Get Mystery Box with random crypto!

ስላም ለሕላዌክሙ ዘአይትአወቅ እምጥንቱ ወዘኢይትረአይ ተፍጻሜቱ ሥሉስ ቅዱስ ዘኢትመውቱ እንዘ ሠለስ | መዝሙረ ዳዊት

ስላም ለሕላዌክሙ ዘአይትአወቅ እምጥንቱ ወዘኢይትረአይ ተፍጻሜቱ ሥሉስ ቅዱስ ዘኢትመውቱ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ ወእንዘ አሐዱ ሠለስቱ ለዕበይክሙ ፍፃሜ አልቦቱ

        መልክአ ሥላሴ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜነ

እንኳን ለአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዓለ ሥሉስ ቅዱስ በዓል ለአው ለቅዱስ ሶል ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በስላም አደረሳችሁ አደረስን


ጥር ፯(7) በዓለ ሥሉስ ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ ዘሮሜ ወኢፍራ ወአትንያኖ ወሉያ ወመይልን ወመሰላዮስ ወማርትያ

✤ ዘነግህ ምስባክ ✤

ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልአ ምድረ
ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዓ ሰማያት
ወእምእስትንፋስ አፉሁ ኵሉ ኀይሎሙ

✤ ትርጉም ✤

የእግዚአብሔር ቸርነትን ምድርን መላች
በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ
ኀይላቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ

             መዝ ፴፪-፭
                    32  5

✤ ወንጌል ✤

ማቴ ም ፳፰ ቁ ፲፮-ፍ.ም
            28    16  ፍፃሜው

የቅዳሴ ምንባባት

ቈላስ ም ፪ ቁ ፲-፲፯
፩ ዮሐ ም ፪ ቁ ፳፭-ፍ.ም
ግብ.ሐዋ ም ፳፪ ቁ ፯-፳፪

❖ ምስባክ ❖

የሐዩ ወይሁብዎ እምወረቀ ዓረብ
ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ
ወኵሉ ዓሚረ ይድኀረዎ

ትርጉም

እርሱ ይኖራል፤ከዐረብ ወርቅ ይስጡታል
ሁልጊዜ ወደርሱ ይጸልያሉ
ዘወትርም ይባረኩታል

             መዝ ፸፩-፲፭
                     71  15
❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፪ ቁ ፳፩-ፍ.ም
           2     21   ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ዘእግዚእነ

" በሱራፌል በኪሩቤል የምትቀመጥ አምላካችን እግዚአብሔር የምትመለከት ወንዶቹንና ሴቶቹን ባሮችህን ልጆቻቸውንም ባርክ "
        ቅዳሴ እግዚእነ
          ም ፩ ቁ ፸፰
              1 78

በዓሉን በዓለ ምህረት በዓለ ፀጋ በዓለ በረከት ያድርግልን አምላካችን መድኃኒታችን ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በምልጃዋ አትለየን ፍቅሯን በልባችን ጣዕሟን በአንደበታችን ታሳድርብን በዕፀ መስቀሉ ይባረክን ይጠብቅን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረድኤት ይጠብቅልን በየሰዓቱ በየደቂቃው ጠባቂ መላዕክት አያሳጣን በቅዱሳኑ ፀሎት ይማረን ዕጣነ አሮን ፀሎተ ምናሴ የተቀበለ ዘላለም ሥላሴ የኛንም ፆም ፀሎት ምስጋና በብሩህ ገጽ ይቀበልልን በዓል ተከትሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱሳን ይሰውረን ይጠብቅን ለሃገራችን ስላም ለህዝባችን አንድነትን ይስጥልን ለብርሃነ ጥምቀቱ በስላም ያድርሰን ህንጻ ስናዖርን ያፈረሰ ዘላለም ሥላሴ የኃጢአተኛን ድልድይ ያፈርሳል

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥