Get Mystery Box with random crypto!

✞ ስምሽን_ስጠራው ስምሽን ስጠራው ድንግል ስምሽን ስጠራው ማርያም ላንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ስምሽን_ስጠራው

ስምሽን ስጠራው ድንግል
ስምሽን ስጠራው ማርያም
ላንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላም
ስምሽን ስጠራው ማርያም

ትውልድ ነኝና ልጅሽ የፈጠረኝ
ድንግል እመቤቴ ላንቺ ምስጋና አለኝ
በፈቃደ እግዚአብሔር ባባቶቼ ፀጋ
ሳዓሊ ለነ እላለው ሲመሽም ሲነጋ

አዝ___

በጠየቅሽው ጊዜ ወይኑን እንዲመላ
አክብሮሻልና በቃና ገሊላ
የሰላም እናት ሆይ ሰላም ልበልሽ
ዘመኔ ይፈፀም ሳመሰግንሽ

አዝ__

በሰላምታ ድምፅሽ መንፈስ ተመልቼ
አደግድጌ ልቁም እጆቼን ዘርግቼ
በአብይ ቃል ጮሄ ልመስክር በብርቱ
ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናቱ

አዝ__

ከሰማይ ሲገኝ ነው አንችን ማወደስ
ሲገለጥ ሲፈቀድ ከመንፈስ ቅዱስ
ማርያም ህይወቴ ነሽ ምክንያት ለመዳኔ
ብዙ ነው ምስጢሩ አንችን ማመስገኔ

መዝሙር
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

   ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
   ✥      @mezmurochh     ✥
   ✥      @mezmurochh     ✥
   ✥      @mezmurochh     ✥
   ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥