Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት

የቴሌግራም ቻናል አርማ meskal — ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት
የቴሌግራም ቻናል አርማ meskal — ትምህርተ ሃይማኖት ርትዕት
የሰርጥ አድራሻ: @meskal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.91K
የሰርጥ መግለጫ

በወንጌል ኮነ ህይወትነ

ህይወታችን በወንጌል ሆነ
ቅ / ያሬድ

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-11-01 13:27:49 Watch " ወቅታዊ ትምህርት በዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ "ለክርስቲያን ሁሉ የእመቤታችንን ተአምር መስማት ቀላል አይምሰለው" መኀትው ቲዩብ _mehatew tube" on YouTube


1.3K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-01 10:16:12 ጥቅምት 27
 
- መድሃኔአለም(ጥንተ ስቅለት)
- አቡነ መባጽዮን( መድሃኔአለም በስቅለቱ አምሳል ሁኖ የተገለጠላቸዉ)

በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት

በእነዚህ አብያተ ክርስትያናት በአለ ንግሱ ይከበራል።

ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው።
 
ይቀላቀሉን:: 

  መባዓ ፅዮን ይጠብቁን

    መድሃኔአለም ይጠብቀን


1) ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ /ክ/ከ ማሞ አካባቢ

2) ድልበር መካነ ጎልጎታ መድሃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ጉለሌ ድልበር

3) ደብረ ቀራንዮ መድሃኔአለም እና ገብርኤል

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቀራንዮ

4) ፍኖተሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም

5) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል

ልዩ ስም፦አዲስ ከተማ/ክ/ከ አውቶብስ ተራ

6)  አስኮ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አስኮ አዲስ ሰፈር

7) ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና ቅድስት ኪዳነምህረት ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ አባዶ

8) አያት መካነ ህይወት መድሃኔአለም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ /ክ/ከ አያት ጠበል

9) ምስራቀ ፀሐይ መድኃኔአለም ቀበና ካቴድራል

ልዩ ስም፦አራዳ /ክ/ከ ቀበና

10) ቦሌ ሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከሰሚት ወጂ

11) ኮዬ መካነ  ህይወት አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ኮዬ

12) ካራ አሎ ደብር ቅዱስ ደብረ ቀርሜሎስ መድኃኔአለም እና ጻድቁ አቡነ ገሪማ

ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ ካራ

13) ቃሊቲ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 12 ሰሪቲ

14) ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድሃኔአለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ መድሃኔአለም

15) መንበረ ንግስት ቁስቋም ማርያም

ልዩ ስም፦ጉለሌ ክ/ከ  እንጦጦ ቁስቋም

16) ፈረንሳይ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦የካ /ክ/ከ ፈረንሳይ ብረት ድልድይ

17) ቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ  ቦሌ ቡልቡላ

18) ብሔረ ፅጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ብሔረ ፅጌ

19) ረቢ መካነ ጎልጎታ መድኃኔአለም

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ

20) ጎፋ ቤዛ ብዙሃን ቅድስት ኪዳነምህረት  ካቴድራል

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ጎፋ ካምፕ

21) ቶታል ፈለገ ህይወት ቅድስት ኪዳነምህረትና መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ

22)  ማህደተ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያምና ደብረ መድኃነት መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ልደታ /ክ/ከ ልደታ

23) ደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ መስቀል ፍላወር

24) ደብረ ፍስሃ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ቂርቆስ /ክ/ከ ቂርቆስ

25) ላፍቶ ደብረ ኢያሪኮ መድኃኔአለም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አብያተክርስትያናት

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ (ላፍቶ)

26) ፉሪ ደብረ ሰላም መድኃኔአለምቤ/ክ

ልዩ ስም፦ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ጀሞ 1 ኮንዶሚንየም

27) ደብረ ሰሊሆን መጥምቀ መለኮት  ቅዱስ ዮሐንስ እና መድኃኔአለምቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ በርታ ሰፈረሰላም

28)  አቃቂ መንበረ ህይወት መድኃኔአለም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ጋራው መድኃኔአለም
29)  ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈጬ

30)  ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት

31)  ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ

ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ሰፈረ ገነት

32) ጽርሐንግስትቅድስትሐናቤ/ክ

ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ፉሪ ሐና ማርያም
1.3K views07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-30 15:55:59 Watch " ድንቅ ትምህርት በዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ |ዕፀ መስቀል|_መኀትው ቲዩብ_mehatew tube" on YouTube


1.0K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 21:28:45 Watch "ፈረንሳይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ድንቅ ማህሌት።መሰማት ያለበት_መኀትው ቲዩብ_mehatew tube..ethiopan orthodox tewahdo" on YouTube


1.2K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 08:39:08 Watch "ይህንን video ካዩ በኋላ ለግዕዝና ለቅኔ ያላቹ አመለካከት ይለወጣል።መታየት ያለበት መኀትው ቲዩብ።ኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ" on YouTube


1.2K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-06 05:46:03 መስከረም 29 የት ማክበር አስበዋል ?


ቅድስት አርሴማ

በአዲስ አበባበ አህጉረ ስብከት በእነዚህ አብያተክርስትያናት በአለ ንግሱ ይከበራል።

ይህ ቻናል በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር በሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ የሚከበሩ ዓመታዊ የንግሥ በዓላትን የሚገልፅ ነው። 
 
  ቅድስት አርሴማ ትጠብቀን

1)     ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ ዊንጌት ጠሮ አራት መንታ         
 
2)     ገዳመ ኢየሱስ         
 
ልዩ ስም፡-ልደታ ክ/ከ ሆላንድ ኤምባሲ         
 
3)     ኮልፌ ደብረ ፀሐይ አቡነ ተክለሐይማኖት እና  ቅዱስ ገብርኤል         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ፊሊዶሮ         
 
4)    ደብረ መድሃኒት አቡነ ሐብተማርያም ወቅድስት ልደት ወቅድስት አርሴማ ገዳም         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቅ/ክ/ከ አስኮ ካኦጄጄ ዱቄት ፋብሪካ ከፍ ብሎ ቃሌ ተራራ ላይ         
 
5)   አያት መካነ ህይወት መድሃኔአለም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ቦሌ /ክ/ከ አያት ጠበል         
 
6)    ምስራቀ ፀሐይ መድኃኔአለም ቀበና  ካቴድራል         
 
ልዩ ስም፦አራዳ /ክ/ከ ቀበና         
 
7)    ኮተቤ ማህደረ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል  ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ሉቄ          
 
8)     ኮተቤ ሀገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅድስት መግደላዊት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ          
 
9)     ጉራራ ምስራቀ ፀሐይ ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ፈረንሳይ ጉራራ          
 
10)   ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ታቦት ማደሪያ         
 
11)    ደብረ ቢታንያ አቡነ ተክለሐይማኖት እና ቅድስት ልደታ ለማርያም         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ቆሬ 5 ቁጥርና 2 ቁጥር ማዞርያ         
 
12)   አዲስ አምባ ደብረ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምህረት እና ደብረ ፍስሃ  ቅዱስ ገብርኤል         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ሳሪስ አዲስ ሰፈር         
 
13) ጀሞ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ           
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ  ጀሞ         
 
14)     ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል፤ቅድስት አርሴማ እና አቡነ አዳም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ ጀርመን አደባባይ         
 
15)  ሐመረ ወርቅ ቅድስት ማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 5 ወርቁ ሰፈር         
 
16) አለም ባንክ ጀሞ ደብረ ራማ ቅዱስ ገብርኤል         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አለም ባንክ         
 
17)    አቃቂ ፈንታ ደብረ ፅጌ  ቅዱስ ሩፋኤል  እና ቅድስት አርሴማ         
 
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈንታ         
 
18)   ቃሊቲ ደብረ መድሃኒት መድሃኔአለም እና አቡነ አረጋዊ ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 12 ሰሪቲ

19) መንበረ ክብር ቅዱስ ሚካኤል፤ጻድቁ አቡነ ተክለ ሐይማኖት እና ቅድስት አርሴማ

ልዩ ስም፦ጉለሌ /ክ/ከ ቀጨኔ
20) የቃሊቲ መካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን

ልዩ ስም:- አ/ቃ/ክ/ከ/ ወረዳ 5 ሰፈረ ሰላም (አባኮት)

21) ደብረ መዊዕ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ\ክ

ልዮ ስም:- ን/ስ/ላ/ክ/ከ ሀና ማንጎ ሰፈር

22)ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑራኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩ ስም:- ቦሌ ክፍለ ከተማ ከገርጂ መብራት ሀይል ወደ ጎሮ በሚሄደው መንገድ አለማየሁ ህንፃ ገባ ብሎ

23) መንበረ ልኡል ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማሪያም ቤተ ክርስቲያን

ልዩ ስም:-ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላፍቶ 58 ማዞሪያ
24) ምዕራፈ ሰማዕታት ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን

ልዩ ስም:- ቦሌ ክ/ከተማ አዲሱ ስታዲየም

25) የግራር ደብረ ዐባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ

ልዩ ስም:- ኮ/ቀ/ክ/ከ ግራር ኮንዶሚኒየም አካባቢ

26) ቦሌ አራብሳ ዋሻ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፣ ቅድስት ልደታ ለማርያም ፣ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ፣ ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን

27) የካ አባዶ ደ\ል ቅድስት አርሴማ እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዩሐንስ ቤተ ክርስቲያን

28) ገነተ ሰማይ ቅድስት አርሴማ ወአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን

29) ጎፋ መካነ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል ወቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያ

30) ጎጆ አርሴማ ወአቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን

31) ቦሌ ሰሚት ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን

ልዩ ስም፦ ቦሌ ክ/ከ ሰሚት ኮንዶሚንየም አካባቢ

ሼር ማድረግ አይዘንጉ

ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞች ሆይ ለኦርቶዶክሳዊ ወንድምዎ ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያናችንን ቀጥተኛ ትምህርት ያሳውቁ ይመስክሩ ።


@meskal
@meskal
@meskal
2.3K views02:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-30 22:12:06 መስከረም 21 የት ማክበር አስበዋል

?ድንግል ማርያም ትጠብቀን

1)     ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊልጶስ ካቴድራል         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አጠና ተራ         
 
2)     ፍኖተሎዛ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ብርጭቆ ኮንዶሚንየም         
 
3)    ማህደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፡-ኮ/ቀ/ክ/ከ የሺ ደበሌ          

4)    ኮተቤ  ደብረ ልዑል ዳግማዊ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤልና ኆኅተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ ኮተቤ መሳለሚያ         
 
5)    ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ  ካቴድራል         
 
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጉርድ ሾላ         
 
6)    ቦሌ ኆህተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ገርጂ         
 
7)   ደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አርበኞች መንገድ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል          

8)   ቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ህይወት ቅድስት ማርያም እና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ         
 
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም         
 
9)   ብሔረ ፅጌ መካነ ሰላም ቅድስት ማርያምና መድኃኔአለም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ብሔረ ፅጌ         
 
10)   ደብረ ተአምራት ዳግማዊት ጻድቃኔ ቅድስት ማርያም         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ ታቦት ማደሪያ         
 
11)  ፈለገ ዮርዳኖስ ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት ማርያም         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ጀሞ 3 መስታወት ፋብሪካ ጀርባ         
 
12)  ሐመረወርቅ ቅድስት ማርያም እና ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ         
 
ልዩስም፦አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 5 ወርቁ ሰፈር         
 
13)  ፈጬ ደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ፈጬ         
 
14)  ሰርጢ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም         
 
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ሰርጢ ማርያም         
 
15)  ቃሊቲ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል እና ደብረ ቁስቋም ቅድስት ማርያም ቤ/ክ          
 
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ/ክ/ከ ሰፈረ ገነት          
 
16)   ርእሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም  ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፡-ጉለሌ /ክ/ከ እንጦጦ ማርያም         
 
17)   መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም         
 
ልዩ ስም፦አራዳ ክ/ከ አምስት ኪሎ          
 
18)    ምስራቀ ፀሐይ ቅዱስ ሚካኤልና 24ቱ ካህናተ ሰማያት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አባዶ         
 
19)     ኮተቤ ሀገረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ቅድስት ድንግል ማርያም እና ቅድስት መግደላዊት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ          
 
20)    የረር በር መካነ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ቦሌ ክ/ከ ጎሮ         
 
21)   አንቆርጫ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦የካ ክ/ከ አንቆርጫ         
 
22)  ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ ወረዳ 1 ለቡ(ፉሪ)         
 
23)    መካኒሳ ምዕራፈ ፃድቃን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ         
 
ልዩ ስም፦ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ መካኒሳ አቦ         
 
24)  ቂሊንጦ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል እና ቅድስት ድንግል ማርያም         
 
ልዩ ስም፦ አቃቂ ቃሊቲ /ክ/ከ ወረዳ 9  ቂሊንጦ         
 
25)    አውግስታ ደብረ ፅዮን ቅድስት ማርያም ቤ/ክ         
 
ልዩ ስም፦ኮ/ቀ/ክ/ከ አውግስታ ሸሚዝ ፋብሪካ

ኦርቶዶክሳዊ ወንድሞች ሆይ ለኦርቶዶክሳዊ ወንድምዎ ሼር በማድረግ የቤተክርስቲያናችንን ቀጥተኛ ትምህርት ያሳውቁ ይመስክሩ ።


@meskal
@meskal
@meskal
1.2K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-23 21:45:25 ††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አባ አጋቶን ወአቡነ ያሳይ ዘመንዳባ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አባ አጋቶን ዘዓምድ †††

††† ታላቁ ጻድቅ በትውልድ ግብጻዊ ሲሆኑ የነበሩበት ዘመንም ከ4ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እስከ 5ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ ነው:: በእርግጥ 'አጋቶን ' በሚባል ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ቅድሚያውን 2ቱ ይወስዳሉ::
አንደኛው አባ አጋቶን ለ30 ዓመታት ድንጋይ ጐርሰው የኖሩት አባት ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: እኒህኛው 'ዘዓምድ ' ይባላሉ:: ምክንያቱም ለ50 ዓመታት አንድ ምሰሶ ላይ ያለ ዕረፍት ጸልየዋልና ነው::

አባ አጋቶን ገና ከልጅነታቸው መጻሕፍትን የተማሩ ሲሆኑ ምናኔን አጥብቀው ይፈልጓት ነበር:: በዚህም ራሳቸውን በትሕርምት እየገዙ: በዲቁና ማዕርጋቸውም እያገለገሉ እስከ 35ዓመታቸው ቆዩ:: በዚህ ጊዜ ደግሞ 'ይገባሃል' ብለው ቅስናን ሾሟቸው::

የማታ ማታ የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ተምኔተ ልባቸውን ፈጽሞላቸው ወደ በርሃ ሔዱ:: ወቅቱ የግብጽ ገዳማት በቅዱሳን ሕይወት የበሩበት ነውና እዚህም እዚያም አበውና እናቶች ይገኙ ነበር::

አባ አጋቶንም የከዋክብቱ አበው አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም ደቀ መዝሙር ሆነው ገቡ:: አስፈላጊውን የምንኩስና ፈተና ካለፉ በኋላም ምንኩስናን ከእነዚህ አባቶች ተቀበሉ:: በዚያው በገዳመ አስቄጥስ በጽኑ ገድል ተጠምደው ለ15 ዓመታት አገለገሉ::

ጻድቁ ከእርሳቸው በፊት የነበሩ ቅዱሳንን ተጋድሎ ጠዋት ማታእያነበቡ መንፈሳዊ ቅናትን ይቀኑ ነበር:: በተለይ የታላቁን ስምዖን ዘዓምድን ገድል ሲያነቡ ሕሊናቸውን ደስ ይለው: ይህንኑ ገድል ይመኙ ነበር:: እድሜአቸው 50 ዓመት በሞላ ጊዜ በልቡናቸው እንደ አባ ስምዖን ዘዓምድ ለመጋደል ወሰኑ:: ይህን ለገዳሙ አባቶች ቢያማክሯቸው አበው:- "ይበል! ሸጋ ምክር ነው:: እግዚአብሔር ያስፈጽምህ!" ብለው መርቀው አሰናበቷቸው:: አባ አጋቶን የዳዊትን መዝሙር እየዘመሩ ከገዳሙ ወጡ:: በጣምም ወደ ዓለም ሳይገቡ: ከዓለም (ከከተማም) በጣም ሳይርቁ አንድ ረዥም ምሰሶ አገኙና ከላዩ ላይ ወጡ::

ከዚህች ዕለት ጀምረው ጻድቁ ለ50 ዓመታት ከዚያች ዓምድ (ምሰሶ) ወርደው: ለሥጋቸውም ዕረፍትን ሰጥተውት አያውቁም:: ማዕከለ ገዳም ወዓለም ናቸውና ለምዕመናንም ሆነ ለመነኮሳት አጽናኝ አባት ሆኑ:: ለአካባቢውም የብርሃን ምሰሶ ሆኑ:: የታመመ ቢኖር ይፈውሱታል:: የበደለውን በንስሃ ይመልሱታል:: ሰይጣን የቋጠረውን ይፈቱታል:: ለራሳቸው ግን ከጸሎት: ከጾምና ከትሕርምት በቀር ምንም አልነበራቸውም:: በተለይ እነዚህ ስራዎቻቸው ይዘከሩላቸዋል::
1.አጥማቂ ነን እያሉ ሕዝቡን ያስቱ የነበሩ ሰዎችን እየጠሩ እንዲህ የሚያስደርጋቸውን ጋኔን ከእነሱ አስወጥተዋል::
2.እርሳቸውን ያልሰሙት ግን መጨረሻቸው ጥፋት ሆኗል::
3.ፍጹም ወንጌልን በሕይወትና በአንደበት መስክረዋል::
4.ሕዝቡን በንስሃ አስጊጠዋል::
5.ተግሳጽ የሚገባውን ገስጸዋል::

ጻድቁ አባ አጋቶን ዘዓምድ ከእነዚህ የቅድስና ዘመናት በኋላበተወለዱ በ100 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በክብርና በዝማሬ ተቀብረዋል::

††† አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ †††

††† እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ በ14ኛው መቶ ክ/ዘ በጣና ገዳማትውስጥ ያበሩ ኮከብ ናቸው:: ከ7ቱ ከዋክብት (አባ ዮሐንስ፣ አባ ታዴዎስ፣ አባ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አባ ሳሙኤል ዘቆየጻና አባ ሳሙኤል ዘጣሬጣ ) እርሳቸው አንዱ ናቸው:: እነዚህ አበው ከገዳማዊ ሕይወታቸው ባሻገር በምስጉን የወንጌል አገልግሎታቸው የሚታወቁ ናቸው::

ገድላቸው እንደሚለው አቡነ ያሳይ የዐፄ ዐምደ ጽዮን ቀዳማዊ ልጅ ሲሆኑ የተወለዱትም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ሽዋ: ተጉለት ውስጥ ነው:: ገና በልጅነታቸው ወደ አባታቸው ቤተ መንግስት የሚመጡ መነኮሳትን እግር እያጠቡ ሥርዓተ ምንኩስናን በድብቅ ያጠኑ ነበር::

ብሉይ ከሐዲስ የጠነቀቁ ናቸውና የአባታቸውን ዙፋን (ልዑልነት) ስለ ፍቅረ ክርስቶስ ንቀውት እየዘመሩ ጠፍተው ወደ ትግራይ ተጓዙ:: በዚህም ምክንያት 'መናኔ መንግስት' ይባላሉ:: በዚያም ወደ ደብረ በንኮል ገዳም ውስጥ ገብተው የታላቁ አባት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደቀ መዝሙር ሆኑ::

ቀደም ሲል የጠቀስናቸው 7ቱ አበው በዚያ ነበሩና 7ቱም በአንድ ቀን ሲመነኩሱ ገዳሙ የተቃጠለ እስኪመስል ድረስ ብርሃን ወርዶ ነበር:: አቡነ ያሳይ በረድእነት በቆዩበት ዘመን ዛፎችን መትከል ይወዱ ነበር:: ከትሩፋት መልስም በልብሳቸው ውሃ እየቀዱ ያጠጡ ነበር:: በተለይ "ምዕራገ ጸሎት" የሚባለው ተአምረኛ ዛፍ ዛሬ ድረስ አለ ይባላል::

አቡነ ያሳይ ጊዜው በደረሰ ሰዓት ከአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተባርከው: ከ2ቱ ባልንጀሮቻቸው (አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊና አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ) ጋር ወደ ጣና ሐይቅ መጡ:: በዚያም አካባቢ ተአምራትን እየሠሩ ሕዝቡንም እያስተማሩ ከቆዩ በኋላ ጌታ ወደየፈቀደላቸው ቦታ ተለያዩ::

አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ: አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ወደ ገሊላ: ከዚያ ወደ ጉጉቤ ሲሔዱ አቡነ ያሳይ መንዳባ ውስጥ ገቡ:: ጻድቁ ወደ አርባ ምንጭ ሒደው ታቦተ መድኃኔ ዓለምን ይዘው ሲመጡ ጣናን የሚሻገሩበት አጡ:: ጌታን ቢማጸኑት:- "ምነው እሷን ድንጋይ ባርከህ አትቀመጥባትም?" አላቸው:: እሳቸውም በእምነት: ድንጋይ ላይ ተቀምጠው ጣናን ተሻገሩት:: ይህንን ከርቀት ያዩ የዘመኑ ሰዎች "ብዙ ተአምር አይተናል: ነገር ግን ማን እንደ አባ! ጣናን በድንጋይ የተሻገረ" ሲሉ አድንቀዋቸዋል::

ጻድቁ ጣናን ተሻግረው: ገዳም መሥርተው: ብዙ አርድእትን አፍርተው: በተጋድሎ ሕይወታቸው ቀጥለዋል:: በተለይ ዛሬ ድረስ የሚተረከው የ'አትማረኝ' ታሪክም የሚገኘው እዚሁ ገዳም ውስጥ ነው:: ታሪኩም በየዋህነት "አትማረኝ" ብለው ጸልየው ጣናን ያለ ታንኳ በእግራቸው የረገጡ አባትን የሚመለከት ሲሆን ከአቡነ ያሳይ ጋርም ወዳጅ ነበሩ::

አባታችን አቡነ ያሳይ ለዘመናት በቅድስና ኑረው: ቅዱሳንንም ወልደው መስከረም 14 ቀን ታመሙ:: "ጌታ ሆይ!" ብለው ቢጠሩት መድኃኔ ዓለም መጣላቸው:: ጣና በብርሃን ተከበበች:: ጌታም "ወዳጄ! ስለ ድካምህ: ደጅህን የረገጠውን: መታሰቢያህን ያደረገውን: በስምህ የተማጸነውን ሁሉ ከነትውልዱ እምርልሃለሁ" ብሏቸው ነፍሳቸውን አሳረገ:: አበውም ሥጋቸውን ገንዘው እዚያው መንዳባ መድኃኔ ዓለም ውስጥ ቀበሩት:: ዐጽማቸው ዛሬም ድረስ ይገኛል::

††† አምላከ ጻድቃን በምልጃቸው የበዛች ኃጢአታችንን ይቅር ይበለን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† መስከረም 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አባ አጋቶን ዘዓምድ
2.አቡነ ያሳይ ዘመንዳባ
3.አባ ጴጥሮስ መምሕረ ጻና (ጣና)
4.ቅዱስ ዴግና ቀሲስ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
3.ቅዱስ ፊልጶስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ሙሴ (የእግዚአብሔር ሰው)
5.አባ ስምዖን ገዳማዊ
6.አባ ዮሐንስ ጻድቅ
7.እናታችን ቅድስት ነሣሒት

††† "ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" †††
(ማቴ. ፲፥፵፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
1.3K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 22:43:38 Channel photo updated
19:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 22:11:38 Watch "የመስቀል ደመራ መዝሙሮች ስብስብ#1 Ethiopian meskel demera mezmur collection _መኀትው ቲዩብ_mehatew tube" on YouTube


952 views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ