Get Mystery Box with random crypto!

ሲህር ምንድነው? አንባቢ ሆይ አላህ ይጠብቅህና ሲህር ቢያሳምምህና ራስህን መቆጣጠር ቢያቅትህ ቤተሰ | Mohammed Seid Islamic & Traditional Medicine መሀመድ ሰይድ የቁርአንና የባህል ህክምና ማእከል

ሲህር ምንድነው?
አንባቢ ሆይ አላህ ይጠብቅህና ሲህር ቢያሳምምህና ራስህን መቆጣጠር ቢያቅትህ ቤተሰብህ በየትኛው የህክምና አይነት ቢያሳክሙህ ትመርጣለህ?
ሲህር በአላህ በካዱ ጠንቋዮችና በሸይጧን ትብብር የሚሰራ ክንውኑ ከእይታ የተሰወረ በሰው ልጅ ላይ በህይወቱ፣በጤናው፣በንብረቱ ና በክብሩ ላይ ችግር የሚያመጣ በሽታ ወይም ተንኮል ነው።ብዙዎቻችን እስከምንያዝ ስለሲህር እንዘናጋለን።በዘመናዊ
ህክምና ክትትል አመታት ቆይተው ቁርአን ሲቀራላቸው የዳኑ ብዙ እህት ወንድሞች አጋጥመውናል።
ብዙ የአካዳሚክ ትምህርት የቀሰሙ ሰዎች በሳይንስ
አልተረጋገጠም ብለው አለመኖሩን አስረግጠው ቢከራከሩም በተጨባጭ ሰዎች ሲታመሙ በማየታችን በቁርአንና በሀዲስ
የተጠቀሰውን የሲህር ጉዳይ ችላ ማለት የለብንም።ሲህር
የሚሰሩም ሆነ የሚያሰሩት በአላህ በመካድ ስለሆነ ወደጠንቋይ መሄድ ለአኼራ ኪሳራ ይዳርጋል።
ፈውስ፦ሲህር በአላህ ፈቃድ የያዘን እንደሆነ በብዙ መንገዶች የፈውስ አገልግሎቶች አሉ።ይሁንና ሁሉም ሀላል ናቸው ማለት አይደለም።የፈውሱን ሁኔታና በሸሪኣ ያለውን ፍርድ እናያለን።
1–ዛር፥ዛር የሚከናወነው የጂን/አጋንንት በመጥራትና
በመለመን ሲሆን ጂን የሚጠራው ሙስሊም ሊመስል ስለሚችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል።የታመሚውን እጅ በመያዝ ህመሙን መናገር፤ የመኖሪያ አካባቢ፣ያሳለፍነው ህይወት ሌሎች ጉዳዮቻችንንም ሳንናገረው በመናገር ወልይ ለመምሰል ይሞክራል።ሲህር የሰራብንንም ሊጠቁመን ይችላል።አላህ ሊፈትነን ያመጣውን ህመም አላህን በማስቆጣት አናመልጠውም።
2–በኩፍር፦በተለይ ክርስትያኖች ጋር የሚሄዱ
ያጋጥማቸዋል።"ለማርያም ስለት ግቡ፤በእየሱስ እመኑ
ትድናላችሁ" አያሉ ይሰብካሉ።ከሲህር ህመም ለመዳን ጀሀነም መግባትን የሚመርጥ አስተዋይ ይኖራል?
3–በእፅዋት፦አንዳንድ እፀዋት መርዛማነት እንዳላቸው ሁሉ ሌሎች ደግሞ የመድሀኒት ባህሪ አላቸው። መድሀኒቱ
በሙስሊምም ሀይማኖት በሌለው የባህል ሀኪም ዘንድ ሊገኝ ይችላል።ማስተዋል ያለብን ግለሰቡ ትክክለኛ ታማኝ ሰው ነው? አንዳንዶች በታማሚ ሲህር ሲሰሩ አንዳንዶች የማይጠቅም ወይም የሚጎዳ መድሀኒት ይሰጣሉ።
4–በሸሪኣ፦ከነቢዩ(ሰአወ) እና ከሰሀቦች በተገኘው ሁኔታ ቁርአን እየቀሩ እና የነቢዩን (ለታማሚ የሚደረጉ) ዱአዎችን እያደረጉ ታማሚው እንዲፈወስ ማገዝ።ከሁሉም ተመራጩ ይህ አይነቱ ነው።
5–በዘመናዊ ህክምና፦ምንም እንኳ ዘመናዊ ቢሆንም
ታማሚው የታመመው በሲህር እስከሆነና የሳይንሱ ሰዎች ጂን፣አይነናስና ሲህር የለም ብለው ክደው የሲህር ታማሚን የሚፈውስ መድሀኒት ይኖራቸዋል ማለት ዘበት ነው።ምናልባት ከባህል ህክምና ተቀብለው በኪኒንና በመርፌ መልክ ካቀረቡ እንጂ አእምኖው በሲህር የታወከን ግለሰብ መፈወስ አይችልም
ለዚህም እኮ ነው በሲህር የታመሙ ግለሰቦች ለአመታት ከኪኒን ሳይላቀቁ ከሰውነት ተራ ወጥተው ከህይወት በታች ከሞት በላይ የሆነ ህይወት የሚኖሩት።
አንባቢ ሆይ አላህ ይጠብቅህና ሲህር ቢያሳምምህና ራስህን መቆጣጠር ቢያቅትህ ቤተሰብህ በየትኛው የህክምና አይነት ቢያሳክሙህ ትመርጣለህ? እንግዲያውስ አንተም ቤተሰብህና
ወዳጅህ ቢታመሙ በትእግስት ለማሳከም ጥንካሬና ጥንቃቄ ይኑርህ።
《ሸይጣን በአደም ልጅ በደም ቧንቧው ይፈሳል ።ደም
የሚደርስበት ይደርሳል》ነቢዩ ሙሀመድ (ሰአወ)
የሚፈሉጉት ጥያቄበmobile, FBinbox,whatsApp,telegram, comment,imo ይጠይቁ
»የሞባይል ቁጥሩን ሴቭ ያድርጉ ነገ ይጠቅምዎታል ወይም ለተቸገረ ይለግሱታል share ያድሮጉት ሌሎች
ይጠቀሙበታል፣ምንዎን ያምዎታል የሚለውን የFBፔጁን like ይበሉ
0118820789/0911457737/0901954220