Get Mystery Box with random crypto!

ማርያም ማለት ሥጦታና ሀብት (ጸጋ ወሀብት) ማለት ነው። ይህ እንዴት ነው ቢሉ፦ #መጀመሪያ ከእግ | 💜 ...ማርያምን ...🕯

ማርያም ማለት ሥጦታና ሀብት (ጸጋ ወሀብት) ማለት ነው። ይህ እንዴት ነው ቢሉ፦

#መጀመሪያ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ለእናት አባትዋ ነው። "ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው" ተብሎ ተጽፎአልና።

#ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና ነው። "ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል፣ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል" ተብሎ ተጽፎአልና። (ኢሳ 7፥14)

#ሦስተኛ ወላጆችዋ ለእግዚአብሔር ስእለት አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ መሥጠታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር የተሠጠች ሥጦታ ያደርጋታል።

#አራተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ ከመሥጠቱ በፊት እመቤታችን ራስዋን "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ለእግዚአብሔር ሥጦታ አሳልፋ መሥጠትዋ ነው።

#አምስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ላይ ለወዳጁ ለዮሐንስ "እናትህ እነኋት" ብሎ የሠጠ መሆኑ ነው። "በጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ከብርሃናት አባት" ከላይ የሚወርዱ ናቸው። ከእነዚህ የፈጣሪ ሥጦታዎች አንድዋ እመቤታችን ናት።

እመቤታችን ሱባኤያችንን የሐዋርያት ሱባኤ ታድርግልን፣ ካህናትና ምዕመናን እንደ ዕጣን ከእሳት ተጨምረው በሰማዕትነት መዓዛ ያስጀመሩትን ሱባኤ የሰላምና ከበረከታቸው የምንሣተፍበት ያድርግልን። የሀገራችንን ፍጹም ኀዘንዋን፣ የቤተ ክርስቲያንንም ልቅሶዋን በምልጃዋ ትስማልን።

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
ለመቀላቀል
@Mezmure_tewahdo
@Mezmure_tewahdo

ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ