Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚ | MHSS STUDENT LEARNING SYSTEM

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ 15 ይከናወናል።
------------------------
የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20 - ሚያዚያ 15,2015ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለፀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ እንደሚከናወን ገልፀዋል።

መረጃዎችን በትክክል ባለመሙላት ምክንያት የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንደሚፈጥር የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ለማስቀረት ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
ያልተመዘገበ ተማሪ የ 2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዶ/ር እሸቱ ገልፀዋል።

በ 2014ዓ.ም በነበረው የምዝገባ ሂደት የተፈታኞች ምዝገባ መረጃ ጉድለት የነበረበት እንደነበር እና በዚህም ምክንያት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ የተራዘመ እንዲሆን እንዳደረገው በመግለጫው ተነስቷል ።

በመግለጫው ምዝገባው ከ መጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015ዓ.ም ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግስት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለ ድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9-12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡም ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
በመግለጫውም ተማሪዎ፣ ወላጆች ፣ መዝጋቢዎች እና ከመምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።