Get Mystery Box with random crypto!

✞ ያሬድ ይኸው ዘመረ ያሬድ ይኸው ዘመረ/4/ ፅናፅኑ ከነ መቋሚያው የያሬድ ነው/2/ ሀሌሉያ ለ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ያሬድ ይኸው ዘመረ

ያሬድ ይኸው ዘመረ/4/
ፅናፅኑ ከነ መቋሚያው የያሬድ ነው/2/

ሀሌሉያ ለአብ ሰማየ ሳረረ
ያሬድ ተገልጦለት አያለ ዘመረ___ፅናፅኑ
እናንተ አእዋፍት___ፅናፅኑ
ከወዴት መጣቹ___ፅናፅኑ
ልብን ይማርካል___ፅናፅኑ
የዜማ ቃላቹ ___ፅናፅኑ
ሚስጢር ሲያቀብሉ___ፅናፅኑ
የልቡ ሲበራ___ፅናፅኑ
እያለ ዘመረ ___ፅናፅኑ
በራ ለደብተራ___ፅናፅኑ

     ያሬድ ይኸው ዘመረ/4/
ድጓ ጽመ-ድጓ እያሰማመረ
ያሬድ ይኸው ዘመረ/4/

ፅናፅኑ ከነ መቋሚያው የያሬድ ነው/2/

ድጓ ጾመ-ድጓ ዝማሬ መዋእስት
ያሬድ ተሰቶታል ምስጋና መላእክት___ፅናፅኑ
ግዕዙም ይነሳ___ፅናፅኑ
እዝልም አራራይ___ፅናፅኑ
ያሬድ በተመስጦ___ፅናፅኑ
ያንተን እንድናይ___ፅናፅኑ
ዛሬም ልጆች አለህ___ፅናፅኑ
አይጠፋም ስራቱ___ፅናፅኑ
ተረክበንሀል___ፅናፅኑ
ከነ ምልክቱ___ፅናፅኑ

ያሬድ መቋሚያን ያዘ /4/
ያባቶቼ ዜማ እንዳይጠፋ አወሳ

ፅናፅኑ ከነ መቋሚያው የያሬድ ነው/2/

አፄ ገብረ-መስቀል ሲወጋ በጦሩ
ምነው ያልተሰማው ምንድ ነው ሚስጢሩ___ፅናፅኑ
ከቤተመንግስቱ___ፅናፅኑ
ከንጉሱ እልፍኝ___ፅናፅኑ
ያሬድ በተመስጦ___ፅናፅኑ
ሲያስረግጥ ሲቀኝ___ፅናፅኑ
ደሙ እየፈሰሰ___ፅናፅኑ
እግሩ ላይ ተወግቶ___ፅናፅኑ
ይዘምር ነበረ___ፅናፅኑ
እራሱን እረስቶ___ፅናፅኑ

ያሬድ ከበሮ ምታ/4/
በዝማሬ ሚስጢር እስራት ይፈታ

ያሬድ ከበሮ ምታ/4/
ፅናፅኑ ከነ መቋሚያው የያሬድ ነው/2/

የድጓ መጋቢ የዜማ አባት
ዛሬም በመቅደሱ አሉ ሊቃውንት___ፅናፅኑ
ማህሌተ ጽጌ___ፅናፅኑ
ስንቆም ከመቅደሱ___ፅናፅኑ
የያሬድ በረከት___ፅናፅኑ
ይራባል መንፈሱ___ፅናፅኑ
ክበበ ጌራ ወርቅ___ፅናፅኑ
ወረቡ ሲቃኝ___ፅናፅኑ
የማህሌቱ ዜማ___ፅናፅኑ
ትዝታ አለብኝ___ፅናፅኑ

ያሬድ ስምህ ይወሳ /4/
ምንጩ እንተነህና ትውልድ እንዳይ ረሳህ

ያሬድ ስምህ ይወሳ /4/
ምንጩ እንተነህና ትውልድ እንዳይ ረሳህ
ያሬድ ስምህ ይወደስ/2/
ያሬድ ስምህ ይወሳ/2/
ያሬድ መቋሚያን አንሳ/2/
ያሬድ ፅናፅን አንሳ/2/
ያሬድ ድጓውን አንሳ/2/
ያሬድ ከበሮን አንሳ/2/
ያሬድ ቅኔው ይነሳ/2/

ያሬድ ስምህ ይወሳ/2/

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

    ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
    ✥       @mezmurochh    ✥
    ✥       @mezmurochh    ✥
    ✥       @mezmurochh    ✥
    ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

   ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥