Get Mystery Box with random crypto!

💜 ...ማርያምን ...🕯

የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmure_tewahdo — 💜 ...ማርያምን ...🕯 ማ
የቴሌግራም ቻናል አርማ mezmure_tewahdo — 💜 ...ማርያምን ...🕯
የሰርጥ አድራሻ: @mezmure_tewahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.85K
የሰርጥ መግለጫ

/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮን
የጠበቁ መዝሙሮች ና የቅዱሳን ገድል
ይገኙበታል
"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"
''የቅዱሳንን ክብራቸውን እናገር ዘንድ ፍቅር ያስገድደኛል''
✍️ግሩፑ ላይ መዝሙር ብቻ አይደለም
የተለያዩ ነገሮችንም ታገኙበታላችሁ
🙏 ኑ በጋራ ሁነን እንማር
👇
❷❶ ማርያም ሆይ እኖድሻለን
ለማንኛውም አስተያየትና ሀሳብ
@joni_21_27
👆👆

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-21 21:46:08
ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ።
#እመቤቴ_ማርያም_ሆይ_በቅዱስ_ሔሬኔዎ

"የህይወት እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትንሳኤሽ ሳይሆን ሞትሽ ይደንቀኛል፤ እርገትሽ ሳይሆን ወደመቃብር መውረድሽ ይገርመኛል፤ የብርሃን እናት ድንግል ማርያም ሆይ ትወጂኛለሽን? ብየ አልጠይቅሽም ፡...ፍቅርን የወለድሽ አንቺ ለአለሙ ሁሉ ፍቅርሽ የበዛ ነውና ፤ አትናፍቂኝምን? ብየም አልጠይቅሽም ፡ ዘወትር እኔን ለመጠበቅ ከጎኔ እንደማትለይ አውቃለሁኝና ፤

ሆኖም እመቤቴ ሆይ ፦እንደ ቶማስ አይሽ ዘንድ በእጅጉ እጓጓለሁ ፡ የቶማስ ንፅህናና ቅድስና ግን የለኝም ፡ እንደ ዮሐንስ ከጎንሽ ልሆን እጓጓለሁ ፡ የዮሐንስ ፀጋ ግን የለኝም ፤ እናቴ ሆይ ፦እንደኤልሳ የልቦናየ አይን በርቶ ሰማያዊ ክብርሽን ላይ አልተቻለኝምና አዝናለሁ ኤልሳ በፀሎት ሃይል የግያዝን አይን እንዳበራ አንቺም አይኔን ታበሪልኝ ዘንድ ሃይልሽን በእኔ ላይ አበርቺ፡፡

ድንግል ሆይ ፦ ይህን የምል የእምነት ማረጋገጫ ፈልጌ አይደለም ፡ በልጅሽ መሰረትነት የታነፅኩኝ፡ በልጅሽ ስምም የተጠመቅኩኝ ነኝና ፤ ነገር ግን ስለምትናፍቂኝ ይህን አልኩኝ ፦ ስለዚህም ፦ ነይ ነይ እምየ ማርያም እያልኩኝ እንደእናቶቼም እለምንሻለሁ፡፡

የብርሃን ልብስሽን ለብሰሽ ነይ ፡የክብር አክሊልሽን ደፍተሽ ነይ ፡ አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ነይ ፡ እናይሽ ዘንድ ነይ፡፡ መኃ.4:10፤ እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ! በእዉነት እጅግ የተሻለ ነው።


በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ


#ሼር_አርጉ_እባካችሁ

ለመቀላቀል
@Mezmur_tewahdo
@Mezmur_tewahdo

ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ
1.2K views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:30:16

ሥርዓተ ማኅሌት ዘነሐሴ ፲፮ በዓለ ቅድስት ኪዳነምህረት




ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ፦
ወታስተሥርዩ ኃጥያተ ህዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኲኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኃኒተ ኩሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት

ነግስ፦
እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳከዊሁ ብርሃን፤ አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤ ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤ እመቅድሐ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን ወውስቴታ ተሠርዓ ቁርባን።

ዚቅ፦
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል፤ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፤ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጉላት፤ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፤ እንተ ሠረፀት ለሕይወት።

መልክዓ ኪዳነምህረት፦
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ዘተሐደሰ፤ እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤ ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቁዓኪ አንሰ፤ ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚዓየ ነፍሰ፤ እስመ በሥራያ ይዕቲ ቀብዓተኒ ፈውሰ።

ዚቅ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ፤ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፤ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፤ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።

ወረብ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ/፪/
በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፣እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፣ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ፣ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፣ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፤ወልድኪ ይጼዉዓኪ፤ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር።

ወረብ፦
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት/፪/
"ወልድኪ"/፪/ይጼዉዓኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር/፪/

መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለእስትፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት፤ከመ መዓዛ ዕፀ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፤ ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት

ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኵሉ ነገራ በሰላም


ወረብ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ/፪/
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል/፬/


መልክዓ ፍልሰታ
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤ ወዘኢይነጸፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤ ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤ ማርያምሰ በምድር ታንሶሱ።

ዚቅ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ማሕደረ መለኮት፤እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ፤ ሰማያዊት እንተ በምድር ታንሶሱ

አመላለስ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት/፪/
ጽርሕ ንጽሕት ማሕደረ መለኮት/፪/

ምልጣን፦
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር፤ኀደረ ላዕሌሃ፤ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፤ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ

አመላለስ፦
ፀቃውዕ ይውኅዝ/፪/
ይውኅዝ እምከናፍሪሃ/፬/


ወረብ፦
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ/፪/
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ/፪/



እስመ ለዓለም ፦
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት፤እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ እምወይን፤ መዓዛ ዕፍረትኪ እምኲሉ አፈው፤እትፌሳሕ ወእትሐሠይ ብኪ፤ናፍቅር አጥባትኪ እምወይን፤ርቱዕ አፍቅሮትኪ ኵለንታኪ ሠናይት እንተ እምኃቤየ፤ማ፦ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ፤ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት።

አመላለስ፦
አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ/፪/
ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት/፬/


ወረብ፦
"በአልባሰ ወርቅ"/፪/ዑፅፍት ወኁብርት/፪/
እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ/፪/


ሰላም፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኵሉ ነገራ በሰላም


#ሼር_አርጉ_እባካችሁ

ለመቀላቀል
@Mezmur_tewahdo
@Mezmur_tewahdo

ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ
1.2K views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:55:59 .
1.1K views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:35:31 የአባ ዘወንጌል የትንቢት እውነታዎች
የኖኅ መርከብ መድረሻ
የትንቢቱ ፍፃሜዎች
የ666 ደባ በኢትዮጵያ ላይ
,መጽመፈ ሔኖክ
የዕፀ መሰወር ጥናታዊ ፁፍ
ታቦተ ፅዮን
ነጋዴው ታምሪን

open.........open .........open
Open........"open .........open
Open.........open...........open
Open........open............open

እርሶም በዚህ ዙሪያ እውቀቱ እንዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።
"ትምህርቱን በናታኒም ቲዩብ ይከታተሉ"።


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘

የተወደዳችሁ የተዋሕዶ ልጆች ዛሬ የማስተዋውቃችሁ ናታኒም ቲዩብን ነው! በናታኑም ቲዩብ የተለያዩ የአውደ ምሕረት ትምህርቶችን፣ስብከቶችን እንዲሁም ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬዎችን የምታገኙበት መንፈሳዊ ቻናል ስለሆነም ሰብስክራይብ በማድረግ መንፈሳዊ ሕይወታችሁን የበለጠ እንድታጎለብቱ በቅድስት ቤተክርስቲያን ስም እጠይቃችኋለሁ ።
ናታኒም ቲዩብ ሼር ሰብስክራይብ አድረጋችሁ ቻናላችናን ተቀላቀሉ "
ሰብስክራይብ ሼር ያድርጉ




















ኦርቶዶክሳዊ ህይወት
የነፍሴ ጥያቄዎች
ማህተቤ ክብሬ ነው
ናታኒም ቲዩብ
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌

█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN ▒▓█
151 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:08:50 ✞ምን ሰማህ ዮሐንስ✞

ምን ሰማህ ዮሐንስ /በማህጸን ሳለህ /(፪)
ህፃን ሆነህ ነቢይ /ለክብር የተጠራህ /(፪)
እንደ እንቦሳ ጥጃ/ያዘለለህ ደስታ/(፪)
ምን አይነት ድምፅ ነው/ምን አይነት ሰላምታ/(፪)

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው/የእናታችን ፍቅር /(፪)
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና /የሰላምታ ቃሏ /(2)
አዝ= = = = =
በረሃ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴን/ያለ ብሥራት/(፪)
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ/ጭራሽ ያልታሰበ /(፪)
አዝ= = = = =
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ /በሕይወቱ ፍጹም/(፪)
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ/የኪዳን ሰላምታ/(፪)

መዝሙር
ይልማ ኃይሉ

"...እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።..."
ሉቃ ፩፥፵፬


•➢ ሼር // SHARE

@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo
417 views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 06:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:04:39 በልደቱ በእድገቱ በሕይወቱ በሞቱ በቃልኪዳኑ ወንጌልን የሰበከ
ጻድቅ
ሰማዕት
ነቢይ
ሐዋርያ
ባሕታዊ
ድንግል
ካህን
ከዚሁ ሁሉ በላይ መጥምቀ መለኮት የሆነ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኔ_30 ዓመታዊ የልደቱ ክብረ በዓል ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን በረከቱ ይደርብን።
ዮሐንስ የጌታውን ስም አክብሮ ሰበከ እንዲህም አለ
የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር :;በእሳት የሚያጠምቀው መንሹ በእጅ የሆነ ዓሣየ ሕይወት አቡሃ ለምሕረት ኪነኔ በርትዕ ምሳር ቀዳማዊ አምላክ ከእኔ በፊት የነበረ ደኃራዊ አምላክ ከእኔ በኋላ የሚመጣው የቤተክርስቲያን ሙሽራ አካላዊ ቃል ሠራየ ኃጢአት ደምሳሴ አበሳ የዓለሙን ኃጢአት የሚያሶግድ የእግዚአብሔር በግ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሞል።ጌታም ዮሐንስን መልአክ ብሎታል።
ንዋይ ሕሩይ ቅዱስ ጳውሎስ እርሾዋ ቅድስት የሆነች ቡሆውም እንዲሁ ቅዱስ ነው። ሥርዋ እንዲሁ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው። ሮሜ 11:16,
እናት አባት ከጠመሙ ትውልድ ይጠማል ካላወቁ ይደነቁራል ከካዱ ይክዳል።አበው እንዳሉት ነገር ግን ሁለቱም በጌታ ትእዛዝና ሕግጋት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየሄዱ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ።"
(የሉቃስ ወንጌል 1:6እርሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ዘካርያስን እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ እንዲህ ብሎ ጠርቶቸዋል።
ዘካርያስ ካህኑ በእግዚአብሔር ፊት የጸደቀ ንጽህ ካህን ነው ።ጸሎቱ የተሰማለት ባለሟል ነበር።ሰው ሆኖ መላዕክን የወለደ ካህን ነበረ ።እናቱ ቅድስት ኤሌሳቤትም ቧሏ ካህን ሲባል እርሷ ግን ከአሮን ወገን ሆነች።ኤልሳቤጥ ካህን ባትሆንም ከካህናት ወገን እንደሆነች ምዕመናንም ክህነት ባይኖራቸውም ከካህናት በሃይማኖት በምግባር በንስሐ መወለዳቸው የካህናት ወገን መሆናቸውን በተግባር አሳይተናለች። በሰው ፊት ሳይሆን በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ መገኘት ከምንም በላይ መባረክ ነው"ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ከሚያሰደንቀው ገድላቸው ምንም ነውር የሌለበቸው መሆናቸ ነው።ሕግ ባለመሻር ሕግን በመጠበቃቸው ።ሰው ነውረኛ የሚባለው ሕግ ነውር ያለውን በማድረግና ሕግ ጽድቅ ያለውን በማጉደል ነው።ሁለቱ ባልና ሚስት ግን ያለ ነቀፌታ ቅዱሳን ነበሩ በእግዚአብሔር ፊት ነው ተባለላቸው ይሔ ልዩ ያደርጋቸዋል።
ዮሐንስ በምድር እየኖረ በሰማያውያን መላእክት ሥርዓት የኖረ ከሕግ በላይ ነው።ቅዱስ ያሬድ ከነቢያት ማን ይበልጣል?ስሙ ዮሐንስ የተባለ እርሱ ነው የሚበልጠው ከእናቱ ማኅፀን መላእክ እንደሰየመው እርሱ በደስታ በሰላም በክብር ይመጣል የተባለለት ዮሐንስ ነቢይ
በዚህ በተቀደሰ ቤት ውስጥ ደግሞ
እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ በቅዱስ ገብርኤል ቃል አመስግናለች የሰላምታሽን ድምጽ በሰማሁ ጊዜ ጽንሱ በማኅፀኔ ዘለለ አለቻት በዕርግጥም ዮሐንስ የዓለሙ ሁሉ ሰላም አካላዊ ቃል በእርሷ አድሮ ሰላምን ይሰጠናልና ስለዚህ ነው ዮሐንስን ያዘለለው ይህ ቃል በእናቱ አድሮ የሚናገረው አካላዊ ቃል በእናቱ ማኅፀን ያለውን የአዋጅ ነጋሪ ድምፅ አዘልሎታል እና ነው። ሐዋሪያትን መስማት ጌታን መስማት ከሆነ እናቱን እንደምን ያለ ጌታን ማዳመጥ ይሆን?

ይህቺ የደስታ መፍሰሻ ፤ የደስታችንም እናት እመ ብርሃንን ተመልከታት ፤ ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ ትልሃለች፡፡ ጨንቆህ እንደሆነ በጸነሰችው ደስታ እንደ ኤልሳቤጥ ደስ ታሰኝሃለች:: ደስታን በውስጥዋ ይዛ እንደ ዮሐንስ በደስታ ታዘልልሃለች:: እመነኝ ከዚያ በኁላ ደስ ይበልሽ ባልካት ደስ እያለህ "ተፈስሒ ማርያም" (ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ) ስትል ትውላለህ!
ከመጥምቁ ረድኤት በረከት ያሳትፈን።


•➢ ሼር // SHARE

@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo
365 views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:03:42 "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"

ሰኔ ፴ (30) ቀን።

እንኳን ለነቢዩ ለሰማዕቱ ለካህኑ ለሐዋርያው ለመጥምቀ መለኮት ለተወለደበት (ለልደት) በዓልና በሕንደኬ ካሉ ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ ለአባ ጌራን ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ማርያና፣ ከማርታ፣ ከመነኰስ ገብረ ክርስቶስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

+ + +
የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ሰምዑ አዝማዲሃ ወሰብአ ቤታ። እስመ አዕበየ እግዚአብሔር ሣህሎ ላዕሌሃ። ወተፈሥሁ ፍሥሃ ፈድፋደ። ወፈቀዱ ይስምይዎ በስመ አቡሁ ዘካርያስ። ወትቤ እሙ ዮሐንስሃ ይሰመይ"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።

+ + +
ነቢይ፣ ሰማዕትና ሐዋርያ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ልደት፦ ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው።

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው። በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን "አይሆንም ዮሐንስ ይባል" አለች። "ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም" አሏት።

አባቱንም ጠቅሰው "ማን ሊባል ትወዳለህ" አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ "ዮሐንስ ይባል" ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው። ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ሰብአ ሰገልም መጥተው ከሔዱ በኋላ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ስለ ሕፃኑ ዮሐንስ ለሄሮድስ ነገሩት እንዲገድሉትም ጭፍሮችን ላከ ጭፍሮችም ወደ አባቱ ዘካርያስ መጡ ሕፃኑንም ከእርሱ ፈለጉት አባቱም አንሥቶ በትከሻዎቹ ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ ከእርሱ ጋራ እንዲሔዱና ሕፃኑን ከዚያ እንዲወስዱት ወታደሮችን ለመናቸው።

ከዚህም በኋላ ሕፃኑን በመሠዊያው ጠርዝ ላይ አኖረውና "ከዚህ ራሳችሁ ተቀብላችሁ ውሰዱት" አላቸው ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መልአክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው። ጭፍሮችም ባላገኙት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት። ሕፃኑ ግን አድጎ ለእስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በበረሀ ውስጥ ኖረ።

"የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ ጥርጊያውንም አስተካክሉ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ የዐዋጅ ነጋሪ ድምጽ እነሆ" ብሎ ኢያሳያስ የተናገረለት ይህ ነው። ሚልክያስም ስለርሱ እንዲህ አለ "በፊትህ ጎዳናዬን አስተካክሎ የሚጠርግ መልአክተኛዬን እኔ እሰዳለሁ"።

ራሱ መድኃኒታችንም ስርሱ ሲናገር "ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም" ብሏል። ይህ የእግዚአብሔር ልጅ በአጠመቀውና የማትዳሠሥ ራሱን በዳሠሠው ጊዜ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል የአብን ቃል ሰምቷልና።

ዳግመኛም ክብር ይግባውና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ሲቀመጥ አየ። እኛንም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ የመጥምቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ በረከቱም እኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

+ + +
ገድለኛው የሆነ አባ ጌራን፦ ይህም ቅዱስ በሕንደኬ ካሉ ደሴቶች በአንዲቱ ውስጥ የሚኖር ነው። እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚወደው ጾምና ጸሎትንም የሚወድ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም የሚለምነውን ሁሉ ይሰማው ነበር። በጸሎቱም ከዚያች አገር ንዳድ፣ አባር፣ ድርቅ፣ በጠላት መማረክ፣ የደም መፍሰስና የመርከቦች መሥጠም ተወገደ የፈለገውንም ሁሉ በጸሎቱ ያገኝ ነበር።

ሰይጣንም ስለዚህ ስለ ተሰጠው ጸጋ ቀናበት በዕንቊ ያጌጠ ነገሥታትን ልብስ በለበሰች መልከ መልካም ሴት አምሳልም ታየው እርሷም ብቻዋን ትንጎራደድ ነበር። በአያትም ጊዜ ወደርሷ ሒዶ ሥራዋን ጠየቃት እርሷም እንዲህ አለችው "የንጉሥ ሰርስባን ልጅ ነኝ እኅቴ ከአባቷ ባሮች ጋራ በአመነዘረች ጊዜ ሁላችንንም ሊገድለን ፈለገ። ስለዚህ ፈርቼ በሌሊት ወጣሁ ወደዚች በረሀም መጣሁ ቅዱሱን ሰው አንተን በማግኘቴም እድለኛ ነኝ" አለችው። እርሱም "ወደ እኔ የሚመጡ ሰዎች እንዳያዩሽ ወደዚያች የዐለት ዋሻ ሒጂ" አላት።

በሌሊትም ከአራዊት የተነሣ እንደፈራ ሰው እየጮኸች መጥታ "የዱር አራዊት እንዳይበሉኝ ክፈትልኝ" አለችው። እርሱም ከፈተላትና ገባች በጎኑም ተኝታ ደረቱን አቀፈችው ልቡን ወደ ፍቅርዋ እስከ አዘነበለችው ድረስ ነገሯን አለሰለሰችለት። ያን ጊዜ ያደረበት የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተለየው ከእርሷም ጋራ ተኝቶ ኃጢአት እደሚሠራ ሆነ። ከስህተት ስካርም በነቃ ጊዜ በጠላት ሰይጣን ተንኰል ተሸንፎ እንደ በደለ አወቀ።

ከዚህም በኋላ ከሰይጣን ተንኰል የተነሣ ያገኘውን ሁሉ በሥጋውም ኃጢአት እንደሠራ ጻፈ። ከዚህ በኋላም ከደሴቱ ተራራ ድንጊያ አንሥቶ እስከሚሞት ድረስ ራሱንና ደረቱን እየደበደበ ኖረ። ነፍሱም ድና ወደ ዘላለም ሕይወት በጌታ ቸርነት ገባች።

ከዚህም በኋላ እንደ ልማዳቸው ከእርሱ ቡራኬ ሊቀበሉ ሰዎች መጥተው አላገኙትም በፈለጉትም ጊዜ ተኝቶ አገኙትና ያንቀላፋ መስሏቸው ጀምሩ ግን ሞቶ አገኙት አለቀሱለት ተሳለሙት ገንዘውም ቀበሩት።

ከዚህም በኋላ ሞቱ በጠላት ሰይጣን ተንኮል ምክንያት ስለመሆኑ የጻፈውን አገኙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ጸሎት መንፈሳውያን በሆኑ በቅዱሳን መላእክትም አማላጅነት ይልቁንም አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጸሎቷና በአማላጅነቷ ከሰይጣን ወጥመድ ያድነን።

የተባረ የሰኔ ወር በእግዚአብሔር ቸርነት ተፈጸመ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 30ስንክሳር።


+ + +
"ሰላም ለዮሐንስ ግፋዕ ወቅቱል ንጹሕ ወቅዱስ ወስቡሕ ላእክ ወነቢይ ወሰማዕት ድንግል ካህን ጸያሒ ወሰባኪ መጥምቀ እግዚኡ"። ትርጉም፦ ጌታውን ያጠመቀና ሰባኪ፤ መንገድ ጠራጊ፣ ካህን ድንግል ሰማዕት፣ ነቢይና አገልጋይ፤ ምስጉን ቅዱስና ንጹሕ፤ ተገፍቶ የተገደለ ለኾነ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።


+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አሜሃ ይቤሉ አሕዛብ። አዕበየ ገቢረ ሎሙ እግዚአብሔር። ወኮነ ፍሡሓነ። መዝ 125፥2፥3። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥76-ፍ.ም።


•➢ ሼር // SHARE

@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo
330 views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 04:47:41 እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም
አደረሳችሁ፣ አደረሰን።
ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ
የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን
የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል::
"ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ
የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
+የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ
አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ
ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ
90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ
ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት
(ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት
ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
+ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን
መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር
የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ
ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
+የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ
ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ
(ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ በዚህች ቀን (ሰኔ 30) ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ
"ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
=>መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ
+የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ
+በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
+በበርኀ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
+እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
+የጌታችንን መንገድ የጠረገ
+ጌታውን ያጠመቀና
+ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን ነቢይ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ጻድቅ: ገዳማዊ:
መጥምቀ መለኮት: ጸያሔ ፍኖት: ቃለ ዐዋዲ ብላ ታከብረዋለች::
ደግሞም አንተ ሕጻን ሆይ የልዑል ነቢይ ትባላለህ:: መንገዱን ልትጠርግ
በጌታ ፊት ትሔዳለህና:: እንደዚህም የኃጢአታቸው ስርየት የሆነውን የመዳን
እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ:: ይሕም ከላይ የመጣ ብርሃን በጐበኘበት
በአምላካችን ምሕረትና ርኅራኄ ምክንያት ነው:: (ሉቃ. 1:76)
< ወስብሐት ለእግዚአብሔር > የአመት ሰው ይበለን አሜን


•➢ ሼር // SHARE

@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo
489 views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 01:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 12:43:57 #የምትፈልጉትን_የመዝሙር

#ግጥም_እና_ዜማ

#እንድልክላችሁ_በ_comment_ላይ_አሳውቁኝ
568 views 𝐉𝐨𝐧𝐢....... , 09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ