Get Mystery Box with random crypto!

قناة أبي العباد

የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedbatii — قناة أبي العباد ق
የቴሌግራም ቻናል አርማ muhammedbatii — قناة أبي العباد
የሰርጥ አድራሻ: @muhammedbatii
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.53K
የሰርጥ መግለጫ

ليكن هدفنا فهم الكتاب والسنة على منهج السلف والعمل بما فيهما

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 09:58:05 የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-

* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።

3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-

* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
38 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 06:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:14:55 https://t.me/Muhammedbatiii
22 viewsMuhammed Abdillah Bati, 20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 23:13:34 ጥቂት ነጥቦች ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ
~
1.  ወገኔ ሆይ! አገርህን አትልቀቅ።

ባለፈው ተፈናቃዮች ላይ የደረሰውን አስታውስ። ደብረ ብርሃንና ባህርዳር ለተፈናቃዮች ከማጎሪያ ካምፕ የማይለዩ እንደነበሩ ሲወራ ነበር። አሁን ደግሞ ነገሮች ከቀድሞው ቢብሱ እንጂ የተሻሉ አይደሉም። ፖለቲከኛውን ተወው። ህዝብ እራሱ ኑሮ ስለከበደው ሊጨካከን፣ ሊሰላች ይችላል። ሩቅ አትሂድ። ደሴ ወልዲያን፣ ወልዲያ ቆቦን ሊሰለች ይችላል። የጎደለበት ደግሞ በትንሽ በትልቁ ይከፋዋል። ስለዚህ በተለየ እፈለጋለሁ ብሎ የሚሰጋ ካልሆነ በስተቀር ጦርነቱ ቀጥታ ከሚካሄድባቸው ቀጠናዎች ለጊዜው ዞር ከማለት ውጭ ካገር ርቆ መሄድ ስቃዩን የከፋ ያደርገዋል።

2.  ወገኔ ሆይ! ንብረትህን ጠብቅ።

ሩቅ ብቻ አትመልከት። እዚያው በዙሪያህ ለዘረፋ ተደራጅተው ከግለሰብ ንብረት እስከ ተቋም ሲዘርፉ የነበሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ዛሬም ይኖራሉ። ፍሪጅና ቴሌቪዥን ሳይቀር በግመል እየጫኑ የወሰዱ የገጠር ሰዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ። “መብራት የላችሁ ምን ያደርግላችኋል?” ሲባሉ “እንሸጠዋለን” ሲሉ ነበር። ስለዚህ ቅድሚያ ለህይወት ጥንቃቄ ካደረግክ በኋላ በቅርብህ ሆነህ በተቻለህ መጠን ንብረትህን ተደራጅተህ ጠብቅ።

3.  ወገኔ ሆይ! ለፈተና እራስህን አዘጋጅ!

ወደድንም ጠላንም ፈተና ላይ ነው ያለነው። መጠኑ ከህዝብ ህዝብ በእጅጉ እንደሚለያይ ግልፅ ነው። ፈተናው ምን ያህል እንደሚዘልቅም አናውቅም። የሆነች ያክል የምንዘጋጅባት ሰበብ ካለችን ባለችን መጠን ለሚመጣው ሁሉ ራሳችንን እናዘጋጅ። ምግቡ፣ ወፍጮው፣ ባንኩ፣ መብራቱ፣ ቴሌው፣ መድሃኒቱ፣ ... ብዙ ነገር ይቸግራል። እስካሁንም ብዙ የተፈተነ አለ። ልዩነቱ ብዙ ባይሆን እንኳ የተዘጋጁበትና የተዘናጉበት ፈተና አንድ አይደለም። አላህ ለሁሉም ፈረጃውን ያቅርብልን።

4.  ወገኔ ሆይ! ጊዜ አይተህ አትለወጥ!

ለሚያልፍ ቀን ትዝብት ላይ አትውደቅ። የትኛውም ቡድን አጠቃኝ በሚል ማመሃኛ ማንንም ብሄር ለይተህ እንዳታጠቃ። የአማራ ህዝብ ሆይ! ህወሓትን መነሻ አድርገህ ለፍቶ አዳሪ ትግሬን አታጥቃ። “ያው ናቸው” ከሚል ስሜት ወለድ ሂሳብ ራቅ። “ህወኃት እከሌን አካባቢ የተቆጣጠረው ተፈናቃይ ትግሬዎችን ተጠቅሞ ነው” እየተባለ የሚናፈሰው ብታምንም ባታምንም ከንቱ ውሸት ነው። እንዲህ አይነት አሉባልታ ይዘህ ደካሞችን እንዳትጎዳ።
ትግሬው ሆይ! ህወኃት ሲገባ ጠብቀህ አደባባይ ለጭፈራ አትውጣ። ጠቋሚ፣ አፋኝ፣ አሳፋኝ ለመሆን አትሞክር። ሃይማኖት ወይም ሞራል እንኳ ባይገታህ ቢያንስ ለራስህ ፍራ! ነገሮች የተቀያየሩ እለት መግቢያ ታጣለህ። በባለፈው ግጭት አማራውም፣ ትግሬውም፣ ኦሮሞውም፣ አፋሩም ዘንድ ብዙ ደስ የማይሉ ነገሮች ሲወሩ ነበርና አላህን ልንፈራ ይገባል።

5.  ወገኔ ሆይ! ለመጣ ለሄደው አታጨብጭብ።

አንድ ኃይል አንድን አካባቢ ሲቆጣጠር ሆ ብሎ መውጣት፤ ሌላው በግሩ ሲተካ አሁንም ሆ ብሎ መነሳት ይሄ ግልብነት ነው። የሃገራችን ፖለቲካ ቂመኛና ተበቃይ ነው። እንኳን የገባበትን፣ የሌለበትንም ጊዜ ተጠግቶ ያጠቃል። ደግሞም በጣም ተገለባባጭ ነው። እዚች አገር ውስጥ ስንት አይሆንም የተባለ ነገር ሆኗል! መንግስት ትግራይን ሲቆጣጠር ህወኃት ዳግም ያንሰራራል ብሎ የገመተ አልነበረም። ህወኃት ሰሜን ሸዋ ከደረሰ በኋላ በዚያ አሰቃቂ ሁኔታ ይመለሳል ብሎ የገመተም አልነበረም። ስለሆነም ጥንቁቅ መሆን ያስፈልጋል። በሁለቱም አይንህ ዛሬ ላይ ብቻ አታፍጥጥ። በአንድ አይንህ ነገን ተመልከት።

6.  ወገኔ ሆይ! ህይወት አትርፍ።

አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የሚጠሉትን ለማጥቃት የማያመነቱ እርኩስ ፍጡሮች ይኖራሉና ቢቻልህ ያለ ጥፋታቸው የበደለኞች ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉ ወገኖችን አትርፍ። ከጎናቸው ቁም። በባለፈው ግጭት ህወኃት ሲገባ ጠብቀው ደካሞችን ያጠቁ ሰዎች አሉ። ከነሱ አንፃር ሲታይ ህወኃት በጣም የተሻለ ነበር። መረጃ ያለው ሰው የምለው ይገባዋል። ህወኃት ከወጣ በኋላም እንዲሁ ከየትኛውም ኃይል ጋር ምንም አይነት ንክኪ የሌላቸው ምስኪኖች ተጎድተዋል። ከተቻለን ጊዜ አይተው ከሚያጠቁ ነውረኞች አንድ ነፍስ እንኳ ብናተርፍ ዋጋው የትና የት ነው!! በቅርቡ ኦሮሚያ ውስጥ በነበረውን ግጭት የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ኦሮሞዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። አማራ ውስጥ የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው ትግሬዎችን ያተረፉ ስንት አማራዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። የራሳቸውን ህይወት አደጋ ላይ ጥለው አማራዎችን ያተረፉ ስንት ትግሬዎች አሉ። ግን አላወራንላቸውም። ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት!

7.  ወገኔ ሆይ! ወቅታዊ ግጭቶችንና ተያያዥ ጉዳዮችን ከሃይማኖት ጋር እንዳታጠላልፍ።

የየትኛውም ቡድን ደጋፊ ልትሆን ትችላለህ። የኔ የምትለው ወገን ከሌሎች በተለየ እንደተገፋ ሊሰማህ ይችላል። ግን እወቅ! ሌሎችም መሰል ህመም አላቸው። ቢቻል በፖለቲካውም ሞራል ግብረ ገብነት ቢኖርህ እሰየው። ያለበለዚያ ግን የሃይማኖት ተቋማትም፣ አስተማሪዎች እና የደዕዋ መድረኮችም አንተ በምትፈልገው መልክና መጠን እንዲያወሩ፣ የፖለቲካ ፍጭቶች ማራገፊያ እንዲሆኑ አትፈልግ። ማህበራዊ ሚዲያዎችም ላይ ሆነ መሬት ላይ እየተከተልክ በአክቲቪስት ቋንቋ እንዲያወሩ አጉል አትወትውት። ልትረዳ ቢያቅትህ ቢያንስ አደብ ይኑርህ። ከፖለቲከኛ ጋር የለመድከውን እሰጥ አገባ በየደረስክበት አትድፋ።

8. የሃይማኖት አስተማሪ ሆይ! ከመንጋው ተለይ!

ብሄርህን ተከትለህ ቅስቀሳ ውስጥ አትግባ። ሌላው አካል ለጦር ቢቀሰቅስ አንድ ሁለት ነገር ተመልክቶ ነው። አንተ ተጨማሪ አርቀህ የምትመለከትበት አላህን መፍራቱ ሊኖርህ ይገባል። ያለበለዚያ በምንህ ነው ከሌሎች የምትለየው? ኢን ሻአላህ ነገ ሰላም ይመጣል። እሱን ታሳቢ አድርግ። መንጋው ሊያግባባህ፣ ሊገፋፋህ፣ አልሆን ሲለው ሊያወግዝህ ይችላል። የፈለገውን ይበል እሱ በቀደደው አትፍሰስ። የሃይማኖት አስተማሪ ሆነው በቀጥታ የግጭት ተሳታፊ፣ ወይም ቀስቃሽ፣ ወይም ደጋፊ፣ ወይም የዘር ጥላቻ ጠማቂ የሆኑ መርዘኛ ሰባኪዎች ሁሉም ብሄር ጋር አሉ። እነዚህ አካላት ነገ ችግሩ ቢያልፍ እንኳ የማያልፍ ጠባሳ እየጣሉ ነው። ጦሳቸውም ከራሳቸው አልፎ ለህዝብ ይተርፋል። ከሃይማኖትህ ተማር። እስካሁን ካለፈው ተማር። ከሌሎች ድክመት ተማር። የትኛውንም ውሳኔ ብትመርጥ ከትችት ላታመልጥ ነገር የሰው ስሜት ተከትለህ እንዳትወስን። አላህን አስብ።
በመጨረሻም አደራ የምለው እንተዛዘን፣ እንተሳሰብ፣ ዱዓእ እናድርግ፣ ወደ ጌታችን እንመለስ። አላህ ከገባንበት መከራ አውጥቶ የሰላም አየር የምንተነፍስ ያድርገን። ኣሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
16 viewsMuhammed Abdillah Bati, 20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 17:11:29
ታላቅ የሙሀደራ ድግስ ለወንድም እና እህቶች.

እንኳን ሊቀሩበት ሊያረፍዱበት የማይገባ
የተውሂድ አሳሳቢነት
በኡስታዝ አቡል አባስ ናስር حفظه الله

ወጣትነት እና ጊዜ አጠቃቀም
በወንድም አብዱረዛቅ ባጂ حفظه الله

እንዲሁም ሌሎች ድንቅ ፕሮግራሞች አዘጋጅተን አንጠብቃችኋለን.


ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

  እሁድ ነሀሴ22፣2014

ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ
ቀጠሮአችን  አል ኢኽላስ መድረሳ ይሁን።

አድራሻ: ቦሌ ሚካኤል ድልድይ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ
       ለወንዶች 0921617782
                     0911933929
                      0954973802

          ለሴቶች 0901034787
                      0942407049
                       0901033401
መልእክቱን ለወንድም እህቶች በማድረስ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን!

አዘጋጅ ኡሙ አይመን ጀመአ
https://t.me/+-_b3P_EV7AJkMjY8
120 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:48:22 የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

ውድ ሙስሊም  ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ።

የሱና ወንድማችን አብዱ ሰይድ ይባላል። በልጅነቱ በሆነ አጋጣሚ በተፈጠረ አደጋ አንድ አይኑን አጥቶ ሲኖር የነበረና በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን አግብቶ ሁለት ልጆችን ወልዷል።አላህ አግርቶሎት በቀረችው በአንድ አይኑ #ቁረአንም_ሀፍዟል  እስካሁን በቆየበትም ጊዜ ለሱና ባለው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ከቤተሰቦቹ ተገሎና ርቆ ምንም እገዛ እንኳን የማያደርጉለትና ዘወር ብለው የማያዩት ሲሆን ስራም ትንሽም ቢሆን የቀን ስራ እየሰራ ቤተሰቦችን ያስተዳድር ነበር ። አሁን ግን መስጊድ ቁጭ ብሎ ቁረአን ሲቀራ ነው የሚውለው ።

ሆኖም አሁን ደግሞ የአሏህ ውሳኔ ሆነና በሚኖርበት ግቢ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ምክንያት እሳቱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የኤሌክትሪክ መብራት ይዞት ጭንቅላቱን ክፉኛ የተመታ ሲሆን ይህ አደጋም የቀረችው አንድኛው አይኑ ላይም ተፅእኖ በመፍጠሩ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥርበት ዶክተሮችም በፍጥነት አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ህክምና ካልወሰድክ የአይንህ ነርቭ በመነካቱ ሁለተኛውንም አይንህን ልታጣው ትችላለህ ብለውታል።

ስለዚህ ይህ የሱና ወንድማችን የቀረችውን አንድ አይኑን ለማትረፍ  ህክምናውን ለመጀመር በትንሹ 70,000ሺ ብር( ሰባ ሺ ብር) እንደሚያስፈልገው በዶክተሮች ተነግሮታል ።ይሄንን ብር ደግሞ አይደለም በአንድ ጊዜ በአንድ አመትም ማገኘት ስለማይችል የኛ የወንድምና የእህቶቹ እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል

ያ አሏህ... ተመልኩቱ አንዷንም የተረፈችዋንም አይኑን ሊያጣት ነው ሲደመር ችግር ፣ ድህነት ፣ ልጆች ማሳደግ ፣ ስራ ማጣት ፣ ከቤተሰብ መገለል እያሰቃየው ነው።

እኛ ደግሞ ሁለቱም አይኖች አሉን። #አልሀምዱሊላህ ፣ አሏህም በቁረአኑ እንዲህ ብሎናል  (أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ) "ለእርሱ(ለሰው ልጅ) ሁለት አይኖችን አላደረግንለትምን?"( ሱረቱል በለድ ፣ 8) ይላል። ታዲያ አሏህ እንዲህ አይነት ፀጋ ሲውልልን ምስጋናችን ከምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እንዲህ በአይናቸው የተፈተኑ ሰዎችን በማገዝና በመርዳት አሏህ የኛንም አይኖች እንዲጠብቅልን ዱዓ በማድረግ ነው።

ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣  ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን  የአቅማቹህን እንድታበረክቱ  ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች  የእርዳታ ጥሪያችንን   እናስተላልፋለን።

በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት።

ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ  የባንክ አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ
       #1000034096008    
#የአካውንቱ ስም :- አብዱ ሰይድ መሀመድ

ለበለጠ መረጃ የወንድማችን ስልክ
ስልክ:     #0914324157

"በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ  ﷺ ነግረውናል ።

ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንዲታደርጉልን ።
280 viewsMuhammed Abdillah Bati, 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:01:08 #طرفة

مرَّ سفيهان برجلٍ مهذَّبٍ فأرادا أن يسخرا منه؛ فوقف أحدهما عن يمينه والآخر عن يساره وسألاه:

«أمغفَّلٌ أنت أم أحمق؟» فقال لهما : «أنا بين الاثنين».

[«الكنَّاش المفيد» لأحمد العسَّاف (١٦)]
198 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 06:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 00:30:39 كلام الأقران في بعضهم يُطوى ولا يُروى (٢/ ٢)

قال الذهبي:

«كلام الأقران بعضِهم في بعضٍ لا يعبأ به لا سيما إذا لاح لك أنه لعداوة أو لمذهب أو لحسد وما ينجو منه إلَّا من عصم الله، وما علمت أنَّ عصرًا من الأعصار سَلِمَ أهلُهُ من ذلك سِوَى الأنبياءِ والصدِّيقين ولو شئتُ لسَرَدْتُ من ذلك كراريس ، اللهم فلا تجعل في قلوبنا غلا للذين آمنوا ربنا إنك رؤوف رحيم».

[«ميزان الاعتدال» للذهبي (١/ ١١١)]
193 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 21:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 15:42:06 1 . አል ቀዋዒዱል ሙስላ
https://t.me/Muhammedsiragecom/7

2 . መሳኢል ጃሂሊያ 1 እስከ 20
https://t.me/Muhammedsiragecom/17

3 . ዓቂደቱ ተውሂድ 1 እስከ 70
https://t.me/Muhammedsiragecom/38

4 . አቂደቱል ዋሲጢያ 1 እስከ 26
https://t.me/Muhammedsiragecom/109

5 . ኡምደቱል አህካም 1__ 31
https://t.me/Muhammedsiragecom/136

6 . ኩን ሰለፍየን አለል ጃዳ
https://t.me/Muhammedsiragecom/168

7 . ሶስቱ መሰረቶች ( الأصول الثلاثة )
https://t.me/Muhammedsiragecom/201

8 . ሚን ኡሱሊ አቂደቲል አህሉል ሱና ወልጀማዓ
https://t.me/Muhammedsiragecom/215

9 . እስልምናን የሚያፈርሱ (نواقض الإسلام )
https://t.me/Muhammedsiragecom/222

10 . ከሽፉ ሹበሃት كشف الشبهات
https://t.me/Muhammedsiragecom/228

11 . ነዋቂዱ አልኢስላም
https://t.me/Muhammedsiragecom/241

12 . ሙቀዲመቱል አጅሩምያ
https://t.me/Muhammedsiragecom/249

13 . ኪታቡ ሲያም ) ( كتاب الصيام)
ዑምደቱል አህካም عمدة الأحكام
https://t.me/Muhammedsiragecom/273

14 መሳኢሉል ጃሂሊያ ከክፍል 1____17
https://t.me/Muhammedsiragecom/295

የድምፅ ፋይሎችን ለማግኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሸር ያርጉት
ባረከላሁ ፊኩም
t.me/Muhammedsiragecom
t.me/Muhammedsiragecom
t.me/Muhammedsiragecom
216 viewsزبيبة بنت بشير, 12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 18:18:26 https://vm.tiktok.com/ZMNGtrqut/
224 viewsMuhammed Abdillah Bati, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 14:20:11
من سبح الله في دبر كل صلاة ثلاثا وثلاثين وحمد الله ثلاثا وثلاثين وكبر الله ثلاثا وثلاثين فتلك تسعة وتسعون قا تمام المئة لا إلٰه إلا الله وحده لا شريك له له الملك وله الحمد وهو على كل شيئ قدير ، غفرت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر.
226 viewsMuhammed Abdillah Hussein, 11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ