Get Mystery Box with random crypto!

እስቲ ገድሉን እዚያ ያለውን እናንብ” እላቸዋለሁ። “ጥሩ!” ይላሉ ገዳማውያኑ እያበሉ ዐሥራ አምስት | መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

እስቲ ገድሉን እዚያ ያለውን እናንብ” እላቸዋለሁ። “ጥሩ!” ይላሉ ገዳማውያኑ እያበሉ ዐሥራ አምስት ቀን ወይ ሳምንት ተቀምጬ ነው እንጂ የገባሁበት ገዳም ዝም ብዬ አልሄድም። በበዓል አይደለም የምሄደው። ከተጓዦች ጋር አይደለም የምሄደው። ከዚያ ሳሊ ገበያ አጠገብ ወፍ ዋሻ የምትባል አለች። የዝማሬ መዋሥዕት መማርያ ናት። እዚያ የተማረ ዙር አምባ ሄዶ ይመረቃል። ዝማሬ መዋሥዕት አልሞከርንም።
እዚያ ጋይንት የኔታ እጅጉ የሚባሉ ዘንድ ዜማ በጥቅሉ ከአራት መምህራን ዘንድ ዜማ ተማርንና እኔም ጓደኛዬም አንለያይም። ሰባክያን ሲሰብኩ ምን ሲሉ ደስ አለን። መንፈስ ቅዱስ መራን። ትርጓሜ ለመማር ደሞ የት እንሂድ ብለን አየን። እዚያም መካነ ኢየሱስ ነበሩ አንድ ታላቅ አባት። አባትህ እዚያ ተምረዋል መልአከ ምሕረት። የትግሬ ሰው ናቸው። የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ነው ሚባሉ። የቅኔና የመጽሐፍ መምህር ናቸው። አዪ! ወንበር አይደርስም። በዚህ ላይ ሰውየው ጸሎተኛ ስለሆኑ ወደ ቅኔ ማስነገሩ እንጂ ወደ መጽሐፉ አይደሉም። ስንጠይቅ “መጽሐፍ ድሮውንም እዚህ አይደለም ሂዱ ጎጃም ዲማ” ተባለ።

ቅኔስ።

መርጡለማርያም ጥሩ የሆኑ አባት ነበሩ። አለቃ ኢሳይያስ ይባላሉ። ዋድሌ ናቸው። መምህር የሆኑ ፤ አባት የሆኑ በእውነት! ትንቢተ ኢሳይያስ ናት ልጃቸው። ቅኔ ትቀኛለች። አታሲዝም። ትንቢተ ኢሳይያስ ነው ስሟ። እዚያ ገባን። እዚያም ደግሞ አሁን ግብረ በላ ነኝ እኔ። አይለቁኝም በእድሜ ስላነስኩኝ። ሌላ የለም እኮ አዪ እኔ ደሞ ወደ ትምህርት ስል ዛሬ ቅፈፋ ሲሉ አዪ እላለሁ። ጓደኛዬ ይሄዳል ያኔውኑ። የእኔንም ለእርሱ ስጡ ብዬ ለመንደሮቹ ስላሳወቅኩ ይሰጡታል የሁለታችንንም እንጀራ። የሚሰጡት ምንድነው ለእኔ ሲባል ቅርብ ቦታ መደቡኝ። ለእኔ አምስት ቤት ለእርሱ አምስት ቤት ዐሥር ቤት። ከዐሥር ቤት አንዳንድ እንጀራ እየታጠፈ ነው ሚሰጠው። ጨው ስጡኝ ካለ አንዳንድ ጭልፋ ጨው ይሰጣሉ። ጨው ማለት እዚያ ድልህ ነው። ያንን ይዞ ይመጣል። “አዪ እንጀራ በጨው አይደለም ና ና አንተ” ይሉኛል። ልክ እንደ የኔታ ይኄይስ አሁንም እዚህ ግብረ በላ ነበርኩ። የኔታ እጅጉ ቤት ግብረ በላ አይደለሁም። ወንድሜ ያመጣል እንጀራ። እንዲያው አንዱ የገብስ እንጀራ እንኳን ለሁሉ ይበቃል። መንደራቸው የራቀ ልጆች ይሳተፋሉ ከእኛ ጋር። እንግዳ ሲመጣ እናሳትፋለን። እግር አጥበን ራት ሰጥተን እናበላለን። የኔታ እጅጉ ቤት አልበላሁም። የኔታ ምትኬና ሸዋ ላይ የጠቀስኳቸው መምህራን ንባብ ያስተማሩኝ ጋርም አልበላሁም። ወላጆቼ አካባቢ ስለሆነ አንጎለላ መምሬ ዳምጤም አያቴ ቤት አጠገብ ስለሆኑ ቤቴም ቅርብ ስለሆነ እንጀራ ከቤቴ ነው ምበላው። አንጎለላም ደጀ ሰላም ሁሉ አለ አልሄድም። ልምድ የለኝም የደጀ ሰላም። ከዚያ እንግዲህ በየዓመቱ ደብረ ሊባኖስ አንቀርም እኔም ወንድሜም።

እንግዲህ ቅኔ የኔታ ኢሳይያስ ዘንድ ግሩም በሚያሰኝ ሁኔታ ተቀኘሁ። እዚያ ብሉይ መጻሕፍትን ተማርኩ። “እማራለሁ እይዛለሁ አይ የኔታ ይጠይቁኝ እንጂ እኔ ይኼንን ሁሉ በቃል ሳጠና አልገኝም። በቃል ለምን አጠናለሁ እኔ መጽሐፍ አለ አይደለም ወይ? ያስረዱኝ ይጠይቁኝ” እላቸዋለሁ። ደስ ይላቸዋል በቃ። ከዚያ ጀምሮ ነው እንግዲህ በቃል ትምህርት ላይ ያለኝ አቋም እንዲያ የሆነው።
በዚህ ሁኔታ አራቱን ብሔረ ነገሥት ስምንቱን ብሔረ ኦሪት የኔታ ኢሳይያስ ዘንድ ከቅኔ ጋር እኔና ወንድሜ ተምረን እዚያ እንግዲህ ዜማ ተውን። ዜማ ለምን ተዋችሁ ብለኸኝ ታውቃለህ? የተውኩበትን ምክንያት ነግሬአችኋለሁ? አልነገርኳችሁም።
አሁን ከአንጎለላ ጀምሮ በደቡብ ጎንደር የተማርኩት የቤተልሔም ዜማ ነው። ቁሙ ማለት ነው። አቋቋም አልተማርኩም። አቋቋም መማር ከቅኔ በኋላ ስለተባለ ወደ ጎጃም መጣሁ ማለት ነው። የኔታ ገብረ ጊዮርጊስ ዘንድ ብንሄድ ወንበራቸው ፈጣን አይደለም። ዋልን አደርንና እንዲህ ነው ሚማሩት አዎ አይ እንሂድ አልን መርጡለማርያም መጣን ኢሳይያስን አገኘን። ባለቤታቸው እንዴት ያሉ ናቸው። እንዴት መጣችሁ ወንድሞች አሉ። የት ናችሁ ሸዬዎች ናችሁ አሉ። ያውቁናል በመልካችን ባነጋገርም።
“እንዴት መጣችሁ?”
“ኧረ እንዲያውም ጋይንት ድረስ እንዲህ ሄደን ነበረ።” ብለን ስንላቸው ገረማቸው።
“አንተም እዚያ ሄድክ?”
“አዎ”
“አዪ ቅኔ ለመማር ነው?”
“አዎ”

ጭናቸውን መታ መታ አድርገው ቅኔ ሲጀምሩ ቀድመን እንገኛለን። የቅኔው ተማሪ ሲሄድ መጽሐፍ ያስተምራሉ። ቁጭ!
“ምነው?”
“እኛም እንማራለን!”
እንዳጋጣሚ ኦሪት የጀመሩ ነበሩ። ከነእርሱ ጋር ሄድን። ዳዊትን ከጨረስን በኋላ መጽሐፈ ነገሥት ከተማርን በኋላ ሐዲሳት ልንማር ብለን ቅባቶች ናቸው እዚያ ያሉት።
ዜማ የተውንበት ምክንያት ይኽ የጎጃም ዜማ አጫብር ፣ ወጨሬ ሦስተኛም አለ ስሙ ጠፋኝ እንዲህ ያለ ነው። ርዝመቱ አንጀት ይበጥሳል። ዜማው ጥሩ ነው። ግን ማይዘለቅ ነው ርዝመቱ። ልብ ያፈርሳል። ወረብም ስንገባ ለመወረብ የጎንደሮች አጭር አጭር ናት።
የነሱ እንደዚያ ሲሆንብን ዜማ ተውን ተውን ተውን!

ከዚህ የቀጠለውንና የተረፈውን በEOTC TV ከተላለፈው የአንደበታቸው ምስክርነት ያድምጡ።