✞ ገብርኤል መልአከ ራማ ገብርኤል (፪) ገብርኤል መልአከ ራማ (፪) ስንጠራህ ፈጥነህ ድረስ ድምጽህን እናስማ ትንቢቱ ሲፈጸም ዘመኑ ሲያበቃ ከቀናት ሳትዘግይ ሳይጎድል ደቂቃ ወደ ድንግል መጥተህ ደስታን አበሰርክ የአምላክን ሰውን መሆን ለአለሙ ሰበክ(፪) አዝ___ ከውኃ እና ከሳት ከሞት አመለጡ በእሳቱ መካከል ለጥፋት ቢሰጡ አንተ ባለህበት በየትኛውም ስፍራ ምንም ቦታ የለውም ሞትና መከራ(፪) አዝ___ የመንገድ መሪ ፈውስ ነህ ለህመሜ ገብርኤል ስትመጣ በዛልኝ ሰላሜ ደስታን አብሳሪ ተሸክመህ ዜና ዛሬም ለአገራችን ምስራች ይዘህ ና(፪) አዝ___ አንጌቤናይቱ ቅድስት እየሉጣ ስለአንተ ትመስክር እስከ ልጇ ትምጣ እሳተ ነህ ገብርኤል ነባልባልባ አስወጋጅ የአምላክ መወለድ ለአለም ምታውጅ(፪) ዘማሪ ለዲያቆን አቤል መክብብ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|: ══╮ ✥ @mezmurochh ✥ ✥ @mezmurochh ✥ ✥ @mezmurochh ✥ ╰══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ 1.9K views••●◉ Estifanos ◉●••, 16:41