Get Mystery Box with random crypto!

'…በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው። እነሆ፥ ይፈርሳል፥ የፈ | መረጃ ቲቪ🇪🇹

"…በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው። እነሆ፥ ይፈርሳል፥ የፈረሰውም ተመልሶ አይሠራም፤ በሰውም ቢዘጋበት የሚከፍትለት የለም። እነሆ፥ ውኆቹን ይከለክላል፥ እነርሱም ይደርቃሉ፤ እንደ ገና ይሰድዳቸዋል፥ ምድሪቱንም ይገለብጣሉ። ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው።

"…መካሮችንም እንደ ዘረፋ ይወስዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ያሳብዳል። የነገሥታትንም እስራት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ያስራቸዋል። ካህናትን እንደ ዘረፋ ይወስዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል። ከታመኑ ሰዎችም ቋንቋን ያርቃል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈስሳል፥ የብርቱዎችንም መታጠቂያ ያላላል።ጥልቅ ነገር ከጨለማ ይገልጣል፥ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።

"…አሕዛብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ እነርሱንም ያጠፋል፤ አሕዛብንም ያሰፋል፥ እነርሱንም ያፈልሳቸዋል። ከምድር አሕዛብ አለቆች ዘንድ ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት በረሃ ያቅበዘብዛቸዋል። ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ እንደ ሰካራም ይቅበዘበዛሉ።" ኢዮ 12፥ 13-25


"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ