Get Mystery Box with random crypto!

አርምሞ ግማሹን ዘመናቸውን ክፉም ሆነ ደግ ከአንደበታቸው ሳይሰማ፣ ስለደረሰባቸው መገፋትም ይሁን | ምጥን ቅመም (Mitin Kimem)

አርምሞ

ግማሹን ዘመናቸውን ክፉም ሆነ ደግ ከአንደበታቸው ሳይሰማ፣ ስለደረሰባቸው መገፋትም ይሁን ስደት ማንንም ሳይወቅሱ እና ሳይከሱ፣ ዘመናቸውን በጽሙና፣ በጸሎት እና በአርምሞ (በዝምታ) ሆነው ነው የፈጸሙት።

በትምህርተ ክርስትና ዝምታ (አርምሞ) አንዱ የመንፈስ ልእልና (የቅድስና) መገለጫ ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ጸጋ በቅዱስ መጽሐፍ ስማቸው ከሚጠቀሱ ቅዱሳን አንዷ በመሆን ትታወቃለች። ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ “ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።” ሲል ገልጦታል። (ሉቃስ 2፥19)

ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለበደሉ በፍርድ አደባባይ ቆሞ በሚከሱት፣ በሚወቅሱት ፊት በዙሪያው የነበሩት ሁሉ እስኪደነቁ ድረስ ዝም ማለቱ ተጽፏል። "ሊቀካህናቱም እነዚህ ለሚመሰክሩብህ አንድ ስንኳ አትመልስምን? አለው። ኢየሱስ ግን ዝም አለ፦ (ማቴ 26፥63)

መናገር እየቻሉ፣ ለከሰሳ እና ለወቀሳ መልስ መስጠት እየቻሉ፣ ማስረጃ እና መረጃ አቅርቦ ማሳጣት እየቻሉ፣ ሌላው የተሰወረበትን ገላልጠው እያወቁ ... ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አውቀውም እንዳላወቁ ሁሉን በሆድ ችለው ዝም ማለት እንደምን ይቻላል? እንዲህ ዓይነት ትህትና እንደምን ይደንቃል ! ምን ዓይነት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ነው?

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም "ናርምም እስመ ኢንክል ፈጽሞ ጥንቁቀ ነጊረ" (ይህንን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለንም እና ዝም እንበል) እንዳለው ዝም ከማለት በስተቀር ይህንን እንደምን ዘርዝሮ መጻፍ ይቻላል?

አባታችን በረከትዎ ትድረሰን!
https://t.me/Gamel_Tube