Get Mystery Box with random crypto!

✞ በአምሳሉ ለሰራኝ በአምሳሉ ለሰራኝ ለቅድስት ሥላሴ በአርአያው ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ እገዛለታ | መዝሙረ ዳዊት

✞ በአምሳሉ ለሰራኝ

በአምሳሉ ለሰራኝ ለቅድስት ሥላሴ
በአርአያው ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ
እገዛለታለሁ በሥጋ በነፍሴ


ከድንኳኔ ገብቶ በቸርነት ያየኝ
ከአገር ከወገን ከዘመድ የለየኝ
ስሙን ሊያሸክመኝ ስሜን የቀየረው ዘሬን እንደ አሸዋ ያበዛው እርሱ ነው
         "ቅድስት ሥላሴ"
     
አዝ_______

ስሙን እንድቀድስ ክብሩን እንድወርስ
እፍ ብሎብኛል የሕይወት እስትንፋስ
ከፍጥረቱ ሁሉ አልቆኛል ሠርቶ
መንግሥቱን እንድወርሥ ሕያውነት ሠጥቶ
        "ቅድስት ሥላሴ"
     
አዝ_______

ገና ሳልፈጠር ጀምሮ የሚያውቀኝ
በበረከት አድሮ ነገን የሚያይልኝ በእርሱ ነው መቆሜ በእርሱ ነው
መኖሬ ትናንትን አልፌ መድረሴ ለዛሬ
        "ቅድስት ሥላሴ"
      
አዝ_______

በከሃሊነቱ ያመጣኝ ከምድር ከፍጥረት ለይቶ የሠራኝ ለክብር የሚመሰገን ነው በአንድነት ሦስትነት  እግዚአብሔር እርሱ ነው አምላከ አማልክት
       "ቅድስት ሥላሴ"

                   መዝሙር
  ሊቀ_መዘምራን ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥  @mezmurochh ✥
   ✥  @mezmurochh ✥
   ✥  @mezmurochh ✥
  ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

     ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥