Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና ደብረ ዕንቁ ልደታ ማርያም ==================== የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ | መዝገበ ሃይማኖት

ሰበር ዜና ደብረ ዕንቁ ልደታ ማርያም
====================
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት የደብረ እንቑ ልደታ ለማርያም በአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ላይ በመሰረተው ክስ ላይ ፍርድ ሰጠ።

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ እንቑ ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን የቅድስት ቤተክርስቲያናችንን ሉዓላዊነት የሚዳፈርና መላውን የአጥቢያ ምእመናን ያሳዘነ ያልተገባ የቤት ግንባታ መሠረት፣ሰፊና ጥልቅ የመንገድ ግንባታ ቁፋሮ፣እንዲሁም ምንነቱን ያላወቅነው የግንባታ መስመር በቤተክርስቲያኒቷ ይዞታ ላይ በመገንባቱ ሁከት ይወገድልን የሚል ክስ ለፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ሁለቱን ወገኖች ሲያከራክር ቆይቶ በዛሬው እለት ፍርድ ሰጥቷል።

በውሳኔውም "ለቤተክርስቲያኒቷ በስሟ ተመዝግቦ ካርታ በተሰጣት 103,952 ካ.ሜ ይዞታ ውስጥ ተከሳሽ የሚያከናውነው የተለያዩ አይነት የግንባታ ስራዎች የሁከት ተግባር በመሆኑ በፍ/ህ/ቁ 1149 መሠረት ሊወገድ ይገባል" ብሏል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል