Get Mystery Box with random crypto!

ፈውሳችን በእርሱ ነው! በተለት ተዕለት የህይወት መንገድ የሚወጣና የሚወርድ፣ የሚመጣና የሚሔድ፣ | ምርጥ ጽሑፎች✍️✍️

ፈውሳችን በእርሱ ነው!

በተለት ተዕለት የህይወት መንገድ የሚወጣና የሚወርድ፣ የሚመጣና የሚሔድ፣ የሚያሳምምና የሚፈውስ የህይወት ገፅ አለ። በመኖር ውስጥ ጉራማይሌው ማንነት በገሃድ ይገለጣል፤ የማይታወቁ ባህሪያት ገሃድ ይወጣሉ፤ ያልተሰሙ ታሪኮች ይሰማሉ። እራስን በማዳመጥ ሂደት ከጊዜያዊው ህመም በላይ ዘላቂውና ፈዋሹ እራስን ማከም የተረጋጋውን ሰላማዊ ህይወት ያጎናፅፈናል። እራስን ማከም የሁላችንም ስጦታ ነው፤ እራሳችን ለእራሳችን ብቁ እንደሆንን የምናሳይበት ነው፤ በእኛ ውስጥ ፈውሳችን አምላክ እንደሆነ የማረጋገጥልን ነው። እራስን ማከም፣ እራስን መፈወስ (self-healing) የእራሱ መንገድ ቢኖረውም አንድ ሰው ያለማንም እርዳት ከደረሰበትና በጊዜው ካለበት ችግር መውጣት ከፈለገ እራሱ ላይ ያለውን ስልጣን ተጠቅሞ እራሱን በእራሱ እየጠገነና እየፈወሰ ነፃ መሆን የሚችልበት ሁነኛ መንገድ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ፈውሳችን በእርሱ ነው፤ የምንድነው በአምላካችን ሃይል ነው፤ እንደ አዲስ የምንታደሰው፣ ከህመማችን የምንነፃው፣ ያለፈ ታሪካችንን የምንሽረው፣ ማንነታችን የምናሻሽለው፣ ስብዕናችንን ወደ ላቀው ደረጃ ከፍ የምናደርገው በፈጣሪያችን መልካም ስጦታና በእራሳችን ይሁንታ ነው። ያንተ አንገት ደፍቶ መሔድ ግድ የሚሰጠው ሰው ያለ ይመስልሃል? ያንተ በመከዳትና በመገፋት መሃል መሰቃየት የሚያስጨንቀው ሰው ያለ ይመስልሃል? ያንተ ከብዙሃኑ መንገድ ወጥቶ ለብቻ መጓዝ የሚያሳስበው ሰው ያለ ይመስልሃል? አይምሰልህ። ያንተ እራስህን በእራስህ ማከም፣ አገግሞ መምጣት፣ እራስን መዝኖ አስተካክሎ መመለስም ያንተ እንጂ የሌላ ሰው ጉዳይ አይደለም። በነፃ አለም ነፃ ፍቃድ አለህ፣ ፍፁም አባት ፍፁም አምላክ አለህ። እራስህን ለማዳን ስታስብ የምትተማመነውና የምትደገፈው ሰውን ሳይሆን ችሩ አምላክህን ነው።

አዎ! ሰው ለሰው ያስፈልጋል ነገር ግን አንዳንዴ ለእራስህ ምንያክል ብቁ እንደሆንክ ማየት ይኖርብሃል። ሰዎች በየደቂቃው በሚቀያየሩበት አለም እራስን በእራስ ለማከም መሞከር፣ " ከአምላኬ ቀጥሎ ለእራሴ እኔ አለው፣ እኔ ደርስለታለው " ማለት ወሳኙና አዋጩ መንገድ ነው። በአንተ ውስጥ ከሚመላለሰው አሉታዊና ጎጂ ስሜት ከእራስህ ውጪ ሌላ ነፃ የሚያወጣህ ምድራዊ ሃይል የለም። ጭንቀትህን ለፈጣሪህ የምትናገረው፣ ህመምህን ለሰዎች የምታማክረው፣ ያለፈ መጥፎ ታሪክህን የምትሽረውና በአዲስ ማንነትና መንገድ ተመልሰህ የምትመጣው አንተ ነህ። ነፃ መሆን ከፈለክ ነፃ የምትሆንበት መንገዶች አሉ። እራስህን በእራስህ ነፃ ከምታወጣው ነፃነት የተሻለ መንገድ ግን አታገኝም። በአንተ ውስጥ የሚሰራው አምላክህ ነው፤ ብርታትህ፣ ድጋፍህ፣ አለኝታህ፣ ጠባቂህ፣ ፈዋሽህ እርሱ ነው። በፈጣሪ ሃይል፣ ባንተ ፍቃድ እራስህን ፈውስ፣ ስብራትህንም ጠግን።
═════════❁✿❁ ═════════
ሶሻል ሚዲያ ያገኘነውን እውቀት ለሌላውም የምናደርስበት የመረጃ ቋጥ ነውና ይህን ጹሁፍ ካነበባችሁት በኋላ ለሌላውም እንዲደርስ #ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ!!! የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q