Get Mystery Box with random crypto!

መሠረታቲሀ ውስተ አድባር ቅዱሳን

የቴሌግራም ቻናል አርማ mesertatihawusteadbarekidusan — መሠረታቲሀ ውስተ አድባር ቅዱሳን
የቴሌግራም ቻናል አርማ mesertatihawusteadbarekidusan — መሠረታቲሀ ውስተ አድባር ቅዱሳን
የሰርጥ አድራሻ: @mesertatihawusteadbarekidusan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.16K
የሰርጥ መግለጫ

ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ፦
በዚህ ቻናል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙሮች እና መንፈሳዊ ትምሕርቶችን ያገኙበታል።
ዘማሪ ዲያቆን ፍጹም ከበደ
✍🏾 ለአስተያየት

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 23:18:43 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






6 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 21:14:26 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 2
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






45 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:11:13 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






82 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 05:18:29  የእመቤታችን ሕይወት ከጌታ ሞት በኋላ

እመቤታችን በቤተ ዮሐንስ ከቤተሰቦቹ ጋር አሥራ አምስት ዓመት  ኖረች።   ቤታቸው በደብረ ዘይት ተራራ አቅራቢያ ነበር። እርሱም ከሔደበት አገልግሎት ሲመለስ ይጎበኛት ነበር። በወቅቱ ለአማንያኑና ለሐዋያት አማካሪም አጽናኝም ነበረች።  ለሐዋርያት ተአምራታዊ  ስለ ነበሩት የመልአኩ ብስራት፣ ያለ ወንድ ዘር ስለ መጽነስዋ፣ የእርሷን የልጅነት ታሪክ ትነግራቸው ነበር ይላል።

በተጨማሪም ልክ እንደ ሐዋርያቱ እርስዋም ቤተ ክርስቲያንን (ማኅበረ መእመናንን) በማቋቋም ረድታቸዋለች፤ በምልጃዋ ይታገዙ ነበር። ሐዋርያት ከበዓለ ሃምሳ በኋላ ሐዋርያት ለአሥር አመታት ያኽል ኢየሩሳሌም ነበሩ። ለአይሁድ ድኅነትን ሲሰብኩ። 

ሐዋርያት ብዙውን ጊዜ ከእመቤታችን ጋር ያሳልፉ ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ሲሔድ ከእርሱ ጋር ወስዷታል። ብዙዎ እርሷን ለማየት ከሩቅ ይመጡ ነበር። ይኽንን አስመልክቶ ቅዱስ አግናጥዮስም የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ለቅዱስ ዮሐንስ ሲጽፍለት ሲጽፍ እንዲኽ ነበር ያለው፡- 

“ከተቻለ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን የአማኞች ጉባኤ ለማየት ለመካፈል እመጣለሁ፡፡ በተለይም የኢየሱስን እናት ለማየት፡ እርሷ የተከበረች ፣ትሁት፤ በሁሉም አስደናቂ፣ ሁሉም እርሷን ለማየት ይሻል፡፡ እርሷ የእግዚአብሔር እናት ሁላችንን ትባርካለች፤ ምልዕተ ጸጋ ወክብር፣ እርሷ በስደትና በመከራ ውስጥ ሁሉ ደስተኛ ናት፣ ደኃ በመሆን አታዝንም፣ በሚያበሳጩአትም ሁሉ አትበሳጭም፣ እንደውም አብልጣ ታደርግላቸዋለች፡፡ ያያት ሁሉ ይደነቃል፣ ይደሰታል” በማለት ጽፎለታል።

በመጀመሪያው የክርስቲያኖች ስደት ከዮሐንስ ጋር ሆና ወደ ኤፊሶን ተሰዳ ነበር በ43 ዓ.ም። “በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው። የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው” ሐዋ.12.1

በቆጵሮስም(ሳይፕረስ) ከሞት ከተነሳው ከአልአዛር ጋር  ነበረች ሊቀ ጳጳስ ሆኖ ሳለ።

ዲዮናስዮስ፤ አግናጥዮስ፤ አምብሮስ ስለ እመቤታችን መንፈሳዊ ሕይወት ትንታኔ ሲሰጡ፦ 

"ድንግልናዋ በሥጋ ብቻ አይደለም በነፍስዋ፣ በሕሊናዋ፣ በልብዋ። በልብዋ ትኁት፣ አእምሮዋ ጠቢብ ነበር። ሥራና ንባብ ወዳጅ ነበረች። ጥንቁቅ ተናጋሪ ናት፣ የኑሮዋ መመሪያ ማንንም አያስቀይምም ነበር። ታላላቆችን ታከብራለች፣ አትታበይም። አትቀናም፣ ጤናማ አእምሮ አላት፤ ምግባር ትወዳለች፣ ሁሌም ትጾማላች፣ ሲያስፈልጋት ብቻ ትተኛለች፡ ሰውነቷ እንኳ ዐረፍ ብሎ መንፈሷ ንቁ ነው። ቀን ያነበበችውን በሕልምዋ ትደግመዋለች፡ ከቤት የምትወጣው ለቤተ ክርስቲያን ሥራ ብቻ ነው፡፣ አልያም ዘመዶቿን ለማየት" በማለት ገልጦታል።

ቅዱስ አትናቴዎስም ሲቀጥል፡-

በጣም መልካም ያማረ አቋም የነበራትና መልካም ሥራዎችን የምትወድድ ነበረች። በወንዶች መታየትን ፈጽማ አትፈልግም ነበር፣ ግን እግዚአብሔርን እንዲመረምራት ትጠይቃዋለች፤  ከጨዋታ የራቀ (የመናኝ) ሰውን ኑሮ ትኖር የነበረ ሲኾን ማር ከምትሰጥ ንብ ጋር ትመሳሰላለች። በእጆቿ ከሠራቻቸው ሥራዎች የምታገኘውን ገንዘብ ለድኾች ታከፋፍላለች። በብቸኝነት ኹለት ነገራትን እንዲያደርግላት ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች፤ ይኸውም መጥፎ ሐሳብ በልቧ ውስጥ እንዳይሠርጽና ልቧ በጭራሽ ከፍቅር አምላካዊ እየቀዘቀዘ እንዳይኼድ ነበረ። ንግግሯ የተረጋጋ እና ድምፆቿም ዝግ ያሉ ናቸው፤ በየቀኑም መንፈሳዊ ርምጃ (ብቃታዊ መሻሻል ዕድገት) ማድረግ ትፈልጋለች፤ በየቀኑም ያነን ታደርጋለች፤ በጠዋት ስትነሣም ከዚኽ በፊት አስቀድማ ከሠራቻቸው አስበልጣ ሥራዎቿን ለመሥራት ትፈልጋለች፤ ሞትን ፈጽማ አትፈራም ነበር። ይልቁኑ በሐዘን ኹና የመንግሥተ ሰማያት መዠመሪያ (መግቢያ) እንዳላቋረጠች በየቀኑ እያየች በጸሎቷ ታነሣለች) በማለት የደናግል መመኪያነቷን በስፋት ገልጾታል፡፡ (ዶ/ር ሮዳስ)

ኒሲፎረስ (ታሪክ ጸሐፊው) ስለ መልኳ ሲጽፍልን፦

"መካከለኛ ቁመት፣ ጸጉሯ ወረቃማ፣ ዓይኗ እንደ ወይራ ዘይት ብርሃን ያበራል፣ የዓይን ቅንድቧ ጠንካራና ጥቁር ነው፣ አንደበቷ የሚጣፍጥ ንግግር አለው፣ ጣቶችዋና መዳፍዋ ረጃጅም ናቸው"። በተአምረ ማርያም ላይ የእመቤታችን መልክ የአምላክን መልክ ይመስላል የሚል ንባብ አለ። ይኽም በአካል ልጇን ትመስላለች ማለት ሲሆን፤ ሌላውና ትልቁ ግን  መልክ የውጭ ውበትን ሳይሆን የመንፈሳዊ ሕይወትን ውበትን ማለት ነው። ቅዱስ ጳውሎስም የልጁን መልክ እንድንመስል ነግሮናል። 

ኒሲፎረስ ይቀጥላል እንዲኽ በማለት፦ "ስትናጋገር ተራ ንግግር አትናገርም፤ አትበሳጭም በፍጹምም አትናደድም፣ በፍጹም ስለራስዋ አትናገርም፣ የምታስበው ለሌላው ነበር። የልብሶችዋ ቀለም ተፈጥሮአዊ ቀለም ነበር።

ዲዮናስየስም ሲጽፍ ስለ እመቤታችን እረፍት  “አንቀላፋች ” ብሏታል። የሥጋዋን ወደ ሰማይ ማረግ የተናገረውና ጽፎ የተገኘው ለመጀመሪያ ጊዜ የሰርዴሱ ሊቀ ጳጳስ ሜሊተን ነው ብሎ አስፍሮላታል።

በአጠቃላይ ስለ እመቤታችን የማረፍ ታሪክ በትክክል መረጃን ሰብስቦ ያሰፈረው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጸሐፊው ኒሲፎረስ ነው። በተመሳሳይም የሐገራችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለ እመቤታችን እረፍት ሲናገር ፦“ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ”  ማርያም ሆይ አሟሟትሽ ሰርግን ይመስላል ይላል። 

የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
280 viewsወሰንየለው ባህሩ, 02:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 19:23:14  የተዘጋች የውኃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ 

ቅዳሴ ማርያም ላይ የምናገኘው ቃል ነው።  በቆየው የእስራኤላውያን ልማድ መሠረት ውኃን የሚጠቀሙት ከከርሰ ምድር የሚገኝ ውኃን ሲሆን ይኽውም ጉድጓድ በመቆፋር ነበር። በዚህም አንድ የቤተሰብ ኅላፊ የውኃ ጉድጓድ ቆፍሮ ለቤተሰቡ፣ ለወገኑ፣ ለእንሰሶቹ ጥቅም ላይ ያውላል። በተጨማሪም እነዚህን ጉድጓዶች መጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ምክንያቱም ጉድጓጎቹ ጠላት አለባቸው።

 አንደኛው ችግር የራሳቸው ጉድጓድ ባልሆነው ሌሎች ሰዎች ይመጡና ሲመነጭ ያደረውን ውኃ ይጠቀሙበታል። በዚህም ምክንያት ይመስላል አብርሃም የአቤሜሌክ እረኞች የጉድጓድ ውኃውን ስለተጠቀሙበት ስሞታ አቅርቦ እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። “አቢሜሌክንም ባሪያዎቹ በነጠቁት በውኃ ጕድጓድ ምክንያት አብርሃም ወቀሰው” ዘፍ. 21:25

 ከአብርሃም ቀጥሎም ይስሐቅ ሶስት የውኃ ጉድጓዶችን ቆፍሮ እንደ ነበርና በዚኽም ምክንያት ጠላት እየደፈነበት ብዙ ፈተናን አይቷል። ውኃ መሠረታዊ ስለሆነ ጉድጓዳቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል። ከአብርሃም ቤት ተሰዳ ወደ ግብጽ ትጓዝ የነበረችው አጋር በበረሃ የተቆፈረው ውኃ ልጅዋንም ሆነ እርስዋን በጥም ከመሞት እንደታደጋት መጽሐፍ ቅዱስ ይነግራናል። "እግዚአብሔርም ዓይንዋን ከፈተላት፥ የውኃ ጕድጓድንም አየች፤ ሄዳም አቁማዳውን በውኃ ሞላች፥ ብላቴናውንም አጠጣች" ዘፍ. 21:19

 ያዕቆብ በዘመኑ ጉድጓድ አስቆፍሮ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ባይነግረንም በዮሐንስ ወንጌል ላይ ሳምራዊቷ ሴት ልትቀዳ የሔደችበት ጉድጓድ በያዕቆብ መቆፈሩን ነግራናለች። ይኽ የሚያመለክተን እስራኤላውያን ውኃን ከጉድጓድ እንደሚጠቀሙና ለልጅ ልጅም በስማቸው ይተላለፍ እንደነበር ነው። “በእውኑ አንተ ይኽን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል አለችው” ዮሐ.4:12

ሁለተኛው የውኃ ጉድጓዶቹ የሚገጥማቸው ችግር ቢኖር ጠላት ሊያጠቃቸው ሲመጣ የውኃ ጉድጓጎቹን መርዝ ከቶ መንጎቹንም ሰዎቹንም ሊገድል ስለሚችል ይጠብቁታል። ለዚኽም እንደ መከላከያ የሚጠቀሙት በውኃው ጉድጓድ ላይ ለብዙ ሰው ካልሆነ ሊንከባለል የማይችል ድንጊያ እንደ ክዳን ይገጥሙበታል። (ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ)

 በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በትንቢትና በምሳሌ ለሰው ሊሆን የሚችለውን የመዳን ትንቢት ከሚነግሩን ድርጊቶች መካከል "የውኃ ጉድጓድ" አንዱ ነው። ለዛሬ ያዕቆብ በጉዞው ሰላገጠመው  የውሃ ጉድጓድ በአጭሩ እንመለከታለን።

ከቤርሳቤህ ወደ ካራን በጉዞ ላይ ሳለ በመንገድ እረኖች በጎችን ይዘው በውኃው ጉድጓድ አጠገብ ተመለከተ። ይህ ጉዞ ለያዕቆብ ከሕልሙ በኋላ አስደሳች ነበር ይላል አንዱ መተርጉም ሲጽፍ።

 ከእረኞቹ ጋር ለመግባባት ያህል ይመስላል አጎቱን ላባን ያውቁት እንደሆነ ቢጠይቅ እንደሚያውቁት በዝርዝር ነገሩት እንደውም ልጁም ራሔል አሁን በጎቹን ልታጠጣ እንደምትመጣ ነገሩት። ቀጥሎም ታድያ ለምን መንጎቻቸውን አጠጥተው እንደማይሔዱ ቢጠይቃቸው ችግራቸውን አስረዱት አንዲህ በማለት “እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን” ዘፍ. 29፡8

ይህንን ሲነጋገሩ የአጎቱ ልጅ ራሐል ደረሰች፣ባያት ጊዜ አለቀሰ፣ሳማት፣ ሰላምታ ተለዋወጡ። ለእረኞቹ የዘመናት ችግር የነበረውን ድንጋይን የማንከባለል ችግር ያዕቆብ ማንንም እገዛ ሳይፈልግና ሳይጠይቅ ድንጋዩን አንከባለለው። እረኞቹን መንጎቻቸውን አጠጡ። " ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች ባየ ጊዜ፥ ቀረበ ከጕድጓዱም አፍ ድንጋዩን ገለበጠ፥ የአጎቱን የላባን በጎችንም አጠጣ"  ይለናል። 

ይህ የያዕቆብ የተዘጋ የውኃ ጉድጓድ ትርጉም በቀደሙትም ሆነ የቅርብ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ መተርጉማን ሰፊ ቦታ ተሰጥቶት ተተርጉሟል። ይህውም፦ የእረኞችን መምጣት ይጠብቁ የነበሩት ሶስት እረኞች፦  ሕገ ልቡናንን፤ የሙሴ ሕግን፡ የነቢያትን ትንቢትን ይጠብቁ የነበሩትን እስራኤላውያንን ያመለክታሉ። አንድም እረኞች የነቢያት ምሳሌ ነበሩ። ይወርዳል ይወለዳል ብለው ትንቢት እየተናገሩ ተስፋ ሲያደርጉ፤ የመሲሁን መምጣት ሲጠብቁ የነበሩ መሆኑን ያሳያል።

በጉድጓዱ ላይ ተገጥሞ የነበረው ድንጋይ፤ በአዳምና በልጅ ልጆቹ ላይ የነበረውን መርገመ ነፍስ መርገመ ሥጋን ያመለክታል። ይኽንንም መስዋዕት ቢሰዉ ጸሎት ቢያደርጉ ከሰው ማራቅ አለመቻላቸውን ነው። ራሔል የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ስትሆን ያዕቆብ ሚስት  እድርጎ ወስዷታል። ይኽውም ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን  በሙሽሪት እንደመሰላት። እርሱ ሙሽራው ቤተክርስቲያን ሙሽሪት አድርጎ ተናግሮላታልና።  "ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ" ኤፌ 5፡25

በተጨማሪም ያዕቆብ ራሔልን ሲያይ እንዳለቀሰ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመስቀል ላይ ለዓለም ድኅነት "አባ ሥረይ ሎሙ" በማለት እስከ ሞት እንደተሰቃየ ምሳሌው ነበር።

ይኽንንው ቃል ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዝማሬው ሲያመሰጥረው " ወብዙኀን ኖሎት መጽኡ ወስዕኑ ከሲቶታ ለዕብን እም አፈ አዘቅት፤ እስከ ይመጽእ ያዕቆብ ዘክቡት ውስተ ኀቌሁ፤ ዘሀሎ ይሰጎ እም ሰብእ ከሠተ ወአስተየ  መርዔቶ፤  ወከማሁ መጽኡ ብዙኃን ነቢያት ወሰዕኑ ከሢቶታ ለጥምቀት እስከ ይመጽእ ዐቢይ ኖላዊ እም ሰማይ፤  ከሠተ ወአጥመቀ ብዙኀነ አሕዛበ በውስቴታ። መንክር ተአምሪሁ ለመድኃኒነ"   

ትርጉሙም " ብዙ እረኞች መጡ ፥ ከጉድጓዱ አፍ ድንጋዩን መክፈት (መገልበጥ) አልተቻላቸውም ። ከሰው ወገን ሰው የሚሆነው ጌታ በአብራኩ ያለ ያዕቆብ እስኪመጣ ድረስ ፤ እሱ ከፍቶ መንጋውን አጠጣ ። እንደዚሁ ሁሉ ብዙ ነቢያት መጡ፣ ጥምቀትን መመሥረት አልሆነላቸውም ፤  ደገኛው እረኛ ከሰማይ እስኪመጣ ድረስ፤   እርሱ መጥቶ (ጌታችን) ሥርዓተ ጥምቀትን መሠረተ፣ ብዙ አሕዛብን አጠመቀ የአምላካችን ተአምሩ ድንቅ ነው" ይላል።

በአጠቃላይ ቅዱስ ያሬድ ያዕቆብን የጌታ፤ እረኞችን የነቢያት፤ደንጊያ ጥንተ አብሶ (መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ)። ውኃውን ለድኅነታችን የሆነው ጥምቀት መሆኑን አመለከተ።

አባ ሕርያቆስ በውዳሴ ማርያም ላይ እመቤታችንን በሚስጢር ሲያመሰግን "ገነት ዕፁት ዐዘቅት ኅትምት " የታጠረች ተክል የተዘጋች የውሃ ጉድጓድ አንቺ ነሽ" ብሏታል። የሕይወት ውኃ የተባለ ጌታችን መድኅኒታችንን ያስገኘች የተዘጋች የውኃ ጉድጓድ ድንግል ማርያም ስትሆን  የተዘጋች ጉድጓድ መባሏ፤ ኅትምት  በድንግልናዋ መሆኗን ያመለክታል። ከእርስዋ የተገኘው ጌታ የዓለም ሕይወት ሆኗልና። ዮሐ 4፡14

የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
798 viewsወሰንየለው ባህሩ, 16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 20:03:30 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው
ታቦር ማለት ምን ማለት ነው
ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል
ሙልሙል ልምን ይታደላል
በቡሄ ወቅት ጅራፍ ለምን ይጮሃል
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የደብረ ታቦርን ተራራ ለምን መረጠ
በኢትዮጵያ የሚገኘው ደብረ ታቦር ለምን ስሙ በደብረ ታቦር ተሰየመ

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

የቡሄ መዝሙሮች በYouTube ለማግኘት

https://youtube.com/channel/UC3X56bMco4R7NmiQxOgySAg
https://youtube.com/channel/UC3X56bMco4R7NmiQxOgySAg
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘






𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
585 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:23:40 + ከታቦር ተራራ አትቅር +

"አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ። "
ማር 9: 3
/ሽራፊ ሃሳቦች ከደብረ ታቦር ንባብ/

የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን ለማየት የማንፈልግ ፣ በእኛ በኩል ያለፈን ነገር ብቻ የምናራግብ ፣ የሌለንበትን ነገር ጥሩም ቢሆን እንኳን ለምናጣጥል "በእኔ በቀር ባዮች" ትምህርቱ ድንቅ ነው።

ሌላ ማሳያም አለ ማቴዎስ ወንጌላዊው ስለ ራሱ ታሪክ ሲጽፍ "ማቴዎስ የተባለ ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ" ብሎ በኃጢአት ከተዘፈቀበት ሥራ ላይ ወደ ክርስትና እንደተጠራ በግልጽ ሲጽፍ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ማቴዎስ ያሉትን ሰው ስለ ቀድሞ የቀራጭነት ሥራው ሲጽፉ ግን ሌዊ የሚል ተለዋጭ ስሙን ተጠቅመዋል። ትሑቱ ማቴዎስ ግን በሌሎች ወንጌላውያን የተሸሸገ የቀድሞ የኃጢአት አኗኗሩን ለእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማሳያ እንዲሆን ስለፈለገ ጭራሽ በሐዋርያት የስም ዝርዝር ላይ "ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ራሱን ጠርቷል።

የሚገርመው ከቀራጭነት ከተጠራ በኋላ በቤቱ ታላቅ ድግስ ደግሶ ጌታችንን ከኃጢአተኞች ጓደኞቹ ጋር የተቀበለ መሆኑን በሌሎች ወንጌላውያን ሲጽፉ ማቴዎስ ግን ቀራጭነቱን አጉልቶ እንዳልጻፈ ሁሉ የግብዣው ነገር ደጋሹ እርሱ መሆኑን አድበስብሶ በመጻፍ አልፎታል።

★ ★ ★

ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ለእኛ" መልካም ነው የሚለው ቃል ድንቅ ነው። በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን መልካምነቱና ጥቅሙ ለእኛ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። የማንጠቅም ባሪያዎቹ ስሙን በአሕዛብ ዘንድ ከማሰደብ በቀር ለእርሱ ምን እንጠቅመዋለን። ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ያለው።
ስለዚህ ጴጥሮስ "ለእኛ መልካም ነው" አለ።

"ብትወድስ ሦስት ዳስ እንሥራ" አለ ፣ ጌታ ካልወደደ እንኳን ሦስት አንድ ዳስ መሥራት አይቻልም ፣ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ" ስለዚህ "ብትወድስ" አለ።

የዋሁ ጴጥሮስ ለእኔ ልሥራ አላለም ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐዋርያ ነኝ ብሎ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ከማክበር ወደ ኋላ አላለም። "አንተ ዓለት ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ" በተባለ ማግስት ለነቢያቱ ድንኳን ሊቀልስ የጠየቀ ከጴጥሮስ በቀር ማን አለ?

ከእግዚአብሔር አብ ግን "አትሙት" እስከማለት ለደረሰው ለነጴጥሮስ ንግግር "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል ትእዛዝ መጣ። ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ቃሉን ሳይሰሙ ዳስ መሥራት መጀመር አይቻልም።

በዚያ ላይ ጌታ የመጣው በደብረ ታቦር ድንኳን አስጥሎ ሊኖር ሳይሆን በቀራንዮ በተሰቀለበት በመስቀሉ ካስማ በደሙ ድንኳን ተክሎ ሊያስጠልለን ነው። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ "ጴጥሮስ ሆይ ለአንተ የፊቱን ብርሃን እያየህ በዚህ መኖር መልካም ነው ፣ እኛ ግን የምንድነው በተራራው ሲኖር ሳይሆን ወርዶ ፊቱን በጥፊ ሲመታ ነው" ብሎታል።

ጴጥሮስ የዋሁ "በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ" ላለው ለክርስቶስ ድንኳን ሊቀልስ ጠየቀ። በሰማይ "በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ድንኳን" ላለችው ሊቀ ካህናት ድንኳን ሊሠራ ለመነ። እዚህ አለ ሲሉት እዚያ ለሚገኘው ፣ በመንፈስ እየተነጠቀ አድራሻውን ለመወሰን ያስቸግር ለነበረው ኤልያስ እንዲቀመጥ ተስፋ አድርጎ ድንኳን ልሥራ አለ። እጅግ የተዋበችና በወርቅ በሐር ያጌጠችን የኦሪት ድንኳን ለሠራው ሙሴ ዓሣ አጥማጁ ጴጥሮስ ድንኳን ልሥራለት አለ። ሐዋርያት ነቢያቱን ሊያስተናግዱ የለመኑባት ደብረ ታቦር ፣ ሐዋርያት ነቢያቱን ለጌታ ቀኝ አዝማች ግራዝማች አድርገው በድንኳን አስቀምጠው እነርሱ እንደ ሎሌ ከደጅ ሊኖሩ የጠየቁ እነ ጴጥሮስ እንደምን ይደንቃሉ? ጴጥሮስ ሆይ አሁን በሰማይ ድንኳኖች ውስጥ እያገለገልህ ይሆንን? ደብረ ታቦርን አይተህ በደስታ "እንኑር" ያልከው ጴጥሮስ ሆይ የገነት ደስታ ስታይ ምን ተሰምቶህ ይሆን?

በእሳት ድንኳን ለመኖር ተስፋ የምናደርግ "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" የተባልን እኛስ ምንኛ የታደልን ነን?

★ ★ ★

በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል።

ከጌታችን በዚያ ተራራ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ነበረ። ሙሴ እንደምናውቀው ጽላቱን ተቀብሎ ሲወርድ ሕዝቡ "እባክህን ተሸፈንልን" ብለውት ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፍኖ ነበር። የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ሲወድቁ አይቶ በልብሱ እንዳይሸፈን ያበራው ፊቱ ብቻ ሳይሆን ልብሱም ነበር።

" አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ" ማር 9: 3
የሚለው ቃል ምንኛ የሚደንቅ ነው። በምድር ላይ ያለ አጣቢ ቢፈትግ ቢታገል የዚያን ያህል ሊያነጻው የማይችለው ነጭ እንዴት ያለ ነው? መቼም ሁላችን የምናውቀው ነጭ ነገር ሁሉ በምድር ላይ ባለ አጣቢ የታጠበ ስለሆነ እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ብቻ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምድር ያሉ አጣቢዎች ከሚያነጡት በላይ ልብስን ማንጣት ይችላል።

ይህ ቃል በኃጢአት እድፍ ልብሳችን ላደፈ ሁሉ መጽናኛችን ነው።

መቼም የምድር አጣቢዎች አቅማቸው ውስን ነው።
ቆሽሸን ያዩን ሰዎች ብንታጠብም አያምኑንም ፣ ቢያጥቡልንም በኅሊናቸው የሚያስቀሩብን ቆሻሻ አለ።
በሰው ዓይን አንዴ ቆሽሸህ አትገኝ እንጂ ከተገኘህ መቼም ነጭ አትሆንም። አንተ ግን የደብረ ታቦሩ ብርሃን መድኃኔ ዓለምን ብቻ "እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" በለው "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች። " ብሎ በገባው ቃል መሠረት ነጭ ያደርግሃል።

እርሱ ወዳለባት የቅድስት ቤተክርስቲያን ተራራ በንስሓ ከደረስክና በታቦር ያበራውን ብርሃኑን ካበራልህ ነጭ ትሆናለህ። ከዚያ "አጣቢ የማያነጻውን ያህል ትነጻለህ" ከአብ የባሕርይ ልጅ ከብርሃኑ ፀዳል ስትቀርብ አንተም በጥምቀት ያገኘኸው የጸጋ ልጅነትህ ያንጸባርቃል። ነጭ በሆንህ ጊዜ የሚያዩህ ሁሉ "በበጉ ደም ልብስህ መታጠቡን"ና ነጭ መሆኑን አይተው ይደነግጣሉ ፣ ሊሰሙህ ያልወደዱ ሁሉ ለባሕርይ ልጁ "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" ብሎ እንዳዘዘለት ለአንተም ጆሮ እንዲሠጡህ ያደርግልሃል።

አንተ ብቻ ከደብረ ታቦር አትቅር ፣ ካልሞትህ እንደ ኤልያስ ፈጥነህ ና ፣ በበደል ከሞትክም እንደሙሴ ተነሥተህ ና። ብቻ ወደ ደብረ ታቦር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለመምጣት ተስፋ አትቁረጥ ፣ እንደ ሙሴ ትሞታለህ እንጂ ምድረ ርስትን አታይም ብትባል ፣ እንደ ኤልያስ ትኖራለህ እንጂ ሞትን አታይም ብትባል ብቻ አንተ ከደብረ ታቦር አትቅር።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
https://t.me/akanim1wasen2
545 viewsወሰንየለው ባህሩ, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 06:02:18 “ንዑ ናስተብጽአ ለማርያም

 ኑና ማርያምን እናመስግናት

ነገረ ማርያም (Mariology) በቅድስት ቤተክርስቲያን ሰፊ ትምህርት ሲሆን፤ እመቤታችን በነገረ ድኅነት(soteriology) በነበራት ሱታፌ (ድርሻ) ምክንያት ነገረ ማርያም ከሁሉም ትምህርት ጋር የተያያይዘ ትምህርተ ሃይማኖት ነው። በተለይ በነገረ ሥጋዌ። ለዛሬ ቀዳሚት ሔዋንን እና ዳግሚት ሔዋን እመቤታችንን  በንጽጽር እናያለን።

የጽሑፌ ዓላማ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቀደሙት ቅዱሳን አበው አንደበት እና ትምህርት ማየት ሲሆን፤ ከዚኽ በፊት “ማርያም ማለት” በሚል ጽሑፌ የስሟን ትሩጉ ከመሠረታዊው ትምህርት ጋር ማስነበቤ ይታወሳል።

 ቅዱስ ጳውሎስ በቀዳሚ በቆሮንቶስ መልእክቱ ስለ ጌታችን መድኅኒታችን ሲናገር ይኽውም በቀዳሚው አዳም የሆነብንን ውድቀት፤ መረገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ስላዳነን ሲናገር “ሁለተኛ አዳም” ብሎታል። “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና።ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና” 1ቆሮር.15:21-22 

በዘፍጥረት ላይ  ቀዳሚ ሔዋን ለሰው ውድቀት ምክንያት እንደሆነች እናነባለን። በመሆኑም ኢየሱስ ክርስቶስ የሁለተኛውን አዳምን ቦታ ከወሰደ ማለትም ሁለተኛ አዳም ከተባለ የሔዋንን ቦታ ማን ወሰደ የሚለው ጥያቄ ይነሳል።

የጥንት ክርስቲያኖች እንደሚያምኑት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  ይህንን ቦታ ትወስዳለች ይላሉ። ቀዳሚት ሔዋን ሰይጣንን አመነች፤ አዳምን ወደ ኃጢአት መራች ። ዳግሚት ሔዋን የመልአኩን ቃል አመነች። አምላክን በመውለድ መድኅኒትን ለዓለም ሰጠች ። ዳግሚት ሔዋን የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ የቀደሙት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት የገለጡበትና ያስተማሩበትን መንገድ በጥቂቱ እንግለጽ።

ሰማዕቱ ጀስቲን (100-165) መ/ክ/ዘ

ድንግል በምትሆን በቀዳሚት ሔዋን (ሔዋንን ከመውለዷ በፊት ማለት ነው)  የእባቡን ምክር ጸንሳ አለመታዘዝና ሞትን አመጣች። ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግሊቱ ሰው ሆነ። በዓለም የነበረውን አለመታዘዝ ወደ ቀዳሚ ክብሩ መለሰችው ይላል። እመቤታችን ተስፋን ተቀበለች። የመልአኩን ቃል በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ወደ እርሷ መጣ፤ የአርያም ክብር ከበባት፤ ከአንቺ የሚወለደው የእግዚአብሔር ልጅ ነው ባላት ጊዜ እንደቃልህ ይሁንልኝ በማለት መለሰችለት። (Dialogue with Trypho, 100, A.D. 160)

ቅዱስ ኤሬኔዎስ (ከ130-201 ዓ.ም)

መናፍቃንን በተቃወሙት ጽኁፉ “ቀዳሚ ሔዋን ባለመታዘዝ ታሰረች (ማእሰረ ሔዋን)። የቀደመው የሔዋን አለመታዘዝ እስር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  በመታዘዝ ተፈታ(የባርያይቱን መዋረድ አይቷልና እንዳለች) ጸሎተ ማርያም። ሔዋን በሳተው (መልአክ) እባብ ተመርታ ከእግዚአብሔር ፊት ተሰደደች፤ ዳግሚት ሔዋን ድንግል ማርያም ከመልአኩ ጋር በተነጋገረች ጊዜ ለዘላለማዊ ደስታ ማሰርያ ሆነች። ለቃሉም ታዛዥ ሆነች ። ድንግል ማርያም ለቀዳሚት ሔዋን ካሳ ሆነች በሔዋን ምክንያት የሰው ዘር በሞት ማሰሪያ ተይዞ፤ በዳግሚት ሔዋን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  ምክንያት ዳግም ዳነ። የሔዋን ያለመታዘዝ ሚዛን በተቃራኒው በድንግል ማርያም ተስተካከለ” ይላል (Against Heresies, III.22.4, A.D. 180)

ተርቱልያን (ከ160-220 ዓ.ም›)

ሔዋን ገና ድንግል ሳለች የጠላትን ማጥመጃ ቃል ወደ ጆሮዋ በገባ ጊዜ፤ የሞትን ግድግዳ ገነባ። በዳግሚት ሔዋን (እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም) በእግዚአብሔር ቃል ሕይወት ተመሠረተ። በሰው ዘር የሚተላለፈው ኃጢአት ያለወንድ ዘር በመጽነስ ወደ ድኅነት አመጣችው።  የጠብ ግድግዳ ፈረሰ። ሔዋን አባቡን እንዳመነች እመቤታችን መልአኩን አመነች። ሔዋን የእባቡን ቃል በማሕጸን አልጸነሰችውም፤ ነገር ግን የሐዘን እና ከገነት የመሰደድ ዘር ሆነባት በክፋት የሚጣሉ ልጆችን ወለደች (ቃየን አቤልን መግደሉን ሲያስታውስ)። እመቤታችን በተቃራኒው እስራኤልን የሚያድነውን  ወለደች ። በሥጋ የገዛ ወገኖቹ ግን ሰቀሉት። (The Flesh of Christ, 17)

ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት (213-270 ዓ.ም)

የሔዋንን አለመታዘዝ ሳስብ አለቅሳለሁ፤ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ፍሬ ሳስብ እንደገና እታደሳለሁ። የማይሞተው ወደ እኛ መጣ፤ የማይታይ፡ የማይመረመር፤ ከዘመናት በፊት የብርሃናት ብርሃን የአብ የባህርይ አንድያ ልጁ የእግዚአብሔር ቃል ከእመቤታችን ሥጋን ለብሶ የሰው ዘር ከኃጢአት ፡ከብልየት(ከእርጅና) ያድሰው ዘንድ ዳግማይ አዳም በእመቤታችን እቅፍ ሆነ (Homily Concerning the Holy Mother of God Ever-Virgin, 1)

ቅዱስ ጄሮም

ሞት በሔዋን በኩል መጣ። ነገር ግን ሕይወት በድንግል ማርያም በኩል መጣ (Epistle 22, 21)

ቅዱስ ኤፍሬም (306- 373 ዓ.ም)

በሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ፤ ዳግመኛም በድንግል ማርያም  ተከፈተልን። (ወዳሴ ማርያም ዘሐሙስ)

አውግስጢኖስ (354-430 ዓ.ም)

ጌታ ወንድ ሆኖ መጣ ከዚህ ጀርባ ትልቅ ምስጢር አለ።ሞት በሴቲቱ በኩል ስለገባ ነው ይላል።
 እንግዲህ የቀደሙት ሊቃውንት እመቤታችን በነገረ ድኅነት ውስጥ ከቀዳሚ ሔዋን ጋር በማነጻጸር የተረጎሙበትን በአጭሩ መረዳት ያስፈልጋል። 

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
954 viewsወሰንየለው ባህሩ, 03:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 20:40:03 ያዕቆብ ያየሽ መሰላል አንቺ ነሽ

ያዕቆብ የአብርሐም ልጅ ነው። ያዕቆብ የስሙ ትርጉም "ተረከዝ ያዥ" ማለት ነው ። የወንድሙን እግር ይዞ ከማሕጸን ስለወጣ። ዘፍ. 25  ከወንድሙ በነበረው ጠብ ከሶርያ ምድር ተነስቶ ሸሸ። ያዕቆብ ከወንድሙ ተጣልቷል፣ አባቱን አታልሎ ብኩርናን ተቀብሏል። በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ ውስጥ እጅግ ደስ ከሚያሰኙት ምስጢራዊ ትርጉሞች ከተተነተኑት መካከል ያዕቆብ በሕልሙ ያየው መሰላል አንዱ ነው። 

ያዕቆብ ከሶርያ ተነስቶ ሲሔድ ሎዛ ሲደርስ  በመንገድ ሳለ ፀሐይ አዘቅዘቀች፤ ያዕቆብም የቀን ጉዞውን ድካሙን ሊከፍል ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ። ያዕቆብ አስደናቂውን ሕልም ተመለከተ። ይኽ የያዕቆብ ሕልም እጅግ አስገራሚና በቀደምት ሊቃውንትም ጥልቅ ምስጢርና ትንታኔ ተሰጥቶበታል። 

ያዕቆብ ያየው ድንጋይ ተንተርሶ ሲሆን ተዘርግቶ ያየው መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ይደርስ ነበር። በመሰላሉ ከላይኛው ጫፍ እግዚአብሔር አለበት። በመሰላሉ መላዕክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። "ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር" ይላል። ዘፍ. 28:12

ይኽንን ቃል ከጥንታውያኑ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት  እንዴት እንደተረጎሙት እንመልከት፡-

አርጌንስ (Origen)፦  ዘፍጥረትን በተነተነበት መጽሐፉ ያዕቆብ ምዕመናንን ሲወክል መሰላል በመንፈሳዊ ሕይወት ያለን እድገት ያሳያል ይላል። ይኽንን ሲያብራራም መሰላል ደረጃ እንዳለው ሁሉ ክርስትናም እንዲሁ እያደገ የሚሔድ ነው ይላል። ምጽዋት ስትሰጥ መሰላሉ በአንድ ደረጃ ከፍ ይላል። ቤተ ክርስቲያን ሔደህ ምስጢራትን ስትፈጽም መሰላሉ በአስር ደረጃ ከፍ ይላል ብሎታል። Gregory of Nazianzus, Homily n. 43 (Funeral Oration on the Great S. Basil), 71

 ይኽንን ኅሳቡን የሚጋራው ቅዱስ ጄርምም በጎ ምግባራት ባደረግህ ጊዜ እንዲሁ ወደ ላይ (ወደ እግዚአብሔር) ማደግ ትጀምራለህ።  አርጌንስ ይቀጥልና ምግባርን እየጨመርክ በሔድክ ጊዜ ብርሃን ወደሆነው እግዚአብሔር እየተጠጋን ነው። ከሞት በኋላም የነስፍ እድገቷ አይቆምም ይለናል።

 ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ሲናገር ይኽ መሰላል ወደ ላቀ መንፈሳዊነት ማደግን በተለይም በተባሕትዎ (Asetic life) መኖርን ያሳያል ሲል፤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ጳውሎስን አብነት እድርጎ ደግሞ መሰላሉ በሰው እጅ ባልተሰራችው ሰማያዊ ቤተ መቅድስ የሚያደርስ ነው ይለናል። Gregory of Nazianzus, Homily n. 43 (Funeral Oration on the Great S. Basil), 71

የሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሶርያዊው አፍርሐት የተባለው በተለይ በነገረ ማርያም ላይ ሰፊ ጽኁፍ በመጻፉ ሲታወቅ በተለይም ፡ ዓይነ ልብ ( the luminous eye)በሚባለው ጽኁፉ እናውቀዋለ። ይኽንን መሰላል ሲተረሩም መሰላል የክርስቶስ መስቀል ነው ይላል። “the ladder of Jacob’s dream symbolizes the cross of Christ” ይህውም መስቀል ከታች ከምድር (ከውድቀት) ወደላይ ወደሰማይ (ወደ እግዚአብሔር) አድርሶናል። በማለት አመስጥሮታል። 

የቅርብ ጊዜያት የነገረ መለኮት ምሑራን (contemporary theologian) በመጀመሪያ እግዚአብሔር ያዕቆብን ያስተማረው ከራሱ ሕይወት በመነሳት ነው። ይኽውም ወንድሙን አታሎ፣ አባቱን ዋሽቶ ነው የመጣው ስለሆነ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነትን አሻክሮ ነበር ። ስለሆነም እግዚአብሔር መንገዱን እንዲያስተካክል ነው የነገረው። ያዕቆብም መንገዱን ቃል በመግባት አስተካክሏል። ይህም የተነሳሂን ሕይወት ያሳያል ብለውታል።

 የያዕቆብ ሕልም የሕይወቱ መቀየሪያም ክስተት ነበር። እግዚአብሔርንም ለማገልገል ቃል የገባበት ነበር።  ለያዕቆብም የተነጋገረው እግዚአብሒር ለኃጢአቶኞች አዛኝ እና ይቅር ባይ መሆኑን አሳይቷል  ይላሉ። (sacred symbols that speak p 62) 

 አውግስጢኖስም (Augustine) መሰላልን  በተለየ መልኩ ሲያብራራ መሰላል ቤተ ክርስቲያን ናት ይላል። (lecture or tractate st. john, tractate 7) 

ቅዱስ ጄሮም ይቀጥልና ያዕቆብ የተንተራሰው ድንጋይ ክርስቶስ ነው ይለናል።  ይኽንንም መጽሐፍ ቅዱስ በመዝሙረ ዳዊት የተነገረው ትንቢት በጌታም ትምህርት እንዲሁም በሐዋርያት ስብከት በተደጋጋሚ ስለ ማዕዘን ራስ ድንጋይ ተነግሯል " ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ" እንደተባለ። መዝ.118፡22  ማቴ.21፡42

የማዕዘን ራስ ድንጋይ ዋና ዓላማው የቤቱን ላይና ታች አጋጥሞ ማቆም ነው። የተጣላውን የሰውን ዘር ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቆ  አንድ አድርጓልና። ቅዱስ ጴጥሮስንም ስለ ጌታ በመሰከረው ትምሕርት "እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። በማለት አለትነቱን አረጋግጦልናል" ማቴ 16፡ 18

የቢዛንታይን ቤተ ክርስቲያን አባቶች  የያዕቆብ መስላል እመቤታችን ናት በማለት ይተረጉማሉ። ይኽንን ትርጉም ሁሉም ኦርቶዶክሶች ይስማማሉ ። ቅዱስ ኤፍሬም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ላይ "አንቺ የያዕቅብ መሰላል ነሽ" ይላታል።

 "አንቲ ወእቱ ሰዋስው ዘርእየ ያዕቆብ እምድር ዘይበጽሕ አስከ ሰማይ" ከምድር እስከ ሰማይ ተተክላ መላዕክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ አላት። ይኽም መሰላል የወርቅ ነው ምሳሌውም  ቅድስናዋን ንጽሕናዋን ያመለክታል።

 ከምድር እስከ ሰማይ መድረሱ አምላክን እና ሰውን ያገናኘች መሰላል (ቃል ሥጋ የሆነባት) መሆኗን ያመለከታል። ያዕቆብ የተንተራሰው ድንጊያ የእመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ጸንታ መገኘቷን። አምላክ ሰው ከሆነ በኋላ መላዕክት ለምስጋና ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ መሆናቸው አሳይቷል በማለት ያብራራዋል።  (ውዳሴ ማርያም ትርጉም)

 አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ብለው መውጣት መውረዳቸውን አስረጅ ነው። ጌታችንም ለናትናኤል  "እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ አለው"  ብሎታል። ዮሐ. 1፡52

እመቤታችን ሰውና አምላክን ያገናኘች መሰላል ስትሆን የሰውን ልጅ በምልጃዋ ወደ እግዚአብሔር በማቅረብ ወደ መንግስተ ሰማይ የሚገቡበትን ጸጋ ያገኛሉ። ድንግል ሆይ አንቺ መስለላላችን ነሽ።

ለጥልቅ ንባብ Ancient , Christian commentary on scripture old testament vol 2 p 186 

የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን

መ/ር ንዋይ ካሳሁን

https://t.me/akanim1wasen2
828 viewsወሰንየለው ባህሩ, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 05:23:43 ቅበላ ዓላማው ምንድን ነው?

ስለ ቅበላ ያለን አመለካከት በልማዳችን ውስጥ የተንሸዋረረ ነው። ከጾም ጋር ተያይዞ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ከሚፈጸሙ ተግባራት መካከል በአጽማት መግቢያ የሚደረገው የአቀባበለ ሥነ ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት በራሱ መጸሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት ያለውና በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያንም የተለመደ ትውፊታዊ ቅብብሎሽ ያለው ሥርዓት ነው። ይህ ግን አሁን ከምንፈጽመው የቅበላ ሥርዓት የተለየ ነበር። ጥቂት ማሳያዎችን እንመልከት።

1:-በመጸሐፍ ቅዱስ አይሁድ ቀዳሚት ሰንበት ከመግባቷ በፊት በዋዜማው የተለየ አቀባበል ያደርጉ ነበር። ዓርብ ፀሐይ ሲገባ ካህኑ ደውል
ይደውላሉ አሊያም በቤት ያለ የቤቱ አባወራ የሰንበት
መግቢያ ሰዓት መቃረቡን ድምጽ በማሰማት ያሳውቃል፡፡ በአካባቢው ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በአንድ ላይ ሆነው ወደ ፀሐይ መውጫ ይሰግዳሉ፡፡ ጸሎት ይደረጋል፡፡ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል፣አሥርቱ ቃላት ሌሎችም ንባባት ይደገማሉ፡፡ ማብራት ተይዞ “ዕለተ ሰንበት እንኳን
ደህና መጣሽ” ብለው ያከብሯታል፡፡ ከሦስት ሰዓት በኋላእራት ይበላሉ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ እግዚአብሔርን
ሲያመሰግኑ ያድራሉ፡፡" ከዚህም ጎን ለጎን ከግብጽ ባርነት መውጣታቸውን ምክንያት በማድረግ ለሚያከብሩት የፋሲካ ሏዓል በታዘዞት መሠረት ጠቦት አዘጋጅተው አቀባበል ያደርጉለት ነበር። ኦዘጸ 25:12

2:-ትክለኛው ቅበላ ግን ከሕሊና ዝግጅት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው። ቀደምት አበው አጽዋማት ከመግባታቸው በፊት ለቤተመቅደስ አገልግሎት የሚሆኑ መገልገያዎችን ያዘጋጃሉ እነርሱም እራሳቸውን ለአገልግሎት ያዘጋጃሉ። ምእመኑም ሱባኤውን የሚያሳልፍበትን ቦታ መርጦ ይጠብቃል ንሰሐ ገብቶ እራሱን ለቅዱስ ቁርባን ያዘጋጃል። የቀማውን ይመልሳል የበደለውንም ይክሳል። ማጠናቀቅ ያለበትን ተግባረ ሥጋ ፈጽሞ ይጠብቃል። በጥቅሉ በጾም ወቅት ሊሟሉ የሚገቡ ውጫዊና ውስጣዊ ዝግጅቶችን በዋዜማው ይፈጽማሉ። ካገኙ በመጠኑ መቀበያ የፍስክ ምግብ ይመገባሉ ካላገኙ ግዴታ ስላልሆነ ጥሬ ቆሬጥመው ውሀ ተጎንጭተውም ቢሆን ይቀበሉታል።

3:-አሁን ያለው ደግሞ ፍጹም የተለየ አቀባበል ነው። በጾሙ ላይ ተሳትፎ የሌለውም ያለውም በጠቅላላ የህሊና ዝግጅት የለውም አቀባበል ሲባል ቀጥታ ግንኙነት ያለው ከመብላትና ከመጠጣት ጋር ይመስለዋል። በየቦታው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሲበላ ሲጠጣ ሲያልፍም ወዳልተገባ ሥጋዊ ስሜት ውስጥ ይገባል። ብዙ ነዳያን የሚቀምሱት ባጡበት ዘመን ከገደብ ያለፈ የአመጋገብ ሥርአት በቅበላ ወቅት የተለመደ ነው። ይህ ከክርስትናው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለውም ሰው ለፈቃደ ስጋው ሲያደር የፈጠረው እንጂ። እግዚአብሔር ለቅበላው ስለበላነው እና ስላልበላነው ጉዳይ ሳይሆን ሚያሰበው የእኛ በኃጢአት መኖር መሆኑን ልብ እንበል። ስጋ በልቶ የተቀበል ቆሎ በልቶ ከተቀበለው ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ብልጫ የለውም። ከሁሉ ሚያሳዝነው በቅበላውም በፍቺውም የፍስከ ምግቦች ለመብላት የሚሰለፉት ማይጾሙት መሆናቸው ነው። ስለዚህ በቅበላ ጊዜ "የግድ እነዚህን ካለበላችሁ የሚል ህገ የለም ያገኘም በመጠኑ እና በማያስነውር መልኩ ቢመገብም ነውር የለውም። በአጽማት ስጋ መብሊት አለመብላት ግዴታ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ዝግጅቶች ምናደርግበት ነው።

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም
1.2K viewsወሰንየለው ባህሩ, 02:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ