Get Mystery Box with random crypto!

✞ ትምክህቴ መዳኒቴ ትምክህቴ መዳኒቴ አንቺው ነሽ 2 እመብርሀን 4 ምርኩዛችን ሸክም የከበደኝ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ትምክህቴ መዳኒቴ

ትምክህቴ መዳኒቴ አንቺው ነሽ 2
እመብርሀን 4 ምርኩዛችን

ሸክም የከበደኝ ደካማነኘ እኔ
እረዳትም የለኝ ከአንቺ በቀር ለእኔ
እመአምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ
እመብርሀን 4 ምርኩዛችን

አዝ-------------

የአጢያትን ቋጥኝ በጀርባዬ አዝዬ
እቅበዘበዛለው ተገፎ ፀጋዬ
በአንቺ እማፀናለው ነፍሴን በእጅሽ ጥዬ
ምርኩዝ መሰላሌ ጥላ ከለላዬ
እመብርሀን 4 ምርኩዛችን

አዝ-------------

ልዩ ነሽ እናቴ ማርያም ድንግል
ማን አዛኝ እዳንቺ ግራ ቀኝ ቢባል
በአንቺ ላይ አረፈ ልቤ ተረጋጋ
የሕይወቴ ተስፋ በአንቺ ተዘረጋ
እመብርሀን 4 ምርኩዛችን

አዝ-------------

ፈፅሞ አርቂልኝ የኔን ክፉ ሽታ
በሽቶሽ መአዛ አድይኝ እርካታ
የኪሩቤል አክናፍ የነፍሴ ዋስትና
ነይነይ እመቤቴ ምርኩዜ ነሽና
እመብርሀን 4 ምርኩዛችን

አዝ-------------

በፍቅርሽ ምስጋና ዝም እንዳልል ድንግል
አደበቴን ፍችው ህሊናዬም ይቁሰል
የፍቅርሽ መአዛ ይፍሰስ በህይወቴ
በእቅፍሽ አድርጊኝ እንደልጅነቴ
እመብርሀን 4 ምርኩዛችን


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥      @mezmurochh     ✥
   ✥      @mezmurochh     ✥
   ✥      @mezmurochh     ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥