Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የታብሌት አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች፡- 1ኛ= ኦንላይን (Onli | 𝗘𝗧𝗛𝗜𝗢 𝗔𝗠𝗔𝗭𝗢𝗡 𝗦𝗧𝗢𝗥𝗘 🇪🇹🛒

የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የታብሌት አጠቃቀም የትኩረት ነጥቦች፡-

1ኛ= ኦንላይን (Online) ፈተና ለመውሰድ በየክፍሉ ማገኘት የሚገቡ የፈተና መሳሪያዎች በክፍል ተማሪዎች ብዛት ልክ ታብሌት ኮምፒዮተር , በየክፍሉ አንድ ላብቶኘ , ሶኬት, ቻርጀር, ጀኔሬተር(መብራት) ወዘተ ናቸው፡፡

2ኛ= ተፈታኝ ተማሪዎች ለ2 ሳምንት ከ2009 ዓ,ም እስከ 2011 ዓ,ም የ12ኛክፍል ተማሪዎች በሀገር አቀፍ የተፈተኑትን ፈተና ጥያቄዎች በየት/ቤታቸው ተገኝተው ይለማመደሉ፡፡ ግን ታብሌት ከት/ቤት ውጭ መውሰድ አይቻልም፡፡

3ኛ= ታብሌቱ በተለያዩ አሻራዎች ማለትም በ5 ጣቶች, በፊት ገፅ በጆሮና በአይን ከተማሪው ጋር ትውውቅ ያደረገ ስለሆነ ተማሪው ወደ ጎን ሲዞርና ሌላ ሠው ሲደረብ ታብሌቱ ይዘጋል፡፡ ስለዚህ ጥያቄ መስራት ስለማይቻል
በፍፁም ኩረጃን አያስተነግድም፡፡

4ኛ= ታብሌቱ የሚሠራው በዋይፋይ (Wi-Fi) በየክፍሉ በተዘረገው ሆኖ ቀጥታ አገር አቀፍ ማሰራጫ ጋር መረጃ ያስተላልፋል፡፡

5ኛ= ፈተናው አራትና ከዛ በላይ ኮድ ይኖረዋል፡፡

6ኛ= ዲሽ ሲተከል በነፃ ቦታ ወይም ዛፍና ተራራ የማይጋርድና ሲግናሎች
በቀለሉ የሚገቡበት መሆን አለበት፡፡ በተተከለው ዲሽ ብቻ ታብሌቱ ስለሚሠራ
ችግር እንዳይደርስ በአጥር አጥሮ በዘበኛ ማስጠበቅ አለበት፡፡ ዲሹ በቀጣይ ዲጂታል ቤተመፃህፍት አገልግሎት ስለሚሰጥና በቀጣይ ተማሪ ምዝገባ ከ9-12ኛ ክፍል ስለሚካሄድ የተሸሉ ተማሪዎችን ለመምረጥ ስለሚሰራ በጥንቃቄ መያዝ አለበት፡፡

7ኛ= ታብሌቱን ለተማሪዎች የሚያሰለጠኑ ባለሙያዎች በየት/ቤቱ ይመደበሉ፡፡

8ኛ= ፈተና ለሚያስፈፅሙ መ/ራንና ለሌሎች አካለት ስለ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አጨጭር ስልጠናዎች ይሠጣሉ፡፡

9ኛ= ፈተናው በኦን ላይን (online) መሰጠቱ ወጭ ከመቀነስ አኳያ በወረቀት
ግዥ, በቀለም ግዥ, ፈተና በጓጓዝ, በእርማት ወዘተ ከሚያወጠው ወጪ
በአምስት እጥፍ ያነሰ ነው፡፡

10ኛ= የፈተና ውጤቱን ለተማሪዎች ሞራል ካልሆነ ፈተና እንዳጨረሱ
መለፊያውን ውጤት ማወቅ ይቻላል፡፡ ግን በቀናት ልዩነት ውጤቱን እንዲየውቁ
ይደረገል፡፡

#SHARE

@MEREJAET @MEREJAETHIO_BOT #SHARE