Get Mystery Box with random crypto!

አኺራችንን እናስቀድም ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በ | መወዳ ቻናል(MEWEDA CHANNEL)

አኺራችንን እናስቀድም

ልጅ ሆይ! ስለ ወላጅ ሐቅ ክብደት ሲነገር አይክበድህ። የወላጅን ሐቅ በመጠበቅ ከወላጅ በላይ የሚጠቀመው ልጅ ነው።

ሚስት ሆይ! ስለ ባል ሐቅ በተደጋጋሚ ሲነገር አይደብርሽ። የባልን ሐቅ በመጠበቅ ከባል በላይ የምትጠቀመው ሚስት ናት።

ባል ሆይ! ስለ ሚስት ሐቅና ኃላፊነትህን ስለ መወጣትህ ሲነገር አትሰላች። የሚስትን ሐቅ በመጠበቅ ከሚስት በላይ የሚጠቀመው ባል ነው።

ማንም ቢሆን በፈጣሪው የተጣለበትን ሐቅ ቢወጣ ከሚያከብረውና ከሚንከባከበው አካል በላይ የሚጠቀመው እራሱ ነው። ደግሞም በፈጣሪ የተጣለብንን አደራ ለመወጣት ሲያደርጉ እናደርጋለን፣ ሲተው እንተዋለን ዓይነት የ 'ሰጥቶ መቀበል' ሂሳብ ውስጥ መግባት የለብንም።

አባትህ ቢበድልህ የበደል ሂሳብ ውስጥ አትግባ። በወንጀል እስካላዘዘህ ድረስ በምትችለው ከጎኑ ሁን። ከሌሎችም አንፃር እንዲሁ። አላህ ነፍስያችንን ረግጠን ለትእዛዙ የምናድር ያድርገን።


IbnuMunewor

▬▬▬▬▬▬▬▬▬●●▬▬▬▬▬▬


https://t.me/mewedachannel