Get Mystery Box with random crypto!

ፊርማ ለወዳጅ ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ል | መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

ፊርማ ለወዳጅ

ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ልጆች በሙሉ።

አንዳንዶቻችሁ በቅርብ ለገበያ የቀረበውን መጽሐፌን " አዘጋጁ ካልፈረመበት አንገዛም ሙተን እንገኛለን" ማለታችሁን ሰምቻለሁ። ሌሎቻችሁ ደግሞ "ለበዓል መጥተን ሰኞ ፣ ማክሰኞ ሂያጅ ነን። መጽሐፉን አስቀምጥልን" እያላችሁ በውስጥ መስመር እየወተወታችሁኝ ነው። እኔ የሺህ ወዳጅ ወንድማችሁ ወገቤ እስቲንቀጠቀጥ ጥፌ ማዘጋጀቴ አንሶ እናንተን እግር በእግር እየተከተልኩ መጣፍ ማቀብልበት ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና የግቢ ጉባኤ ፣ የዓለም ት/ቤት ፣ የፕሪፕ ፣ የሚካኤልና የሌላም ሌላም የሰፈር ወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ደቀ መዝሙርና ደቂቀ መዝሙር ሁሉ በትንሣኤ ዋዜማ በቀዳም ሥዑር ዕለት በደብረ መድኃኒት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከትተህ ላግኝህ። ማኅተምና ፊርማዬን ከስምህ ጋር ከትቤ እንዳስፈላጊነቱም በሥዕል አስውቤ ዘላለማዊ የወዳጅነት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ መጽሐፈ መሠረትን አበረክትልሃለሁ። መርኃ ግብር አይደለም ደግሞ መጥቶ መሄድ ነው። አንድ የጋራ መገናኛ ለመፍጠር ያመች ዘንድ ነው። ማን ያውቃል በስንት እግዚኦታ ፣ ሠርግና ምርቃት መገናኘት ያልሆነለትን ጀማ ማገናኛ ሰበብ ይሆናል። ዘር ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ እድሜ ፣ ባች ፣ ጸባይ ፣ የአመራርነትና የሥራ እርከን አይለይም። "ከሣችን አውቀዋለሁ" የሚል ሁሉ ጎራ ይበል።
https://www.instagram.com/p/Cq8b-10oXh8/?igshid=MDJmNzVkMjY=