Get Mystery Box with random crypto!

#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሃዋ ገላን ወረ | Ethio channel

#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን በሃዋ ገላን ወረዳ (መንደር 20 እና መንደር 21) ላይ ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ ንፁሀን ዜጎች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል።

ኮሚሽኑ ሁኔታውን እየተከታተለ መሆኑና እና ከአካባቢው ተርፈው የሸሹ ሰዎችን ማረጋገሩን አመልክቷል።

ኮሚሽኑ ጥቃቱ ያደረሱት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ሸኔ) አባላት መሆናቸውንና ግድያውም ከጥዋት አንስቶ መጀመሩን ምንጮቼ አመልክተዋል ብሏል።

ኢሰመኮ የመንደር 20 እና መንደር 21 ነዋሪዎች በዋናነት የአማራ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን መረዳቱንም ገልጿል።

የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ወደ አካባቢው መድረሳቸው ተነግሯል ያለው ኢሰመኮ ነዋሪዎቹ ግን ወደ ሌላ ቦታ ሄደው መጠለላቸውን ቀጥለዋል ሲል ሁኔታውን አስረድቷል።

የኢሰመጉ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ " በአካባቢው የቀጠለው የጸጥታ ችግር እና በነዋሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ብሔር ተኮር ግድያ በአስቸኳይ መቆም አለበት " ሲሉ አሳስበዋል።

ተጨማሪ የንፁሃንን ሞት ለመከላከል መንግስት የፀጥታ ኃይሉን እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።

@adis_mereja