Get Mystery Box with random crypto!

ጌታ ሆይ ውለታህ ጌታ ሆhይ ውለታህ ታምራትህ ድንቅ ነው አምላካዊ ቃልህ ስምህ | መዝሙር ዘኆኅተ ብርሃን

ጌታ ሆይ ውለታህ
ጌታ ሆhይ ውለታህ ታምራትህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው(3)
በሐዋርያት አድረህ ብዙ መክረኸኛል
ስለ ኃጢአቴ ሞተህ ሕይወት ሰጥተኸኛል
ጌታ ሆይ ውለታህ ታምራትህ ድንቅ ነው
አምላካዊ ቃልህ ስምህ ሕይወቴ ነው
በሐዘኔ ደርሰህ ፈጥነህ አረጋጋኸኝ
አይዞህ ልጄ ብለህ ስወድቅ አነሳኸኝ
ከማይጠፋው እሳት ከሞት ያወጣኸኝ
ላንተ የምከፍለው ምን ስጦታ አለኝ
እውነተኛ ረዳት ወገኔ አንተ ነህ
ጌታ ሆይ ከእናት ልጅ እጅግ ትበልጣለህ
መታመን በአንተ ነው ደግሞም መመካት
ወቅት የማይለውጥህ የማታውቅ ወረት
ስምህ ምግቤ ሆኖ ስጠራህ እጠግባለሁ
ፍቅርህን ቀምሼ ፍፁም እረካለሁ
በሰማይ በምድር በነፍስም በሥጋ
ባንተ እመካለሁ አልፋና ኦሜጋ



@mezmurzhohte