Get Mystery Box with random crypto!

✞ ቸርነትህ ነው ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ ላመስግ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ቸርነትህ ነው

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/

መክሊቱን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታህ እንዳትረሳኝ
በፍቅርህ ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በርሃብ በእርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ
ለይቅርታህ መጣሁ ተቀበለኝ

አዝ______

አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር
ስራህን ለትውልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
በሰው እጅ መመካት አቁሚያለሁ

አዝ______

እረዳቴ አንተ ነህ አውቂያለሁ
አንተ ከጠበቅከኝ በሕይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድሃኒቴ
የእኔን ስራ ተወው ተግባሬን
የመስቀሉን ነገር መርሳቴን
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ

አዝ______

ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/

                   መዝሙር
           ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
   ✥ @mezmurochh    ✥
   ✥ @mezmurochh    ✥
   ✥ @mezmurochh    ✥
   ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥