Get Mystery Box with random crypto!

❖ ብክዩ ኀዙናን ሃልየክሙ ስደታ ለማርያም ❖     ትርጉም ምዕመናን የማርያምን ስደቷን አስባ | መዝሙረ ዳዊት

❖ ብክዩ ኀዙናን ሃልየክሙ ስደታ ለማርያም ❖

    ትርጉም

ምዕመናን የማርያምን ስደቷን አስባችሁ አልቅሱ

  ሰቆቃው ድንግል ደራሲ አባ ገብረኢየሱስ ዘደብረ መጓዬና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በአቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሥሮ ለሰይጣን አግዕዞ ለአዳም
ሠላም እምዜይስ
ኮነ ፍስሐ ወስላም

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ምድር ግብፅ  የተሰደደችበት ዓመታዊ መታሰቢያ እንዲሁም ለታላቁ ነቢይ ዕንባቆም በዓለ ዕረፍት አደረሳችሁ አደረስን

ግንቦት ፳፬(24) ቦአ እግዚእነ ውስተ ምድረ ግብጽ ወዕንባቆም ነቢይ

ዘነግህ ምስባክ

ወየአምር እግዚአብሔር ፍኖተ ንጹሃን
ወለዓለም ውእቱ ርስቶሙ
ወኢይትሐፈሩ በመዋዕለ እኩያት

ትርጉም

የንጹሓንን መንገድ እግዚአብሔር ያውቃል
ርስታቸውም ለዘላለም ነው
በክፍ ዘመንም አያፍሩም

    መዝ ፴፮-፲፰
           36   18

ወንጌል

ማቴ ም ፲ ቁ ፵-ፍ.ም
           10   40  ፍፃሜው

የቅዳሴ ምንባባት

ገላትያ ም ፬ ቁ ፬-፲፫
ራእ.ዮሐ ም ፲፪ ቁ ፲፫-ፍ.ም
   ዓዲ
፩ ጴጥ ም ፩ ቁ ፰-፲፫
ግብ.ሐዋ ም ፲፪ ቁ ፳-ፍ.ም

ምስባክ

ዘገብረ ተአምረ ግብጽ
ወመንክረ በሓቅለ ጣኔዎስ
ወረሰየ ደመ ለአፍላጊሆሙ

ትርጉም

በግብጽ ያነደረገውን ተአምራቱን
በጣኔዎስም በረሃ ያደረገውን ድንቁን
ወንዞቻቸውንም ወደ ደም ለወጠ

   መዝ ፸፯-፵፫
          77  43

ወንጌል

ማቴ ም ፪ ቁ ፲፫-፲፮
           2     13  16

ቅዳሴ

ዘእግዝእትነ

" ድንግል ሆይ ለዮሴፍ የታጨሽ ለመገናኘት አይደለም ንፁህ ሆኖ ሊጠብቅሽ ነው እንጂ እንዲሁ ስለሆነ "
      ቅዳሴ ማርያም
       ም ፩ ቁ ፵፬
            1    44

በዓሉን በዓለ ድኀነት በዓለ ምህረት ያደረግልን ለአረጋዊ ዮሴፍ ለቅድስት ሱሎሜ የተለመነች እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ በምህረት በድኅነት ትለመነን ከልጁ ከወዳጁ ታማልድ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥