Get Mystery Box with random crypto!

ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች የሽያጭ ታክስ/ Turn over ta | M.O.R East Addis Ababa Branch

ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች

የሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክስ አይነቶች የሚመደብ የታክስ አይነት ሲሆን ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገቡ ግብር ከፋዮች በአገር ውስጥ በሚከናውኑት ግብይት ወይም አገልግሎት ነጻ ከተደረጉት በስተቀር የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል የታክስ አይነት ነው፡፡

ከሽያጭ ታክስ/ Turn over tax/ ክፍያ ነፃ ግብይቶች፡-

• ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ የመኖርያ ቤት ሽያጭ እና የመኖርያ ቤት ኪራይ
• የፋይናንስ አገልግሎቶች
• ለሳንቲሞችና መዳልያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጭ አገር ገንዘቦች እና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት
• በሃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች
• የሕክምና አገልግሎቶች እና አግባብ ባለው የመንግስት መሥርያ ቤት በሚወጣ መመርያ መሠረት ነፃ የተደረጉ አገልግሎቶች
• በትምህርት ተቁዋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋእለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች
• ለሰብአዊ ዕርዳታ የሚውሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች፣ የኤሌክትሪክ፤የኬሮሲን እና የውሃ አቅርቦት፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
• ማንኛውም የስራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚስጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚሰጥ ክፍያ
• ከ60% በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞች የሆኑበት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች
• መፃሕፍት( ወደ ሀገር የሚገቡ፣ በሀገር ውስጥ የሚሸጡ እና መጻህፍትን ወቅታዊ ለማድረግ የሚወጡ እትሞች )
• የምግብ እህል (ጤፍ፤ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ዘንጋዳ ፣ዳጉሳ ፣ አጃ፣ እንዲሁም የነዚህ ዱቄት ከጥራጥሬ አተር ፣ባቄላ፣ምስር ፣አኩሪ አተር፣ሽንብራ ፣ግብጦ ፣ጓያ )
• የቅባት እህሎችም ሆኑ ፕሮሰስ የተደረጉ ምግቦች፣ ፉርሽካም ጭምር የታክስ መነሳት አይመለከታቸውም ፡፡