Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurzhohte — መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmurzhohte — መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን
የሰርጥ አድራሻ: @mezmurzhohte
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.33K
የሰርጥ መግለጫ

✟የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአቱን የጠበቀ በሰንበት ት/ቤቶች የሚዘመሩ መዝሙራትን ከነ ግጥም እና ዜማቸው ለማግኘት ይቀላቀሉን @mezmurzhohte
☆ለማንኛውም ሐሳብ አስተያየት ጥያቄ ጥቆማ
@Kal11
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን መዝ ፻፶፥፮

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-19 09:57:13 በኆኅተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት የተዘጋጀ አዲስ ዝማሬ





2.1K viewsedited  06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 11:47:52 ኆህተ ብርሀን ንዋያተ ቅድሳት መሸጫ
የ ገርጂ ኆህተ ብርሀን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሰንበተ ትምህርት ቤት ሱቅ
*መንፈሳዊ መፅሐፍት
* ዘቢብ፣እጣን፣ጧፍ እና ጥላዎች
*የፀሎት መፅሐፍት
*የተለያዩ ቅዱሳን ስዕላት አንዲሁም ሌሎች መገልገያዎች
ለበለጠ መረጃ @MikAlexander
https://t.me/zhohtebirhanstore
2.3K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 09:24:48 አድኚኝ እናቴ
አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጢያቴ ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ
የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሃል እንደትሆኚን ኃይል
ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቁልና
ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና
ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለሁ
ግራ ቀኝ አልልም ምርኮኛሽ ሆኛለሁ
የመንግስቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ
መልካም ሥራን መሥራት እኔን አስተምሪኝ
በሥጋ ደክሜ በነፍስ እንዳልጠፋ
እማፀንሻለሁ ድንግል የእኔ ተሰፋ
የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ
መልካም ሥራን መሥራት እኔን አሰተምሪኝ
አንቺ የሌለሽበት ጉባዔው ባዶ ነው
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው
ከመካከል ገብተሽ ሙይው የጎደለው
ሠርጉ ተደግሷል ጎብኚልን ጓዳው

@mezmurzhohte
2.2K viewsedited  06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 09:21:48 ጌታ ሆይ ውለታህ
ጌታ ሆhይ ውለታህ ታምራትህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው(3)
በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል
ስለ ኃጢአቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል
ጌታ ሆይ ውለታህ ታምራትህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
በሐዘኔ ደርሰህ ፈጥነህ አረጋጋኸኝ
አይዞህ ልጄ ብለህ ስወድቅ አነሳኸኝ
ከማይጠፋው እሳት ከሞት ያወጣኸኝ
ላንተ የምከፍለው ምን ስጦታ አለኝ
እውነተኛ ረዳት ወገኔ አንተ ነህ
ጌታ ሆይ ከእናት ልጅ እጅግ ትበልጣለህ
መታመን በአንተ ነው ደግሞም መመካት
ወቅት የማይለውጥህ የማታውቅ ወረት
ስምህ ምግቤ ሆኖ ስጠራህ እጠግባለሁ
ፍቅርህን ቀምሼ ፍፁም እረካለሁ
በሰማይ በምድር በነፍስም በሥጋ
ባንተ እመካለሁ አልፋና ኦሜጋ



@mezmurzhohte
1.9K viewsedited  06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 09:19:24 ወላዲተ አምላክ
ወላዲተ አምላክ የሁሉ እመቤት
ለምኝልን ለኛ ከልጅሽ ምህረት
በአንቺ አማላጅነት በእርሱ ቸርነት
እንዲያወጣን ነፃ ከፍርድ ቅጣት
ቅድስት ሆይ ለምኝልን
በበደል ተዳክሞ ፈቃደ ነፍሳችን
በምድራዊ ምኞት ናወዘ ልቦናችን
ፍቅርና ትህትና ጠፍቶ ከፊታችን
ለሞት እንዳይሰጠን ይህ ክፉ ስራችን
የምስኪኖች ተስፋየደካሞችም ኃይል
ጠውልገናልና ጥላ ሁኝን ድንግል
እምነት ጨምሪልን ልቦናችን ይቅና
እመአምላክ አብሪልን የመዳንን ፋና
ፍጹም እንዳናዝን እንዳናፍር ኋላ
ተነጥቀን እንዳንቀር ከዘላለምe ተድላ
በፍቅርሽ መልሺን ከሲኦል ጎዳና
ድንግል መመኪያችን ተስፋችን ነሽና



@mezmurzhohe
1.8K viewsedited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 09:14:05 ልቤ አቤት በል እንጅ
ልቤ አቤት በል እንጅ አምላኬ ሲጣራ
ኃጢአትን ተውና መልካም ምግባር ሥራ
በደሌን አውቄ ይቅርታ ልጠይቅ
ሁሉን ቻይ ነህና ፍጥረትን የማትንቅ
አለቅሳለሁ ዘወትር አነባለሁ
አውቃለሁ አምላኬ ብዙ በድያለሁ
ለቅሶና ጩኸቴን ተቀበለኝ
ጐስቋላ ሆኛለሁ ኃጢአት ያደከመኝ
መንገድ ተላልፌ ፈጣሪ አስቀየምኩህ
በሚጠፋ ንብረት አምላኬ ለወጥኩህ
አሁን ግን አምኜ ብዙ እንደበደልኩህ
ምሕረትን እንዳገኝ ይቅርታ ለመንኩህ
የኃጢአት መጋረጃ ፊቴን ሸፍኖታል
ኃይሌ ከእኔ ርቆ መቆም ተስኖኛል
ነሽና በፊቱ ክብር ሞገስ ያለሽ
ድንግል ልመናዬን አድርሽ ከልጅሽ
ጉልበት አንተ ሁነኝ መተማመኛዬ
በደሌን አጥፋልኝ ሁን አስተማረዬ
ከበደል እንድርቅ እጅህን ዘርጋና
ዳግም እንዳልበድል አጽናኝ በምስጋና


@mezmurzhohe
1.7K viewsedited  06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 09:12:39 ኑ እንቅረብ
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ(2)
ሥጋውን እንብላ(3)ደሙንም እንጠጣ
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተሰውቶልናል እንመገበው
እድፉን ኃጢአታችን በንስሐ አንጽተን
እንቀበል አምነን በልጅነታችን
መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱለት
ከዋክብተ ሰማይ የተነጠፉለት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት
ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን
የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ
ለግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ
መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በእልልታ
በኃላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ
ይኽን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይባት
ከአሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ
ይኽ ዓለም ጠፊ ነው በሃብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ



@mezmurzhohe
1.6K viewsedited  06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 09:11:29 የሰው ልጅ ሁልገዜ
የሰው ልጅ ሁል ጊዜ በጣም ደስ ቢለው(2)
ደግሞም የጭንቁን ቀን ማሰብ ተገቢ ነው(2)
ምንም ቢደሰቱ ቢበዛ ምቾት(2)
አይቀርም በኋላ መወሰድ በሞት (2)
ችግር ቢፈራረቅ ኀዘን ቢከበን(2)
ከክርስቶስ ፍቅር ማንም አይለየን(2)
ሳናውቀው ዲያብሎስ እንዳይነጣጥለን(2)
ፀንተን እንጠብቀው የእምነት ሰይፍ ይዘን(2)


@mezmurzhohe
1.6K viewsedited  06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ