታ ነው፡፡
ሺዓዎች የነቢዩን ﷺ ባለቤት እናታችን ዓኢሻን በዝሙት ይወነጅሏታል። ዝሙተኛ ናት ብለው ስለሚያምኑ እናትነቷን ክደዋል። ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ አንድ ጊዜ የሆነ ሰው ይመጣና “አንዳንድ ሰዎች እናታችን አይደለሽም እያሉ ነው” ይላታል፡፡ አንበሳዋ ምን ብትል ጥሩ ነው? “እውነት ተናግረዋል! እኔ የአማኞች እንጂ የመናፍቃን እናት አይደለሁም!!” ልክ ብለሻል የኔ እናት!! ልክ ብለሻል የኔ ጀግና!! የማን ሚስት ነሽና! የማን ልጅ ነሽና!
ዓኢሻዬ የኔ እናት
ጀግና የጀግና ልጅ ናት …. ባለ ብሩህ ህሊና
በሐያእ በሱና የታነፀች …. ገና እድሜዋ ሳይጠና
ቆንጆ የቆንጆዎች አለቃ
አስተዋይ ህሊናዋ የነቃ
አንደበተ ርቱእ ናት …. ምላሷ ማር የሚተፋ
እሷን እናቴ ያረገ …. ሀያል ጌታዬ ክብሩ ይስፋ!

መና - ፍቃን በክፉ ቢወነጅሏት ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታ ከሰማያት በላይ ሆኖ ንፁህ መሆኗን ዘላለም የሚቀራ አንቀፅ አወረደ፡፡ ግና ዛሬም እነዚያን መና - ፍቃን ተምሳሌት ያደረጉ ቂሎች ከጥፋታቸው ሊመለሱ ፈቃደኞች አልሆኑም፡፡ “ጂልና ወረቀት የያዘውን አይለቅም” ነው ነገሩ፡፡ ውስጥ አዋቂው ጌታ ንፁህነቷን ቢያውጅም ሰማያዊውን አዋጅ “አሻፈረን” እንዳሉ ናቸው፡፡ እነሱም ቆሻሻዎቹ ራፊ - ዷዎች (ሺዐ - ዎች) ናቸው፡፡ አዎ ቆሻ - ሻ ናቸው!! ለዚያም ነው እነሱን አብጠርጥረው የሚያውቋቸው ከቀደምት አበው አንዱ የሆኑት ዓሚር አሸዕቢይ ረሒመሁላህ (104 ሂ.) “እንስሳ ቢሆኑ ኖሮ አህ- ዮች ነበር የሚሆኑት!! የወፍ ዘር ቢሆኑ ጥንብ አንሳ ነበር የሚሆኑት” በማለት በሚሰቀጥጥ መልኩ የገለጿቸው፡፡ [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 4/472]

እናም እነዚህ ቆሻ - ሻዎች ዛሬም ድረስ ምላሳቸውን ሊሰበስቡ አልፈቀዱም፡፡ ዛሬም ድረስ እናታችንን በዝሙት እየወነጀሏት ነው፡፡ ዛሬም ድረስ በነብዩ ﷺ ክብር ላይ እየተረማመዱ ነው፡፡ ጠቢቡ ጌታ ግን ድንቅ ፍርዱን በነሱ ላይ እያሳየን ነው፡፡ "አላህ ከነዚያ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል” አይደል ያለው? [ሐጅ፡ 38] ከላይ ባሳለፍነው የቁርኣን አንቀፅ መሰረት ንፁሃንን በዝሙት የሚወነጅል 80 ጂራፍ ይገረፋል፡፡ ይሄው ሺዐ - ዎች በያመቱ ሙሐረም 10 ላይ እራሳቸውን በስለት እንዲገርፉ የአላህ ውሳኔ ሆኗል፡፡ የሰው ልጅ ህሊናው እያለ ያደርገዋል ተብሎ በማይታሰብ መልኩ እራሳቸውን በደም እያጨቀዩ እራሳቸውን እየገረፉ እራሳቸው እንዲያለቅሱ ወሰነባቸው፡፡ ታዲያ (አላህ ከፈራጆች ሁሉ የበለጠ ፈራጅ አይደለምን?!) [ቲን፡ 8] እንዴታ!! (እርግጠኛ ሆነው ለሚያምኑ ሰዎች ከአላህ ይበልጥ ፍርዱ ያማረ ማን ነው?!!) [ማኢዳህ፡ 50]
ምን ይሄ ብቻ!! እሷን በዝሙት ሲወነጅሉ እራሳቸው በዝሙት መጨማለቅ መታወቂያቸው ሆነ እንጂ!! “ምን ማስረጃ አለህ? ይሄስ ዞሮ በዝሙት መወንጀል አይደለም ወይ?” የሚል ይኖር ይሆናል፡፡ አንድ ሰው እራሱ ካመነ ምስክር አያስፈልግም፡፡ “አልኢዕቲራፉ ሰይዪዱል አዲላህ!” ይባላል፡፡ “በራስ ላይ መመስከር (ማመን) የማስረጃዎች ሁሉ ቁንጮ ነው” እንደማለት ነው፡፡ እናም እራሳቸው ሺዐዎቹ የኮንትራት ወይም “የሙትዐ ጋብቻ” ከመፈፀምም በላይ “ይህን ያልተቀበለ ከኛ አይደለም” ብለው ዝሙትን ከመፈፀምም በላይ ዲን አድርገውት አረፉ፡፡ [ወሳኢሉ ሺዐህ፡ 4/438] ሌሎችም ብዙ ኪታቦቻቸውን መዘርዘር ይቻላል፡፡ አዑዙ ቢላህ!! እነዚህ ናቸው እንግዲህ ዓኢሻን በዝሙት የሚወነጅሉት!!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 13/2008)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
206 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 13:44:04
267 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 10:18:11
265 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 10:15:12
438 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ