2022-08-24 09:47:50
በአንድ የፅጌሬዳ እሾህ ስለተቧጨርክ ጽጌረዳ አበባዎችን ሁሉ ትጠላ ይሆን?
በእርግጥ አስቸጋሪ ጊዜዎች በግንኙነቶች መሃል መጠራጠር ሲፈጥሩ ጫን ሲልም ደግሞ ለመቃቃርና ለመለያየት ምክናያት ሲሆኑ አስተውለን ይሆናል።
ሆኖም በትንንሽ መሰናከሎች እየተደነቃቀፍክ "በእናቴ መቀነት ጠለፈኝ" ስበብ ከተዳከምክ ለዓላማህ ያለህ ፅናት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል ማለት ይቻላል።
ከህልሞችህ መሃል አንዱ ስላልተሳካ ሁሉንም መተው የለብህም፣ በጥረተህ ውስጥ አንደኛው ሙከራህ ስላልተሳካ ሁሉንም እርግፍ አድርገህ ትተዋለህ ማለት አይደለም።
በሌላ መንገድ አንድ ሰው ስለከዳህ ሁሉንም ጓደኞችህን መጠራጠር ተገቢ አይደለም፣ ወይም ፍቅርህን የገለፅክላት እንዴት ኮረዳ አንተን ስላልወደደች ብቻ አፍቃሪ ሴት ፍፁም እንደሌለ ድምዳሜ ላይ መድረስ ልክ አይደለም።
ይህን አትዘንጋ በእያንዳንዱ ዝቅታ ውስጥ ከፍ የማለት እድል አለ፣ ለእያንዳንዱ ጫፍም ሁሌም አዲስ ጅማሬ አለ.......ሁሌም ሌላ ዕድል፣ ሌላ ጓደኛ፣ ሌላ አፍቃሪ፣ አዲስ ጥንካሬ ይኖራል።
ስለዚህ መስተጋብሩ በጠነከረ ፍቅር ከፀና፣ አንዳቸው ለሌላኛው እውነተኛፍቅር ካላቸው ከአውሎ ነፋሱም፣ከመዕበሉና ከወጀቡም በኋላ ግንኙነቱን ጠንካራ ማድረግ ይቻላል።
እናም ከትዳር አጋራችን፣ ከፍቅር አጋራችን፣ ከቤተሰቦቻችን፣ ከስራ ባልደረባችን፣ ከጓደኛችን ወይም ከሌሎች የምንወዳቸው ሰዎች ጋር ፈታኝ ጊዜ ሲያጋጥመን እርስ በርስ ለመደጋገፍ መተማመንን መፍጠር ይገባናል።
በመተማመን ፀንተን በጋራ ማዕበሉን ካለፍን በኋላ ደግሞ፣ አብሮ የመሆንን ጥንካሬ እናጎለብታለን።
ይህ ደግሞ የበለጠ እንድንቀራረብ ያደርገናል።
ምክናያቱ ደግሞ ፈተኙ ጊዜ መቀራረባችንን አጠነክሮታልና ነው።
በፈተና ጊዜ ፅና!
- ሣሙኤል ተክለየሱስ
281 viewsSami, edited 06:47