Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ የትንሳኤ መዝሙር በ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው ✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ ትንሳኤከ ለእለ አመ | መዝሙረ ዳዊት

አዲስ የትንሳኤ መዝሙር በ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው

✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ

ትንሳኤከ ለእለ አመነ
ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/

የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት
ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት
በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው
አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው

በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__________________

የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል
የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል
የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን
ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን

በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__________________

ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ
በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ
መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል
የነገራችሁን እዩተሰ ተፈፅሟል

በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__________________

የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ
በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ
እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው
በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው

በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/

አዝ__________________

ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ
ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ
እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ
ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ

በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን
የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/

ዘማሪ
በሱፍቃድ አንዳርጋቸው

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
✥ @mezmurochh ✥
╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥