Get Mystery Box with random crypto!

✞ ሰማዕታት መስተጋድላን       ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/2/ ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያ | መዝሙረ ዳዊት

✞ ሰማዕታት መስተጋድላን
     
ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/2/
ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያን /4/

በምድር ሊቪያ ተጣራ እየሱስ
በተዋህዶ ልጆች ስሙ እንዲ ቀደስ
ኢየሱስ አምላክ ነው እያሉ በፅናት
መንግስተ ሰማይን ህፃናት ተሻሟት /2/
    ከዋክብት ለቤተክርስቲያን /4/

በመከራ ጊዜ ሚዛን ላይ ወታቹ
በክርስቶስ ፀጋ እንደ እንቁ አበራቹ
እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ሰይፍን ሳትፈሩ
እግዚአብሔር ይመስገን በቃቹ ለክብሩ /2/
   ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/2/

እዮ ሲያንገላቱ ሲያዳፉት ጨክነው
ምንም አልቀመሰም ወንድሜ ፆሙን ነው
ግን እንደ ሰርገኛ በደስታ ይጓዛል
በሰይፍ ፊት ቆሞ ለወንጌሉ ታምንዋል
መከራውን ንቆ ለወንጌሉ ታምንዋል
     ሰዓሉ ለነ ሰዕማታት መስተጋድላን/4/

ግርፋቱን ይስሙ መታረዱን ደግሞ
ከክርስቶስ ፍቅር እኛ የሚለየን
ያመለክ ነው አምላክ የእውነት ስለሆነ
ለክብር ተፋጠኑ ልባቸው ጨከነ /2/
      ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያን/4/


የዋልዮሽ ታስረው እንደ በግ ሲነዱ
ይመስሉ ነበረ ለሰርግ የሚሄዱ
በጉድጓድ ተከተው ለቀናት ቢራብ
በውሃ ጥም ዝለው አልተለዋውሱም/2
       ሰዓሉ ለነ ሰማዕታት መስተጋድላን/2/
       ከዋክብት ለቤተ-ክርስቲያን/4/


ገዳይወች ድል ሆኑ ሙታን ሆኑ እነሱ
የተዋህዶ ልጆች በድል ገሰገሱ
በደማቸው ፀዳል አለምን ቀየሩ
የኢትዮጵያ ከዋክብት በሊቪያ አበሩ
የኢትዮጵያ ከዋክብት በዓለም አበሩ
      ከዋክብት ለቤተ-ክርስትያን/2/

                       ዘማሪ
         ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሃይሉ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮
   ✥
@mezmurochh    ✥
   ✥
@mezmurochh    ✥
   ✥
@mezmurochh    ✥
   ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥