Get Mystery Box with random crypto!

✞ ኃያል ነው እግዚአብሔር ኃያል ነው እግዚአብሔር ኃያል ነው ቅዱሱ ኃያል ነው ንጉሱ አይቻለው | መዝሙረ ዳዊት

✞ ኃያል ነው እግዚአብሔር

ኃያል ነው እግዚአብሔር
ኃያል ነው ቅዱሱ ኃያል ነው ንጉሱ
አይቻለው ባይኔ ሲቆም ማእበሉ
አይቻለው በአይኔ ሲታዘዝ ንፋሱ


ሰረገላውን በእሳት ሰርቶታል
በደመና ላይ ይረማመዳል
የብርሃን ድንኮን በሰማይ ያለው
እሱ ነው ጌታ የምናመልከው/2/

አዝ______

እውነት በፊቱ ፍትህ በእጁ
ሲኦልም ገነት አሉ በደጁ
ስልጣን የሱ ነው አለቀነት
ማን እንደ ጌታ ከአማልክት/2/

አዝ______

ታቦር ተራራ ተንቀጠቀጠ
ግርማው ሲገለጥ ሁሉ ቀለጠ
ድንቅን አድራጊ ተአምረኛ
ከማዳኑጋር ይምጣ ወደኛ/2/

አዝ______

ምድር ጠፈሩ ታዟል ለእሱ
እሳት ተፈትሎ ሆኖል ቀሚሱ
የልብ ብርሀን ይብራ በልቤ
አንተነህ ለኔ ውድ ገንዘቤ/2/

                   ዘማሪ
      ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

  መዝሙረ ዳዊት

              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
           @mezmurochh    
              |❀:✧๑ ✞✞ ๑✧❀|:

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥