በዚህ አመት ሐጅ ማድረግ ያልቻላችሁ ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
«√ ዐረፋህ ተራራ ላይ የመቆም እድል ያላገኘ፣ በሚያውቀው የአምላኩ ወሰን ላይ ታቅቦ ይቁም።
√ በሙዝደሊፋም ማደር ያልቻለ ሰው እሱ ዘንድ ይቃረብበት ዘንድ ለአምላኩ ታዛዥ ሆኖ ይደር።
√ ስጦታንም በሚና ማረድ ያልቻለው ሰው ለአምላኩ ሲል ፍላጎቱን ይረድ (ዝንባሌውን ይቃረን)።
√ ወደ ቤቱ (ከዕባህ) ድረስ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለም ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ዘንድ ይከጅል።»
[ኢብኑ ረጀብ: ለጣኢፉ-ል-መዓረፍ: ገፅ 633]