Get Mystery Box with random crypto!

✞ ​​የሲሎንዲስ ጥበብ የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ የናሆም መድሐኒት እወድሻለሁ ማርያም አከብር | መዝሙረ ዳዊት

✞ ​​የሲሎንዲስ ጥበብ

የሲሎንዲስ ጥበብ እወድሻለሁ
የናሆም መድሐኒት እወድሻለሁ
ማርያም አከብርሻለሁ
ማርያም እወድሻለሁ/፪/

አዝ____

ተጨንቄአለሁ ልንገርሽ
ምሥጥረኛዬ እናቴ ነሽ
ሠው የአልሠማውን ብርቱ ምሥጢር
ድንግል ሆይ ለአንቺ ለአማክር

ለቁሥለኛውም መድሐኒቱ
ለአዳም ዘር ሁሉ ነሽ ሕይወቱ
መፍትሔ አለ በእጅሽ
ተንበርክኬ ልማጸንሽ

አዝ____

ሳልናገረው ይገባሻል
የውሥጤ ሁሉ ይታይሻል
ድርሽ እናቴ ተረጅኝ
ያለ አንቺ ለእኔ ማን አለኝ

ደሥታዬ ደሥታ የሚሆነው
በሐዘኔም የምጽናናው
አንቺ ከእኔ ጋር ስለ ሆንሽ
ተጽናንቻለሁ በሥምሽ

አዝ____

ወንድሞቼ እንኳን ቢሸጡኝ
ሠው ሁሉ ጠላት ቢሆነኝ
በእመ አምላክ ሐይል ከብሬአለሁ
በጠላት ላይ ሠልጥኛለሁ

የረሱኝ ሁሉ የአስቡኛል
የተጣሉኝም የአከብሩኛል
አንቺ አንግሠሽኝ አልወድቅም
እቆማለሁኝ ዘለዓለም

አዝ____

መንገዴ ረዝሞ ደክሜብሽ
መከራው በዝቶ ታምሜብሽ
ወድቄ ሳዝን ድረሽልኝ
ለባርያሽ ሐይሉን እንድትሠጪኝ

ፍቅርሽ በውስጤ ተንሠራፋ
በእናትነትሽ ልቤ ሠፋ
የሚለያየን ማንም የለም
ማርያም ልበልሽ ለዘለዓለም

                  መዝሙር
           ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥     @mezmurochh     ✥
   ✥     @mezmurochh     ✥
   ✥     @mezmurochh     ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥