Get Mystery Box with random crypto!

❖ ጥቀ ሠነይኪ ወጥቀ አደምኪ አፈቅሮ ለፍግዕኪ ❖        ትርጉም ወዳጄ ሆይ እንዴት | መዝሙረ ዳዊት

❖ ጥቀ ሠነይኪ ወጥቀ አደምኪ አፈቅሮ ለፍግዕኪ ❖
 
     ትርጉም

ወዳጄ ሆይ እንዴት የተዋብሽ ነሽ እንዴትስ ደስ ታሠኛለሽ

      መኃ ም ፯ ቁ ፯
                 7     7

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በአቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሥሮ ለሰይጣን አግዕዞ ለአዳም
ሠላም እምዜይስ
ኮነ ፍስሐ ወስላም

እንኳን ለእናታችን ንፅህት ንፁሃን ቅድስት ቅዱሳን እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ደብረ ምጥማቅ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ አደረስን


ምጥማቅ ማለት መገለጥ ማለት ነው እመቤታችን በግብፅ ገምኑዲ በምትባል ቦታ ለአምስት ቀን ከፀሐይ ፯ እጅ አብራት የተገለጸችበት ቀን ናቸው


ግንቦት ፳፩(21) በዓለ እግዝእትነ ማርያም ወደብረ ምጥማቅ


ዘነግህ ምስባክ

ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኩሎሙ አህዛብ ብዑላነ ምድር ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሥ ሐሴቦን
በዘአዝፉረ ወርቅ ዑጽፍት ወሑብርት

ትርጉም

የምድር ባለጠጎች አህዛብ በፊት ይማላለሉ
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው
ልብስዋ የወርቅ መጎናጸፊያ ነው


         መዝ ፵፪-፲፪
                42  12

ወንጌል

ሉቃ ም ፩ ቁ ፴፱-፶፮
           1     39  56

የቅዳሴ ምንባባት

፩ ቆሮ ም ፯ ቁ ፱-ፍ.ም
ራእ.ዮሐ ም ፲፪ ቁ ፩-፭
  ዓዲ
፩ ጴጥ ም ፪ ቁ ፩-፲፪
ግብ.ሐዋ ም ፯ ቁ ፵፬-፶፩

ምስባክ

ሰወርከኒ በዕለተ ቀትል መልዕልተ ርእስየ
ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን
ተማከሩ ላዕሌየ ወኢትኀድገኒ ከመ አይዘኀሩ

ትርጉም

በሰልፍ ቀን ራሴን ሽፈንህ
አቤቱ ለኃጢአተኞች ምኞት አትሰጠኝ
በላዬ ተማከሩ እንዳይጓደዱ አትተወኝ

    መዝ ፻፴፱፥ ፯
          139    7 

ዓዲ

ምስባክ

ኢትሚጦ ለልብየ ውስተ ነገር እኩይ
ለአመክንዮ ምክንያት ለኀጢአት
ምስለ ሰብእ ገበርተ ዐመፃ

ትርጉም

ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው
ዓመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋራ
ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ

   መዝ ፻፵- ፬
          140  4

ወንጌል

ማቴ ም ፲፰ ቁ ፩-፲፪
            18     1  12

ቅዳሴ

ዘእግዝእትነ

"ወዮ ይህ ነገር ዕፁብ ድንቅ ነው፤የቀደሙ አባቶች ከሞት ወደ ህይወት የተሽጋገሩብሽ ድልድይ ሆይ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርሽ መሰላል ሆይ የፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ በአንቺ ታደሰ "
         ቅዳሴ ማርያም
            ም ፩ ቁ ፴
            1    30

በዓሉን በዓለ ሐሤት በዓለ ምህረት ያደረግልን አባ ህርያቆስ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተለመነች እኛንም በምህረት ተለመነን

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

                  ✧ ምስባክ ✧

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
          
@mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

        ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥