Get Mystery Box with random crypto!

#በጎ_መአዛ በጎ መአዛ ሽቶዬ ነሽ በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ ባንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ እጠራሻለሁ | 💜 ...ማርያምን ...🕯

#በጎ_መአዛ
በጎ መአዛ ሽቶዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
ባንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
#አዝ
ምሳሌ የሌለሽ ነይ እመቤቴ
ዘመዴነሽ " ""
ያን ክፉ ዘመን " ""
ያለፍኩብሽ " ""
በፍቅርሽ እሳት " ""
ልቤ ነደደ " ""
እናትነትሽን " ""
ስለወደደ " ""
#አዝማች
የሰውስ ጉልበት ነይ እመቤቴ
ምን ይረባኛል " ""
ሰረገላዬስ " ""
መች ያድነኛል " ""
ከተሠወረ " ""
ክፉ መከራ " ""
እድናለሁኝ " ""
አንችን ስጠራ " ""
#አዝማች
ለስንፍናዬስ ነይ እመቤቴ
መቼ ልክ አለው " ""
ስለበደሌ " ""
እተክዛለሁ " ""
ላነጋገሬ " ""
ማጣፈጫ ነሽ " ""
ተሰምቻለሁ " ""
ድንግል ሆይ ስልሽ ""
#አዝማች
የመንገዴ ሥንቅ ነይ እመቤቴ
የራቤ መርሻ " ""
ለታመመ ሰው " ""
ነሽ መፈወሻ " ""
የተማፀነ " ""
በስምሽ አምኖ " ""
ማን አፍሮ ያውቃል " ""
ፊትሽ ለምኖ " ""

ለመቀላቀል
@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo

ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ