Get Mystery Box with random crypto!

በህንድ ሀገር ማኅበረ ቅዱሳን ያስተማራቸው የማርዋዲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ። በማኅበረ ቅዱ | ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

በህንድ ሀገር ማኅበረ ቅዱሳን ያስተማራቸው የማርዋዲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተመረቁ።

በማኅበረ ቅዱሳን ሩቅ ምሥራቅ ማእከል አስተባባሪነት ላለፉት አራት ዓመታት ተከታታይ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲማሩ የነበሩ አሥራ ዘጠኝ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ/ም ተመረቁ።

በዚህ የተማሪዎች ምርቃት መርሐ ግብር ላይ የግቢ ጉባኤው አባላትና ተመራቂ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ጸሐፊ እና የግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ክፍል አባላት መርሐ ግብሩን በዙም (Zoom) ተከታትለዋል።

የሩቅ ምሥራቅ ማእከል የተተኪ ትዉልድ እና ግቢ ጉባኤ ማስተባበሪያ ክፍል ተጠሪ ዶ/ር ሲራክ ተከተል ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልእክታቸውም "ተመርቃችሁ ከወጣችሁ በኋላ በየአካባቢያችሁ በሚገኙ ማእከላት ሥር በመታቀፍ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የድርሻችሁን እንድትወጡ ማኅበራችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ያሳስባችኋል" ብለዋል። በተጨማሪም ለግቢ ጉባኤዉ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ መምህራንና አስተባባሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

በዕለቱም በዲ/ን ፋንታሁን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል ጸሐፊ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። ተመራቂዎችመ‍እ መዝሙር ያቀረቡ ሲሆን ለተመራቂዎች የመስቀል ስጦታ በግቢ ግባኤው ሰብሳቢ መምህር ዋሲሁን አገሩ አማካኝነት ተበርክቷል።

በተመሳሳይ በህንድ ሀገር በኬአይአይቲ (KIIT) ግቢ ጉባኤ ስር ሆነዉ ላለፉት 3 ተካታታይ ዓመታት ሲማሩ የነበሩ 5 የግቢ ጉባኤዉ አባላት ተመርቀዋል።

ዘገባውን የማኅበረ ቅዱሳን ሩቅ ምሥራቅ ማእከል ሚዲያ ክፍል አድርሶናል።