Get Mystery Box with random crypto!

Meribah Times - መሪባ ታይምስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ meribahtimes — Meribah Times - መሪባ ታይምስ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ meribahtimes — Meribah Times - መሪባ ታይምስ
የሰርጥ አድራሻ: @meribahtimes
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 997
የሰርጥ መግለጫ

በአገራችንና ቀጠናችን ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን በዚህ ቴሌግራም ገፅ እንጋራለን !!!
This channel provides political, economical and social information, analysis on Ethiopia and the horn of Africa!!!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-12 23:32:46
113 views20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 23:32:40 በክልል ልዩ ኃይሎች ጉዳይ ተጨማሪ ውይይት እንዲደረግ ኢሰመኮ አሳሰበ

የጸጥታ ሀይሎችም በተቃዋሚዎች ላይ ያልተመጣጠነ ሀይል እንዳይጠቀሙ ኢሰመኮ አሳስቧል

መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን "መልሶ ለማደራጀት" የጀመረውን ስራ ተከትሎ የተፈጠረውን ችግር በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን(ኢሰመኮ) አሳሰበ።

ኢሰመኮ ከሰሞኑ የክልል ልዩ ሀይሎችን በሚመለከት በተፈጠሩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል።

ኢሰመኮ የልዩ ሀይሎችን መልሶ የማደራጀትን ውሳኔ ትግበራ በውይይትና የሰዎችን ሰብአዊ መብቶች አደጋ ላይ በማይጥል ሁኔታ ሊከውን ይገባል ብሏል ኢሰመኮ።

ኢሰመኮ መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራልና በክልል መደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ መልሶ ለማደራጀት ያሳለፈውን ውሳኔና ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ የጸጥታ መደፍረስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን በተመለከተ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ኢሰመኮ "በቆቦ፣ በባሕር ዳር፣ በወረታ፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረ ብርሃን እና በመራዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ መንገድ መዘጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥጫዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች በጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎችና ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ሠራተኞችን ጨምሮ የሲቪል ሰዎች ሞት እና የአካል ጉዳት" አስከትሏልም ብሏል። 

በሌላ በኩል በእነዚህ ከተሞችና ሌሎችም አካባቢዎች በተፈጠረው ውጥረት፣ አለመረጋጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እና የእንቅስቃሴ እገዳዎች ምክንያት በነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና ሥራ ላይ እንቅፋት እንደፈጠረም ኮሚሽኑ ገልጿል።

አጠቃላይ ችግሩና የጸጥታው ሁኔታ አስቸኳይ እልባት ካላገኘ ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሥጋት በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን በምክክርና በመግባባት እንዲፈቱ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

ኢሰመኮ አክሎም በተለይም አጠቃላይ የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታው የፈጠረውን ሥጋትና የአለመተማመን ስሜት ከግምት በማስገባት መንግሥት የፖሊሲ ውሳኔውን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ለሚመለከታቸው ሁሉ በትዕግሥትና በጽሞና የሚያስረዳበትን ሁኔታ ሊያመቻች ይገባልም ብሏል።

የጸጥታ አካላት ያልተመጣጠነ እና ሕይወት የሚያጠፋ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ፣ መንግሥት ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ እንዲሁም ሁሉም ሰው ሐሳቡን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲገልጽ ኢሰመኮ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

ኢሰመኮ ከመደበኛው የክትትል እና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ በማነጋገር እና ምክረ ሐሳቦችን በመስጠት የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልጿል። ይህ ወሳኔ በአማራ ክልል ከህዝቡ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) እና ኢዜማ የልዩ ኃይሎችን አደረጃጀት ማፍረስ ወቅታዊ አይደለም ሲሉ የመንግስትን ውሳኔ ተቃውመዋል።

አልአይን

@MeribahTimes
113 viewsedited  20:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:56:04 የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ፤ በባህር ዳር ከተማ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ገለጹ

“አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ዛሬ አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በመከላከያ ሰራዊት አባላት ተይዞ መወሰዱን የዓይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ስለ ጋዜጠኛው መያዝ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል። ጋዜጠኛው የስራ አመራር ቦርድ አባል የሆነበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበርም በተመሳሳይ ስለ ዳዊት መያዝ እስካሁን መረጃ እንደሌለው አስታውቋል።

ጋዜጠኛ ዳዊት ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 4፤ 2015 አመሻሽ ላይ በመከላከያ ሰራዊት አባላት የተያዘው፤ በባህር ዳር ከተማ በሚገኘው ሆምላንድ ሆቴል ከጓደኞቹ ጋር “ሻይ እየጠጣ” ባለበት መሆኑን የዓይን እማኞቹ ገልጸዋል። ጋዜጠኛውን ወዳልታወቀ ቦታ የወሰዱት የመከላከያ ሰራዊት የኮማንዶ አባላት በሁለት “ፓትሮል” ተጭነው የመጡ መሆናቸውን የጠቆሙት የዓይን እማኞቹ፤ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ “አንተን እንፈልግሃለን” ብሎ ዳዊትን ይዞት ወደ ተሽከርካሪዎቹ እንደወሰደው አብራርተዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባሉ ዳዊትን ከጓደኞቹ “ነጥሎ” ከወሰደው በኋላ፤ ከሆቴሉ ቅጥር ግቢ ውጭ ከቆሙት ተሽከርካሪዎች ወደ አንደኛው ውስጥ ሲገባ መመልከታቸውንም እማኞቹ አስረድተዋል። ሆኖም በሰዓቱ “ተደናግጠው ስለነበር” በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ ያሉት የመከላከያ ሰራዊት አባላት አጠቃላይ ቁጥር ማወቅ አለመቻላቸውንም አክለዋል።

ኢትዮጵያን ኢንሳይደር
183 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:03:44
#Breaking

ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው በመከላከያ ኮማንዶ ታፈነ

ዳዊት በጋሻው ባህርዳር ከሚገኘው ሆምላንድ ሆቴል ዛሬ ከቀኑ 11:50 ላይ ከጓደኞቹ ጋር ሻይ እየጠጣ በነበረበት ሰዓት እንደወሰዱት ታውቋል።

ጋዜጠኛው የት እንደተወሰደ እስከአሁን ማወቅ አልተቻለም።

የጋዜጠኛው መታፈን፣መንግሥት በሀገር አቀፍ ደረጃ በብሔራቸው አማራ የሆኑ ጋዜጠኞችን እና የፖለቲካ መሪዎችን እየለየ የማፈን ዘመቻ የመጀመሩ ምልክት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።

@MeribahTimes
198 viewsedited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:12:57 #ጥንቃቄ
#Alert

መከላከያ ሠሞንኛው ህዝባዊ እምቢተኝነትና ተቃውሞ በተደረገባቸው የመላው አማራ ክልል ከተሞች "ተፅዕኖ ፈጣሪና አስተባባሪ ናቸው!" የተባሉ ወጣቶችን ስም ዝርዝር በመዋቅራዊ አመራሮች በኩል ተዘርዝሮ  እንዲሰጠው እየጠየቀ ይገኛል፡፡ ደብረብርሃንን የመሠሉ ከተሞች ላይ የነውሩ ተባባሪ የሆኑ አመራሮች መኖራቸውን መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ እቅዱ ግን በመላው የአማራ ክልል ከተሞች ነው፡፡

ይህ ሌላኛው እልቂትና ትርምስ መፍጠሪያ አጀንዳ መሆኑ ነው! ይህ አሁንም ክልሉ እንዳይረጋጋና አማራጭ መፍትሄዎች ተግባራዊ እንዳይደረጉ የተወጠነ ሌላኛው የሴራ አጀንዳ ነው፡፡

መላው የአማራ ክልል የዞን ፤ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች በዚህን አይነቱ እጅግ አደገኛ መንገድ ውስጥ  ባለመግባት ከታሪካዊ ተጠያቂነት ራሳቸውን ማራቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

እስርና ግድያ ህዝባዊ ትግልን  ይበልጥ ያቀጣጥለዋል እንጂ አይቀለብሰውም፡፡ ነገርግን ይህ መንገድ ህዝቡ ከታችኛው አመራር ጋር እንዲጋጭና የእርስበርስ መተላለቅ እንዲፈጠር ለሚያደርግ የተጠነሰሰ አደገኛ የጥፋት መንገድ ነው፡፡

ይህ በደርግ ዘመን "ኢህአፓ ወዘተርፈ " እያሉ ወጣቶችን  ጠቁመው ሲያስረሽኑ ከነበሩት የዘመናችን የጥቁር ታሪክ አካላት ጋር የሚስተካከል ጉዳይ ነው፡፡

በመላው አማራ ክልል የሚፈፀም እስር ካለ ፥ በቀጥታ የአመራሩ እጅ እንዳለበትም መገንዘብ ያስፈልጋል!

ሠዎቹ ግን የሚረባረቡት  ይቺን ሀገር ከዚህ በላይ ወደምን አይነት አዘቅት ለመዝፈቅ ነው?

#ሼር አድርጉት!

@MeribahTimes
227 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:11:14
ወንጀሉን በሥሙ ጥሩት
የአማራ ሕዝብ በኦህዴድ-ኦነግ አገዛዝ በዚህ መልኩ በገዛ ሀገሩ እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ... ያለው በዜግነቱ የተነሳ ሳይሆን አማራ ስለሆነ ብቻ ነው። ይሄ የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ወንጀል ነው። ይሄ በድፍኑ "የዜጎች መፍናቀል" ብለህ የምትናገርለት ወይም የምትዘግበው ዜና ሳይሆን የአማራዎች መፈናቀል፣ መሰደድ ነው።
214 views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 13:06:27 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔር እየለየ የሚፈታና የሚወነጅል ዳኛ ባለማግኘታቸው "ሌባ ዳኛ" በሚል በይፋና በጅምላ ከፈረጁ በኋላ ሀሳባቸውን የሚጋሩ ሀላፊዎችን ለጠቅላይና ከፍተኛ የፌዴራል ፍርድቤቶች ሾመዋል።

ለህሊናቸው የሚሰሩ ደኞችን በማስገደልና በመወንጀል ከስራ ውጭ በማድረግ ጽንፈኛ ብሔርተኞችን በማስመደብ ፍትህን መቅበር ጀምረዋል።

ለዚህ ምስክር የሚሆነው ከአዲስ አበባ ኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ከተከሰሱ ግለሰቦች ውስጥ ከአምስቱ አራቱ በብሔር ተለይተው በፍርድ ቤት ነጻ መባላቸው ሊሆን ይችላል።

ይህን ብይን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4፤ 2015 የዋለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ችሎት ነው። ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፤ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ” መሆኑን ገልጿል። በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት አቶ ኩምሳ ቶላ ይገኙበታል።

መዲድ ኡጁ
287 viewsedited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 12:51:18 ትጥቅ መፍታት ያለበት ማን ነው?

ኦሮሚያ ውስጥ ትናንት በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ተፈፅሟል። በተጠና መልኩ ከወለንጭቲ ወደ መተሃራ በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጥቃት ደርሶባቸዋል።  ጥቃቱ በተጠና መልኩ የተደረገ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን 50 ያህል የፌደራል ፖሊስ አባላት ተገድለው፣ ከ40 ያላነሱ ቆስለዋል። ከተገደሉት መካከል አመራሮችም እንዳሉ የተገለፀ ሲሆን መሳርያዎቻቸው ተወስደዋል።

ኦነግ ሸኔ ተብሎ የሚነገርለት የክልሉ መዋቅር የሚደግፈው ኃይል ትጥቅ ሳይፈታ ነው የሌሎቹ ክልሎች በተለይም የአማራ ልዩ ኃይል ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ይጠቃለል የሚሉን።

@GetachewShiferaw

@MeribahTimes
280 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:48:17
የወያኔ ጦር አማራን ለመግጠም አሁንም በዋሻዎች ውስጥ እንደመሸገ ስለመሆኑ ራሳቸው ወያኔዎች በግልጽ እየነገሩን ነው። ይህ የትዊተር ልጥፍ ባለፈው እነ ጌታቸው ረዳ በአዲስአበባ ጉብኝት እያደረጉ በነበሩበት ጊዜ አንድ የTDF አባል ዋሻ ውስጥ እንዳሉ የገለጸበት ትዊት ነው።

የአማራ ህዝብና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ የአማራ ልዩ ኃይልን የማፍረስ ተግባር መቃወም አለበት። አለበለዚያ ነገ ከዛሬ የከፋ የኦሮሞ አገዛዝ ሰፍኖ በቀላሉ ማላቀቅ የማይቻል የጭቆና ቀንበር በህዝብ ላይ የሚጫን ይሆናል።

#GranChico

@MeribahTimes
290 views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 07:58:16
ታማኝ በየነ ዝምታውን ሰበረ

"ለህዝባዊ እንቢተኝነት ተዘጋጁ!" ፦አክቲቪስትና አርቲስት ታማኝ በየነ

"ከህወሓት የኮረጃችሁት በበላይነት ደፍጥጦ መግዛት የሚባል አስተሳሰብ አያዋጣም። ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሶማሊ፣ ሲዳማ፣ አማራ ጋር መሬት አለን እያላችሁ ከእያንዳንዱ ክልል ጋር የመሬት ጥያቄ እያነሳችሁ በጉልበት ሁሉንም እንገዛለን  የሚባል አስተሳሰብ አያዋጣም። ከህወሓት ተማሩ። የተወሰነ ጊዜ በስካር መንፈስ ልታደርጉት ትትላላችሁ። ነገ ለሁላችንም ልጆች የማትሆን ኢትዮጵያ ነውጥ በትናችሁ የምትሄዱት።

ኢትዮጵያውያን 'እንቢ' በሉ! አብሩ! ተነጋገሩ! መብታችሁን ለማስከበር አንድ ላይ ቁሙ! ለህዝባዊ እንቢተኝነት ተዘጋጁ

መንግስት ውሳኔውን ቀልብሶ፣ ሁኔታዎችን በሰላማዊ መንገድ ነገሩ እንዲፈታ ካላደረገ የሚመጣው ጦስ በታሪክ የሚያስጠይቀው ነው።"

@MeribahTimes
311 viewsedited  04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ