Get Mystery Box with random crypto!

ከጌዲኦ፣ ቡርጂ እና አማሮ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ሠልጣኞ የተተኪ መምህራን ሥልጠና ጀመሩ። | ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

ከጌዲኦ፣ ቡርጂ እና አማሮ ዞኖች ሀገረ ስብከት የተወጣጡ ሠልጣኞ የተተኪ መምህራን ሥልጠና ጀመሩ።

ማኅበረ ቅዱሳን ከደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ጋር በመተባበር ከጌዲኢ ዞን ቡርጂ እና አማሮ ሀገረ ስብከት ሠልጣኞችን በመልመል የተተኪ መምህራን ሥልጠና አስጀምሯል።

መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም  የሥልጠናውን ማስጀመሪያ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐ ግብር በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽተከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት ዲ/ን ኃይሌ አርአያ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።

ም/ኃላፊው በንግግራቸው ሠልጣኞች በቆይታቸው የተዘጋጁላቸውን የሥልጠና ዓይነቶች በትጋት መውሰድ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል። በተጨማሪም የፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ም/ሊቀ መንበር የሆኑት ቀሲስ ታደሰ እንደገለጹት ሠልጣኞች ተገቢውን ዕውቀት ይዘው እንዲሄዱ በሰ/ት/ቤቱ በኩል አስፈላጊው ዝግጅት በሙሉ እንደተጠናቀቀ ገልጸዋል።

ሠልጣኞቹ በቆይታቸው  የተለያዩ የሥልጠና ርእሶች እና የውይይት ሐሳቦች እንደሚዳሰሱላቸው ለማወቅ ተችሏል