Get Mystery Box with random crypto!

ደስ ይበለን ደስ ይበለን እልል በሉ(2) አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ(2) በብርሀን ሞላት አለም | መዝሙር

ደስ ይበለን
ደስ ይበለን እልል በሉ(2)
አልቀረም ተቀብሮ ተገኘ መስቀሉ(2)
በብርሀን ሞላት አለምን በሙሉ(2)
ምን ቢተባበሩ ምቀኞች ቢጥሩ(2)
ቅዱስ መስቀሉን ሸሽገውቢሰውሩ(2)
አልቻሉም ሊያስቀሩ ምን ቢተባበሩ(2)
በተራራ ተሰውሮ ለዘመናት(2)
ተጥሎ በተንኮል ተደብቆ ከኖረበት(2)
ተገለጠ እነሆ በደመራ እሳት(2)
እሌኒ ናት ይህን መስቀል ያስገኘችው(2)
ደመራን በጥበብ በቦታው ያስቆመችው(2)
የተንኮልን ተራራ ያስቀፈረችው(2)
ታሪካዊ የክርስቶስ ሕያው መስቀል(2)
ይኸው ተገለጠ በግሩም ሀይል(2)
ምን ገዜም ሲያበራ እንዲው ይኖራል(2)

መዝሙር

Share Share Share Share


@MezmurB
@MezmurB
@MezmurB

@biniy27 @biniy27