Get Mystery Box with random crypto!

Dr. Won(Dental consulting)

የቴሌግራም ቻናል አርማ merhshewamene — Dr. Won(Dental consulting) D
የቴሌግራም ቻናል አርማ merhshewamene — Dr. Won(Dental consulting)
የሰርጥ አድራሻ: @merhshewamene
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 206
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ጥርስዎ የምክር አገልግሎት ቢፈልጉ፣ ስለ አፍ ጤንነት ማወቅ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር፣ ከቤትዎ ሳይወጡ በስልክ ብቻ የጥርስ ሀኪም ማናገር ቢፈልጉ፣ ወይም አቅመ ደካማ የቤትሰብ አባልዎን በቤት ውስጥ ማሳከም ቢፈልጉ...0924138598/0911642527 ዶ/ር ወንዳጥር ጌታነህ ብለው ይደውሉ...በምችለው ሁሉ አግዝዎታለሁ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-11 17:21:35 -የህጻን ልጅ ጥርስ መቦርቦር የተለመደ እና በማንኛውም ልጅ ጥርስ ላይ ሊታይ የሚችል ነው

-አንድ ህጻን ከተወለደ ከ6ወር ጀምሮ የወተት ጥርስ ሊያበቅል ይችላል

-አንድ ህጻን አንድ የመጀመሪያ ጥርሱን ወይም ጥርሷን መብቀል ሲጀምር በንጹህ ለስላሳ ጨርቅ እና በንጹህ ውሀ ብቻ በቀን ሁለት ጊዜ ከ1ደቂቃ ላልበለጠ መጸዳት መጀመር ይኖርበታል

-አንድ ህጻን የእርሱን ጥርስ በራሱ ማጽዳት ወይም መቦረሽ እስኪችል ድረስ ቤተሰብ ተከታትሎ የህጻኑን ጥርስ መቦረሽ እና ልጁም ባህል እንዲያደርገው ማለማመድ ይኖርበታል

-የማንኛውንም ህጻን ልጅ ጥርስ ተከታትሎ በማጽዳት ሊከሰት የሚችለውን የጥርስ መቦርቦር በእጅጉ መቀነስ ብሎም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መከላከል ይቻላል…


ቸር ነገር ያሳየን ያሰማን!!!
187 viewsWon Getaneh, 14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 10:37:24

190 viewsWon Getaneh, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 12:58:55 ክርስቶስ ተንስአ ሙታን በአብ ሀይል ወስልጣን

አጋዞ ለአዳም አሰሮ ለሰይጣን እምዜሰ ኮነ ፍሰሐ ወሠላም…
238 viewsWon Getaneh, 09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-12 12:40:17 "ህፃናት መች ነው ጥርስ ማብቀል ያለባቸው?" - ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ሐኪም
.
ህፃናት እስከ መች መብቀል አለበት? ካልበቀለ መች ወደ ባለሙያ መመሄድ አለባቸው? የጥርስ መብቀል ከተቅማጥ በሽታ ጋር ይገናኝ ይሆን? ስለ ህፃናት የጥርስ እድገት ትንሽ ጀባ ልበላችሁ
.
ብዙ እናቶች ልጆቻቸው ጥርስ መች ማብቀል እንደሚጀምሩ በግልፅ ስለማያውቁ ልጄ እስካሁን ጥርስ አላበቀለም/ አላበቀለችም ብለው ጤና ተቋም ሲመጡ ማየት የተለመደ ነገር ነው። አንዳንድ እናቶች ደግሞ እስከመች ድረስ ሊያድግ እንደሚችል አያውቁም በዚህ የተነሳ እራሳቸውን ሲያጨናንቁ እናያለን ይህን ጭንቀታቸውን ለመቅረፍ እኔም ካነበብኩት ትንሽ ጀባ አልኳችሁ።
.
የህፃናት የጥርስ እድገት በጨቅላዎች እና በልጆችዎ ድድ ውስጥ የጥርስ መብቀልን ያመለክታል ይህ የሚጀምረው ብዙውን ጊዜ ልጅዎ ከ6 እስከ 8 ወር ዕድሜ ሲኖረው ሲሆን፡፡ ልጅዎ የ30 ወራት ዕድሜ ላይ ሲደርስ ሁሉም 20 የህጻናት ጥርሶች ቦታቸውን ይይዛሉ ፡፡
.
አንዳንድ ልጆች ግን ከ8 ወር ዕድሜያቸው በሗላም ቢሆንም ምንም አይነት ጥርስ ላያሳዩ ይችላሉ ፣ ይህ ግን ብዙውን ጊዜ የተለመደ ቢሆንም ምንም ጥርስ አስከ 13 ወር ካልበቀለ ለባለሙያ ማሳየት ይገባል፡፡
.
ብዙውን ጊዜ ሁለቱ የታችኛው የፊት ጥርሶች (የታችኛው ኢንሲዘሮች) ቀድመው ይበቅላሉ፡፡ ቀጥለው ሁለቱ የላይኛው የፊት ጥርሶች (የላይኛው ኢንሲዘሮች) ያድጋሉ፡፡
.
ከዚያም ሌሎች ወተት ጥርሶች (ኢንሲዘሮች) ፣ የላይኛውና የታችኛው መንጋጋዎች ፣ የውሻ ክራንቻዎች፣ በመጨረሻም የላይኛውና የታችኛው በጥልቀት የሚገኙት መንጋጋዎች ይበቅላሉ፡፡
.
ልከጆች ጥርስ ማብቀል ሲጀምሩ ምን አይነት ምልክቶች ያሳያሉ ??
.
- መነጫነጭ ወይም ብስጩነት ማሳየት
- ጠንካራ ነገሮችን መንከስ ወይም ማኘክ
- ልጋግ ማዝረብረብ ብዙውን ጊዜ ጥርስ ማደግ ከመጀመሩ በፊት የሚከሰት ነው
- የድድ ማበጥና መጠንከር
- ምግብ እምቢ ማለት
- የእንቅልፍ ለመተኛት መቸገር
.
መፍትሄውስ ምን ይሆን?
.
በዚህ ጊዜ ማድረግ ያለብን ልጅዎ የማያኝካቸው ቀዝቃዛ ነገሮች መስጠት። ለልጅዎ ለስለስ ያሉ ምግብ ይስጦቸው
በቀስታ ጥርስ የሚበቅልበት ቦታ በእጅ መንካት። በዚህ መንገድ የልጅዎን የጥርስ እድገት አብረው በመሆን የተሳካ ያድርጉላቸው።
.
መልካሙን ሁሉ ተመኘው
አንብበው ሲጨርሱ ለወዳጅ ዘመድዎ በቀናነት ሼር ያድርጉት

@HakimEthio
283 viewsWon Getaneh, 09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 18:37:14 ኤድና የጥርስ ክሊኒክ

=>100% ከጀርም ነጻ የሕክምና መሣሪያዎች 

=>የሚፈልጉትን የሕክምና መረጃ በነጻ ይሰጣል

=>ግልጽ የሖነ እና በቢዝነሥ ያልተበረዘ ሕክምና

=>ወቅቱን ያገናዘበ የሕክምና ክፍያ


⇒እነዚሕን የት ያገኛሉ? ኤድና የጥርስ ሕክምና

አድራሻ : CMC ሚካኤል ፊት ለፊት  Enjoy Burgur ማቲ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ

ስልክ 0911642527
284 viewsWon Getaneh, 15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 16:33:51 በአለም ላይ 3.5ቢሊዮን የሚሖን ህዝብ በአፍ ውስጥ በሽታ ይጠቃል
ከነዚህ ውስጥ

1. ሕመም
2. የፊት ቅርጽ መበላሸት
3.ምቾት ማጣት
4. ሞት ጭምር ሊያጋጥማቸው ይችላል
334 viewsWon Getaneh, 13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 13:56:59
302 viewsWon Getaneh, 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 11:04:55 ለሕጻናት እና ታዳጊዎች ሰው ሰራሽ ጥርስ መትከል ይቻል ይሖን?


 አዎ ይቻላል!! 

ለታዳጊ ልጆች ለሁለት አላማ ሰው ሰራሽ ጥርስ ሊተከልላቸው ይችላል


የወተት ጥርሳቸው ካለጊዜው ቢነቀልባቸው ቋሚ ጥርሳቸው የሚበቅልበት ቦታ አጥቶ ተወላግዶ እንዳይበቅል ለመከላከል

(ከጎን እና ከጎን ያሉ የወተት ጥርሶች ተጠጋግተው የተነቀለውን ጥርስ ቦታ ይይዙታል) 

የተቦረቦሩ የውተት ጥርሶችን ይበልጥ እንዳይጎዱ ለመከላከል ሲባል ቀድሞ የተዘጋጁ ጥርሶች የተቦረቦረው ጥርስ ላይ ሊተከል ይችላል::
392 viewsWon Getaneh, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 12:14:12

365 viewsWon Getaneh, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 09:34:57 የሰኳር ህመም እና የአፍ ጤና ምን ግንኙነት አላቸው ?


የስኳር በሽታ በባህሪው የሰውነታችንን ተፈጥሮአዊ በሽታ የመከላከል አቅም የማዳከም፣ አፋችን ወስጥ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ጥንካሬ የማሳጣት፣ የምራቅ እጢዎችን ምራቅ የማምረት አቅም ማሳጣትና አፋችን በምራቅ እራሱን የማጽዳት አቅም የመንሳት ብሎም አፋችን ውስጥ የላሙ ምግቦች ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ  ያደርጋል።


እነዚህ ችግሮች ከሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ የተለያዩ የአፍ ውስጥ በሽታዎች በቀላሉ እንድንጋለጥ መንገድ ይከፍታል።  


አፋችን የያዛቸው እንደ ጥርስ እና አቃፊ ክፍሎች ድድ እና የድድ አጥንት በቀላሉ ሽባ የመሖን እና የጥርሶች ጥንካሬ ደካማ የመሖን እንዲሑም ብዙ ጥርሶች በአንድ ጊዜ የመነቃነቅ ባሕሪ ያሳያሉ

ጥርሶች ከመነቃነቃቸው በተጨማሪ በቀላሉ መቦርቦር እና ሕመም ሊያስከትሉ ይችላሉ

ሌላው በስኳር በሽታ ምክንያት አፋችን ለመጥፎ ጠረን በቀላሉ ሊጋለጥ ይችላል

እንደ አጠቃላይ አፋችን ውስጥ ያሉ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች ቁጥራቸው እየቀነሰ በተቃራኒው ጎጅ ባክቴሪያዎች ቁጥራቸው እየጨመረ አፈችን እና መላው አፋችን ውስጥ ያሉ ክፍሎች ለጎላ ችግር ይጋለጣሉ
355 viewsWon Getaneh, 06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ