Get Mystery Box with random crypto!

ገብርኤል በሰማይ ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤት በምድር (፪) ይመሰክራሉ ድንግል ያንችን ክብር ( | መዝሙር

ገብርኤል በሰማይ

ገብርኤል በሰማይ ኤልሳቤት በምድር (፪)
ይመሰክራሉ ድንግል ያንችን ክብር ( ፪)
አዝ_________
ትጸንሲ ሲልሽ በከበር ዜና
ይሁንልኝ አልሽው ትውልድ እዲጽናና
ከገብርኤል ሰምተው መላእክቱ ሁሉ
ለበጉ ማደርያ ክብርን ይሰጣሉ
ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን
የራማውን ልዑል አብነት አድርገን
አዝ....
ስርሽ በምድር ነው ሀርግሽ በሰማይ
ንጹህ መሶበወርቅ የተመላሽ ሲሳይ
የማህጸንሽ ፍሬ በላነው ጠጣነው
በኤፍራታ ሰምተን በዱር አግኝተነው
የተሰወርውን መና በልተነዋል
ከተመርጡት ጋር ብፅዕት ብለናል
አዝ...
ከተፍጥሮ በላይ ጽንስን ያዘለለ
የእሳት ምሰሶ ባንች ተተከለ
የእግዚአብሔር ሀገር ሆይ የእጀራ ቤታችን
ምንኛ ድንቅ ነው ክብርሽ እናታችን
ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅድስት ኤልሳቤትን አብነት አድርገን
አዝ....
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዩት
ሰውና መላዕክት አብርው አከበሩት
የጥሉ ግድግዳ በልጅሽ ፍረሰ
በዳግሚት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ
እጅ እንነሳለን ሆነን በትህትና
ክብርሽን መመስከር ክብራችን ነውና
አዝ...
ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ስላዩት
ሰውና መላዕክት አብረው አከበሩት
የጥሉ ግድግዳ በልጅሽ ፈረሰ
በዳግሚት ሄዋን የአዳም ዘር ተካሰ
ብፅዕት እንላለን እኛም አደግድገን
ቅዱስ ገብርኤል አብነት አድርገን

መዝሙር


@MezmurB
@MezmurB

@biniy27