Get Mystery Box with random crypto!

የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር ሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በጥንታዊው የደብረ ብርሃን | Mehreteab Assefa

የብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ሥርዓተ ቀብር ሐሙስ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በጥንታዊው የደብረ ብርሃን ቅድስተ ሥላሴ ተፈፅሟል።

ከሥርዓተ ቀብር በፊት ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እና በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት የጸሎተ ፍትሐት መርሐ-ግብር ተካሂዶ ነበር።

ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም በሰሜን ሸዋ ዞን ፣ በትግራይ እና በአርሲ ሀገረ ስብከቶች ቅድስት ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል። ብጹዕነታቸው በ97 ዓመታቸው ነው ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት።
ቅድስት በረከታቸው በሁላችንም ላይ ትደር