Get Mystery Box with random crypto!

#21_ምርጥ_አባባሎች 1. 'አንድ የደስታ በር ሲዘጋ፣ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል። እኛ ግን አብ | MHSS STUDENT LEARNING SYSTEM

#21_ምርጥ_አባባሎች

1. "አንድ የደስታ በር ሲዘጋ፣ ሌላ የደስታ በር ይከፈታል። እኛ ግን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ተዘጋው በር እንጂ ወደተከፈተልን አናይም፡፡"
#ሔለን_ኬለር

2. ‘’አሸናፊ ለመሆን አንድም ሰዉ እንኳ በማይተማመንብህ ወቅት በራስህ ማመን አለብህ።’’
#ሹገር_ሬይ_ሮቢንሰን

3. "የራስህን የህይወት እቅድ ዲዛይን ካላደረግክ ዕጣ ፈንታህ የሚሆነው በሌሎች እቅድ ውስጥ መኖር/መውደቅ ይሆናል።
#ጂም_ሮን

4. "የምታልፈው ደቂቃ የእያንዳንዱ ሰው እኩል ሀብት ናት፤ አንዴ ካለፈች ግን የማንም ሀብት አይደለችም።"
#ማርክስ_አውሬሊየስ

5. "የደስታ ምንጭ የምትሞላውና ሳታቋርጥ የምትፈሰው ከውስጣችን በሚፈልቁ ብሩህ አስተሳሰቦችና ስሜቶች ነው።
#ዊሊያም_ላዩምፊሊፕስ

6. "በውስጥህ ብዙ ዓይነት ባህሪያት፣ ስብዕናዎች እንዳሉ አትዘንጋ ለራስህ እንግዳ አትሁን፡፡ የአዕምሮ ግዛቶችን ዘልቆ ገብቶ ማንነትንና ችሎታን እንደማወቅ ታላቅ ጀብዱ ከቶ የለም።"
#ሩሶ

7. "እንቅፋቶች እንደ ቢላዋ ናቸው፡፡ በስለቱ ከያዝናቸው ይቆርጡናል፡፡ በእጀታቸው ከያዝናቸው ደግሞ ይጠቅሙናል።"
#ጂምስ_ራስል_ሐዌል

8. “ተሳስተህ አታውቅም ማለት አዋቂ ነህ ማለት አይደለም፤ ምንም የማይሞክር ሰውም ከስህተት ነፃ ነውና።"
#እንግሊዛውያን

9. “የሰዎችን መልካም ገፅታ ብቻ ነው የምመለከተው። እኔ ራሴ እንከን የለሽ ሰላልሆንኩ የሌሎችን እንከን የምቆፍርበት ምክንያት የለኝም ።"
#መሀተመ_ጋንዲ

10. "የማይገለን የህይወት ፈተና፣ ጠንካራ ያደርገናል።”
#ፍሬደሪክ_ኒቼ

11. "በዓለም ላይ ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር፤ ያን ካደረግክ ራስህን እየሰደብክ ነው።”
#አለን_ስትራክ

12. "ሌሎች ሰዎች ምን ያህል በጣም ጥቂት ጊዜ (ከስንት አንዴ) ስለአንተ እንደሚያስቡ ብታውቅ ኖሮ፣ ሌሎች ስለ እኔ ምን ያስባሉ ብለህ አትጨነቅም ነበር።”
#ኤልኖር_ሮዝቬልት

13. "እራስን ሁን፣ የሚሰማህንም ተናገር፣ ምክንያቱም እራስህን በመሆንህ ቅር ለሚላቸው ሰዎች ቦታ/ደንታ መስጠት የለብህም፤ የሚበጁህ ሰዎች ደግሞ እራስህን በመሆንህ ቅር አይሰኙምና።”
#ዶ/ር_ሱስ

14. "ቅን አሳቢ ሰው ጽጌረዳ አበባው ላይ ሲያተኩር ጨለምተኛ ሰው ግን ጽጌረዳውን በመዘንጋት እሾሁ ላይ ያተኩራል።”
#ካህሊል_ጂብራን

15. "ሌላን ሰው ለመሆን መፈለግ የራስን ማንነትን ማባከን ነው።”
#ኩርት_ኮቤይን

16. "የዚህች አለም ታሪክ ማለት በራሳቸው የሚያምኑ የጥቂት ግለሰቦች ታሪክ ማለት ነው።”
#ስዋሚ_ቪቬካናንዳ

17. "የወደፊቱን ለመተንበይ የተሻለው ዘዴ፤ ወደፊትን መፍጠር ነው።”
#አለን_ኬይ

18. “እምነት ማለት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ››
#ማርቲን_ሉተር

19. "ማለም የፈጠራ መነሻ ነው፤ የምትፈልገውን ታልማለህ፣ ያለምከውን ትመኛለህ፤ በመጨረሻም የተመኘኸውን ትፈጥራለህ።"
#ጆርጅ_በርናንድ_ሾው

20. ‘’ለመጀመር ስኬታማ መሆን አይጠበቅብህም ነገር ግን ስኬታማ ለመሆን መጀመር አለብህ ፡፡
#ዚግ_ዚግላር

21. "ደሀ ሆነህ ብትወለድ ጥፋቱ ያንተ አይደለም፤ ደሀ ሆነህ ብትሞት ግን ጥፋቱ ያንተ ነው።"
#ቢል_ጌትስ