Get Mystery Box with random crypto!

✞ መርቆሬዎስ መርቆሬዎስ /2/ የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ | መዝሙረ ዳዊት

✞ መርቆሬዎስ

መርቆሬዎስ /2/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ

ባስልዮስ ጎርጎሪወቀስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ

አዝ_____________

ዑልያኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ

አዝ_____________

ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ

አዝ_____________

ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕት ጋ

አዝ_____________

አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥