Get Mystery Box with random crypto!

አትስጉን፣አትፍሩን፣እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጥልን በክርስቶስ መስቀል ገለን፣ሰላምን ለዓለም የምናውጅ እ | Mehreteab Assefa

አትስጉን፣አትፍሩን፣እኛ ኦርቶዶክሳውያን ጥልን በክርስቶስ መስቀል ገለን፣ሰላምን ለዓለም የምናውጅ እንጂ የሰላም ሥጋት አይደለንም።በነገው የቅዱስ አባታችን የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ በመስቀል አደባባይ የምንገኝበት ምክንያት ፣ 1ኛ የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሳቢ፣ የመንጋውና የቅድስት ቤተክርስቲያናችን መሪ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሆኑት ታላቁ አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ በሥጋ ስለተለዩን ሀዘናችንን ለመግለጽ ነው። 2ኛ ቅዱስ አባታችን ታላቅ የበረከት አባት ስለሆኑ የቅዱስነታቸውን በረከት ለመቀበል ነው።ምክንያቱም እግዚአብሔር የቅዱሳኑን አጽም ስለሚጠብቅ፣በኤልሳዕ አጽም ሙት ያነሳና ተአምር ያሳየ እግዚአብሔር፣ ዛሬም በቅዱስ አባታችን አጽም ፣ለህዝባችንና ለሀገራችን ተአምር ይሰራል፣የኢትዮጵያንም ትንሳኤ ያረጋግጥልናል ብለን ስለ ምናምን ነው።የድንግል ልጅ ምን ይሳነውና?????????? 3ኛ ኦርቶዶክሳውያን ምን ያህል ክብረ ክህነትንና አባትን አክባሪ መሆናችንን ለዓለም ለማሳየት ነው።ብርሃናችሁ በሰው ሁሉ ፊት ይብራ እንዲል ቅዱስ ወንጌላችን። ስለዚህ ይህንንና ይህንን በመሳሰለው የተቀደሰ ዓላማ ነገ መጋቢት 3/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት በመስቀል አደባባይ ተገኝተን ቅዱስ አባታችንን ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ እንሸኛለን። ይኸው ነው እንግዲህ ዓላማችን።እረኛው ሲለያቸው በጎች ይጮሀሉ። በጎቹ እረኛቸውን መቀማታቸው ሳያንስ፣ይባስ ብሎ ጩኸታቸውን መቀማት(ቀ ጠበቅ ብሎ ይነብብ) ግን የለባቸውም።የተዋህዶ እረኛ መርቆርዮስ ፣ሲጠብቃቸውና ሲንከባከባቸው ከኖረውና መንጋው ከሆኑት ከምዕመናን ሲለይ፣ጩኸት አለ፣መደናገጥ አለ፣ሀዘን አለ። ስለዚህ ሀዘናችን ይከበር። የጩኸቱ ምክንያት የእረኛው ከበጎች መለየት ብቻ ነውና ለጩኸቱ ምክንያት አይፈለግለት። የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ውሻ፣በንጉሡ ላይ ተንኮል አስቦ በመጣ እንግዳ ላይ ትጮሀለች የሚባል ነገር አለና።አንድ ምንም ክፋትና ተንኮል በንጉሱ ላይ ያላሰቡ ልበ ቀና ሰው ወደ ንጉሡ ሲመጡ አይታ፣ያቺ ልማደኛ ውሻ እኒህ ሰው ላይ እየዘለለች መጮህ ስትጀምር፣በነገሩ ግራ የተጋቡት እንግዳም "" ኸረ ጃንሆይ ይቺ ውሻ ሰው ያላሰበውን ታሳስባለች "" አሉ ይባላል። ስለዚህ ዛሬም አደራ የምንላችሁ ነገር ያላሰብነውን አታሳስቡን ነው።አላማችን ከላይ የገለጽኩት አንድ እና አንድ ነው።እርሱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ቅዱስ አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ናቸው።በእውነት የዱስነታቸው በረከት ይደርብን። ምሕረተአብ አሰፋ መጋቢት 3/2014/ዓ/ም